ማውጫእቴጌ የተመኙ፣ የቴዎድሮስ ፍቅረኛነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝአልቱሪዝም ወይስ ምክንያታዊነት?የዕምነት መንገድየነፋስ ፊርማ(ሰው ማነው?)ደብረ ሮሐየሃይማኖት ፍልስፍና የመጽሐፍ ግብዣውብአረገ አድምጥልዑልሰገድ አስማማውዮዲት አማኑኤልነቢል አዱኛሲራክ ወንድሙሲልአምላክ አሰፋባይራ ዲጅታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7ሐብታሙ ውበት (ካሙ)518283443466337
ባይራ ዲጅታል መጽሔትየዝግጅት ክፍልበማህበራዊ ገጾቻችን ያግኙን www.bayradigital.comግራፊክስ ዲዛይን አርታኢዋና አዘጋጅ ምክትል አዘጋጅዮናስ ኃይለማርቆስ ልዑልሠገድ አስማማውውብአረገ አድምጥ ሩት ሃብተማርያም
እቴጌ የተመኙ፣ የቴዎድሮስ ፍቅረኛውብአረገ አድምጥመንደርደሪያእንደ ብሳና ቅጠል እየተበጠሰ ያለፈውን ዘመን ሲገረምሙት ይደንቃል። ዞር ብለው ሲያዩት ያስገርማል። ከተራው ህዝብ እስከ ነገስታት ድረስ ለስጋ ፈቃዳቸው ያልመሰረቱት ስርዓት መች አለና።ከእነዚህ ስርዓቶች ውስጥ አንዱ የቁባት ጉዳይ ነው። ነገስታት ከህጋዊ ሚስቶቻቸው ውጪ ለገላቸው መፈተሻ፣ ለስሜታቸው ማደሻ ብዙ የጭን ገረዶችን ወይም ዕቁባት ያስቀምጡ ነበር። ይሄ ልምድ በእኛ ሀገር ብቻ የነበረ አይደለም። ታላቁ የመጽሐፍ ቅዱሱ ሰሎሞን እንኳን ከ300 በላይ ዕቁባቶች ነበሩት አሉ።በብዛት ወንድ ነገስታት ሴት ዕቁባትን ያበጃሉ። ታሪክን ስንፈትሽ እንደ ቻይና ባሉ ሀገራት የወንድ ዕቁባትም ነበሩ ይባላል።አንዳንድ ዕቁባቶች ብልሃታቸውንና አጋጣሚዎችን ተጠቅመው ዙፋን እስከሞቆናጠጥ የደረሱ አሉ። ለምሳሌ ያህልም የዘመናዊ ቻይና መስራች ተብላ የምትጠራዋን ሲዢን (Empress Dowager Cixi (1835-1908)) መጥቀስ ይቻላል። ገና በአስራ ስድስት ዓመቷ ለንጉሱ 11 እቴጌ የሚለውን የማዕረግ ስም የምጠቀመው ራሱ ንጉሱ ቴዎድሮስ በደብዳቤው እቴጌ የሚለውን ማዕረግ ስለተጠቀመ ነው። እንጂ ተክለጻድቅ መኩሪያም ሆነ ጳውሎስ ኞኞ ወይዘሮ የተመኙ የሚለውን ስም ተጠቅመዋል።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 5
ዕቁባትነት ተመርጣ፣ በሂደትም የንጉሱን ሞት ተጠቅማ መንገስና ዘመናዊት ቻይናን ያህል ሀገር የቀረጸች ንግስት ነበረች።ብዙዎቹ ግን ለዙፋን ባይበቁም የንጉሱን ጭን አሙቀው፣ በስጋ ድሎት ተንደላቀው አልፈዋል።የዘመናዊ ኢትዮጵያ መስራች ተብለው የሚታወቁት አጼ ቴዎድሮስም ብዙ ዕቁባት ነበሯቸው ይባላል። በተለይ ከሚወዷት ሚስታቸው ከ እቴጌ ተዋበች አሊ ሞት በኋላ በየቦታው ዕቁባት አስቀምጠው ነበር። ከሁሉም ዕቁባት ግን በንጉሱ ዘንድ እጅግ የምትወደደዋ ወይዘሮ የተመኑ ነበረች ሲሉ የታሪክ ሰዎች ይመሰክራሉ። ይሄን ታሪክ መሰረት አድርጎ ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “የማለዳ ድባብ” በሚለው የግጥም ምድብሉ “የቴዎድሮስ ማመንታት በመቅደላ” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ግጥም ጽፎልናል።እቴ የተመኙ፥ ውዴ ውዴ ውዴከጉድጓዴ አጠገብ፥ የበቀልሽ አበባ የመሞት ምክንያት፥ ብዙ ቢኖረኝምየመኖር ምክንያት፥ አንቺን ብቻ አግኝቸሞት እሾህ ገላውን፥ ለማቀፍ ቢያምረኝምጥቂት አመንትቸጣፋጭ ገሃነሟን፥ ጭኗን ለማን ትቸመንገድ የሚያሳየኝ፥ ኣይኗን ለማን ትቸወይን ፈገግታዋን፥ ሳቋን ለማን ትቸእያልሁ አመንትቸ፤እቴ የተመኙለካ እንደዚህ ያምራል፥ የምስራቅ ወገግታለካ እንደዚህ ዉብ ነው፥ የሰማይ ፈገግታለካ ልብ ይሰርቃል፥ የዛፎች ኮሽታለካ እጣን ያስንቃል፥ የርጥብ አፈር ሽታደጁ ላይ እስኪደርስ፥ የሞት ኮቴ ዳናሰው የኑሮን ዋጋ፥ መቸ ይረዳና፤ላጭር ስልጣን ዘመን፥ ላንዳፍታ ክራሞትባቅመቢስ ሕዝብ ላይ፥ የነዛሁት ሺ ሞትሲያንዣብብ በኔው ላይ፥ በኮሶ ላይ አሞትደብልቄ እንደጠጣሁባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 6
ጫፍ አልባ ምሬቱንመግለጫ ቃል አጣሁ፤እቴ የተመኙሽሽግ እመቤቴእጅግ የወደድሽኝ፥ ያውም ከነብደቴያለፈው ትዝታ፥ ባይን ጠርዝ ሽው ሲልእንደ ቆንጆ ልጅ ኩልምንም ጀግና ቢሆን፥ ሰው ለሞት አይቸኩል።ይላል።በገጣሚው ምናብ ንጉሱ ለሞት ሲዋከቡ በህሊናቸው ሽው ካሉባቸው ነገሮች ውስጥ የቁባታቸው የእተጌ የተመኙ ነገር ነው ይለናል። ከህጋዊ ሚስታቸው ይልቅ የቁባታቸው ፍቅር ያየለባቸው ንጉሱ፣ ከልጃቸው ይልቅ የእቴጌ የተመኙ ፍቅር የጠናባቸው ንጉሱ፣ ጸጸት የሚመስል ኑዛዜም ሲያስቀምጡ ያሳየናል።ገጣሚው ከሁሉም ክስተቶች ስለምን የንጉሱን ማመንታት በእተጌ የተመኙ ዓይን በኩል ለመመልከት ፈለገ? ብሎ መጠየቅ የአባት ነው። እነ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ንጉሱን አጀግነው ከመቅደላ አፋፍ ላይ እንደ አርማ ሲሰቅሉት፣ እነ ጌትነት እንየው ራዕዩን ከፍ አድርገው ሲያስቀምጡት፣ በዕውቀቱ ስለምን በሴት በኩል መጣ? ከሴትም በቁባት በኩል ምን ያደርጋል?ለዚህ ምክንያቱን ግጥሙን ከጨረሰ በኋላ እንዲህ ሲል አስቀምጧል። “እቴ የተመኙ የአጼ ቴዎድሮስ ተወዳጅ ፍቅረኛ ነበረች። አጼ ቴዎድሮስ በመቅደላ አምባ ላይ ከማይጋፋው ጠላቱ ጋር በተፋጠጠበት በዚያ ቀውጢ ወቅት የናፍቆት ደብዳቤዎች ይልክላት ነበር። ባንዱም ደብዳቤ ውስጥ ‘አይዞሽ በእግዚአብሔር ሃይል አፈር ካልለበስሁ ሳላይሽ አልቀርም። አትባቢ’ የሚል በተስፋ መቁረጥና በተስፋ ማድረግ መሀል የወደቀ ቃል ይነበባል. . . የኔን ግጥም የቀሰቀሰው ይሄ አንጀት የሚበላ መስመር ነው።” ይላል።እንደ በዕውቀቱ ስዩም ጽሑፍ ከሆነ አጼ ቴዎድሮስ ይሄን ደብዳቤ ለቁባታቸው ይልኩ የነበሩት በመቅደላ ከጠላት ጋር እየተጋፈጡ ነው።የታሪኩ ጉዳይ አሻሚ ቢመስልም ንጉሱ ልባቸው ፍስስ ይልላቸው የነበሩ አንድ ቁባት እንደነበሩ ግን እሙን ነው። ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 7
ዳሩ ግን ስለ እቴ የተመኙ በስፋት ሲነገር አይስተዋልም። እኔ እስከማውቀው ድረስ ቴዎድሮስን አስታክኮ በግጥሙ ሊያነሳቸው የሞከረው በዕውቀቱ ብቻ ነው። እኛስ ስለ እኒህ የንጉስ ቁባት ለማዎቅ ብንፈትሽ ምን አለበት?እቴ የተመኙ ማናቸው?ስለ እቴጌ የተመኙ ውልደትና ዕድገት ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ቴዎድሮስ” በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 314 ሆርሙዝ ራሳምን ጠቅሰው እንዲህ ይላሉ። “. . . የተመኙ ቴዎድሮስ የሚወዷቸው እተጌ ናቸው። የአንድ የየጁ ኦሮሞ(ስሙ ለዛሬው አጠራር እንዲመች በእኔ የተቀየረ) ሚስት ነበረች። ውብ ነበረችና ውበቷን (ቴዎድሮስ) ሰሙ። ከዚያ በኋላ አስመጥተው ክርስትና አስነሷት። ወይዘሮ የተመኙ ወፍራምና ውብ ሴት ነበሩ።” ይለናል።ከላይ እንዳየነው ትውልዳቸው ከየጁ ኦሮሞ እንደሆነና ውብ ወፍራም ሴት እንደሆኑ ይገልጻል።ጳውሎስ ኞኞ እንዲህ የሚል ተጨማሪ ጽሑፍም አላቸው።“ወይዘሮ የተመኙ አጤ ቴዎድሮስ ከነበሯቸው ዕቁባት ሁሉ የሚወዷቸው ሴት ነበሩ። ቴዎድሮስ ወይዘሮ የተመኙን የያዙት ገና እቴጌ ተዋበች ሳይሞቱ በፊት ጀምሮ ነው። ተዋበች ሞተው ጥሩ ወርቅን ካገቡ በኋላ እቴጌ ጥሩወርቅ የቴዎድሮስን ዕቁባት ሁሉ ማየት እንደማይፈልጉ ነግረዋቸው አጤ ቴዎድሮስም ቁባቶቻቸውን ሁሉ ሲያባርሩ ወይዘሮ የተመኙን ግን አላባረሩም ነበር። ቴዎድሮስ በወይዘሮ የተመኙ ላይ የነበራቸው ፍቅር የተለየ ነበር። አጤ ቴዎድሮስ ራቅ ካለ ቦታ በሚሄዱበት ጊዜ ከሚስታቸው ይልቅ ለወይዘሮ የተመኙ የፍቅር ደብዳቤ ይጽፉላቸው ነበር። በደብዳቤያቸው ላይም ‘እህቴ፣ የእናቴ ልጅ አትባቢ፣ አይዞሽ በቅርቡ አይሻለሁ’ እያሉ ይጽፉላቸው ነበር።” ይላል።እቴ የተመኙ በቴዎድሮስ እጅግ እንደሚወደዱ፣ ገና ያኔ ተዋበች ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 8
ሚስታቸው እያለች ቁባት አድርገው እንደያዟትና አትባቢ እያሉ ደብዳቤ ይጽፉላት እንደነበር አስንቷል።እቴጌ የተመኙ በራሱ በንጉሱ እቴጌ ተብለው የሚጠሩ ናቸው። TEWODROS AND HIS CONTEMPORARIES 1855-1868 በሚለው መጽሐፍ ላይ በገጽ 317 ስለ እቴጌዋ እንዲህ ያትታል።“Apparently one of the kings acknowledged wives, as indicated by the use of the title Itege. By Europeans Yetemegnu was in 1866-1868 referred to variously at the kings Itege and his ‘favorite’ or ‘concubine’. She was still at the side of the king when the members of the British mission and the earlier prisoners were sent to Meqdela in July 1866.” ይላል። ይሄም ማለት በንጉሱ ዘንድ ተወዳጅ የነበረችው እቴ የተመኙ የእንግሊዛውያን እስረኞች ወደ መቅደላ ሲጋዙ እዚያው በመቅደላ የነበረች ናት ይለናል ።እነዚህን የተለያዩ የታሪክ ጥቁምታዎች ስንመለከት በህሊናችን ውስጥ የተለያዩ ጥያቄዎች መምጣታቸው አይቀርም።ለመሆኑ ከመቼ ጀምሮ ነው የንጉሱ ቁባት የሆኑት? እውን ንጉሱ ጳውሎስ ኞኞ እንዳለው እጅግ የሚወዷት የህግ ሚስታቸው እቴጌ ተዋበች በህይወት እያለች ጀምሮ እቴጌ የተመኙ ቁባታቸው ነበረችን? እንዲሁም ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም የንጉሱ ዳብዳቤዎች የተጻፉት ከጠላት ጦር ጋር ተፋጠው በነበረበት ወቅት ነው ይላል።በሌላ በኩል ጳውሎስ ኞኞ ደሞ አይ ንጉሱ ከመቅደላ ራቅ ወዳለ ቦታ ሲሄዱ ነው ይላል። የቱ ነው ትክክል? እስኪ አብረን እንዝለቅ።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 9
አንድ፣ ከመቼ ጀምሮ?እቴጌ የተመኙ የንጉሱ ቁባት የሆኑት ከመቼ ጀምሮ ነው ለሚለው ሃሳብ ክቡር አቶ ተክለጻድቅ መኩሪያ ዐጼ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ አንድነት በሚለው መጽሐፋቸው ከገጽ 235-238 ስለ እቴጌ የተመኙና ስለ አጼ ቴዎድሮስ ፍቅር እንዲህ ይላሉ።“ወደ መጨረሻው ዘመን በጥሩ ወርቅ ትዕቢትና በሌላውም ንጉሱ እየተበሳጩ ከፈረንጆቹም፣ ከመኳንንቶቻቸውም በተጣሉበት፣ የእንግሊዝ ጦር በመጣበት ሰዓት ከጥሩወርቅ የበለጠ ይንከባከቧቸውና ይወዷቸው የነበሩት ወይዘሮ የተመኙ ከርሳቸው አልራቁም።” ይላል።ስለዚህም በቴዎድሮስ የጭንቅ ሰዓት ከማንም በበለጠ ከንጉሱ ጎን መቆምና ፍቅርን መስጠት የቻሉ እቴጌ እሳቸው ነበሩ ብንል ማጋነን አይሆንም። ለመሆኑ ከመቼ ጀምሮ ነው ለንጉሱ ቁባት የሆኑት ለሚለው ጥያቄ ከጳውሎስ ኞኞ በተለየ መልኩ ተክለጻድቅ መኩሪያ እንዲህ ይላሉ።“ለዐጼ ቴዎድሮስ በግልጽ የምናውቃቸው ሚስቶቻቸው የመጀመሪያይቱ የራስ ዐሊ አሉላ ልጅ፣ የእቴጌ መነን ልጅ እቴጌ ተዋበችና እርሳቸው ካረፉ በኋላ ደግሞ በወግ በማዕረግ ያገቧቸው የሰሜኑ የደጃዝማች ውቤ ልጅ እቴጌ ጥሩወርቅ ናቸው።ነገር ግን በነዚህ መካከል በተለይ ከተዋበች ሞት በኋላ ወይዘሮ የተመኙ የሚባሉ የየጁ ተወላጅ ፍቅረኛ ወዳጅ እንደነበሩዋቸው አልፎ አልፎ በቃልም በጽሑፍም ተገልጿል። እስረኞቹን ለማስፈታት ከንግስት ቪክቶሪያ ተልኮ የመጣውና በመጨረሻም ራሱ እስረኛ የሆነው ሆርሙዝ ራሳም ወዳገሩ ከተመለሰ በኋላ በጻፈው መጽሐፉ በቴዎድሮስ ዘንድ የተወደደችው እቴጌ ሲላት የቀሩት ጸሐፊዎች የሚወዷት ቁባታቸው እንደነበሩ ይገልጻል።” ይላል።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 10
ከላይ እንዳየነው በጳውሎስ ኞኞ እና በተክለጻድቅ መኩሪያ መካከል ታላቅ ልዩነት እናስተውላለን። ጳውሎስ ኞኞ ቁባት አድርገው የያዟት ተዋበችም እያለች ጀምሮ ነው ሲል፣ ተክለጻድቅ መኩሪያ ደሞ ከተዋበች ሞት በኋላ እንደሆነ ያትታትል።ይሄን ልዩነት ሊፈጠረው የቻለው ንጉሱ ለወይዘሮ የተመኙ የጻፉትን ደብዳቤ ሲተረጉሙ ይሆናል ብለን እናስብ። ለዚህም አስረጂ TEWODROS AND HIS CONTEMPORARIES 1855-1868 በሚል ርዕስ ACTA AETHIOPICA VOLUME II ባሳተመው መጽሐፍ ገጽ 329 ላይ ንጉሱ ለወይዘሮ የተመኙ የጻፈውን ደብዳቤ እማኝ አድርጎ ያብራራል።የንጉሱ ደብዳቤ እንዲህ ይነበባል።“በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፣ ንጉስ ነገስት ቴዎድሮስ፣ ይድረስ ለእቴጌ የተመኙ፣ እንዴት ከረምሽ፤ እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። እናትሽንም እነ ወይዘሮ ሰናይትንም የቤቴን ሰዎች ሁሉ እንዴት ከረማችሁ አለ በይልኝ።አሁንም አይዞሽ። በእግዚአብሔር ሃይል ዐፈር ካልበላሁ ሳላይሽ አልቀርም። አትባቢ። ተዋበችንም ከነደጃች ጎሹ፣ ከነብሩ ዐሊ ስዋጋ ቋራ አስቀምጫት ነው። አሁንም ቋራ መቅደላ ነው። ነፍስና ስጋዬ ካልተለያየ የማልቀርበት ስፍራዬ ነው። በጳጉሜ 5 ቀን ተጣፈ።” ይላል።ከላይ እንዳየነው ጳውሎስ ኞኞን እቴጌ የተመኙ ገና ያኔ እቴጌ ተዋበች በህይወት እያለች ጀምሮ ነው ለቴዎድሮስ ቁባት የሆነችው እንዲል ያደረገው ይሄ ደብዳቤ ይመስላል። ምክንያቱም “…ተዋበችንም ከነደጃች ጎሹ፣ ከነብሩ ዐሊ ስዋጋ ቋራ አስቀምጫት ነው።…” የምትለዋ አረፍተ ነገር ያኔም ጀምራ ቁባት ነበረች የሚል ድምዳሜ የሰጠችው ይመስላል።የደብዳቤው መንፈስ ግን የሚያመላክተው ሌላ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ደብዳቤዎች በቴዎድሮስ የመጨረሻ ሰዓት የተጻፉ መሆናቸው ነው። እንዲሁም የደብዳቤው መንፈስ ያኔ ለተዋበች ምቹ ቦታ ቋራ ነበር። አሁን ደግሞ መቅደላ ነው። እያለ የሁለቱን ዘመን ያወዳድራል እንጂ ደብዳቤው በተዋበች ዘመን የተጻፈ አለመሆኑን TEWODROS AND HIS CONTEMPORARIES 1855-1868 በሚለው መጽሐፍ ገጽ 329 እንዲህ ተገልጿል።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 11
“Tewoderos’s statement about leaving Tewabech, his first acknowledged queen in Qwara, while fighting Against Goshu Zewdie and Biru Aligaz in the early 1850’s is meant to comfort Yetemegnu. As Tewabech had been safe in Qwara, so would Yetemegnu be safe, for Meqdela was now what Qwara had been in the early days. The last two sentences seem to reveal that Tewodros was reflecting on the course of his life, and on the possibility that it was probably approaching the end.” ይላል።ስለዚህ ንጉሱ የተዋበችን የያኔው ማረፊያዋ ቋራን እማኝ አድርጎ ለወይዘሮ የተመኙ መግለጹ ወይዘሮዋ በመቅደላ ተመቻችተውና ደህንነት ተሰምቷቸው እንዲቀመጡ ነው ማለት ነው። እናም እቴጌ የተመኙ የቴዎድሮስ ቁባት የሆኑት ከእቴጌ ተዋበች ሞት በኋላ ነው የሚለውን ድምዳሜ ብንወስድ የሚቻል ነው።ሁለት፣ ደብዳቤው መቼ ተጻፈ?ከላይ በበዕውቀቱ ስዩም ግጥም መጨረሻ በምክንያተ ጽሒፉ ላይ እንዳየነው ንጉሱ ደብዳቤውን ለእቴጌ የተመኙ ይጽፍላት የነበረው በመቅደላ አፋፍ ላይ ከጠላት ጋር እንደተፋጠጠ መሆኑን እንዲህ ሲል ይገልጻል። “አጼ ቴዎድሮስ በመቅደላ አምባ ላይ ከማይጋፋው ጠላቱ ጋር በተፋጠጠበት በዚያ ቀውጢ ወቅት የናፍቆት ደብዳቤዎች ይልክላት ነበር።” ይላል።ተክለጻድቅ መኩሪያ እንዲህ ሲል ይገልጽልናል።“ደብዳቤው የሚያስረዳን ቀድሞ በንጉሰ ነገስትነታቸው ዘመን ዋዜማ ላይ ከጎጃሙ ባላባት ከነደጃዝማች ጎሹ ጋር፣ ከየጁው ባላባት ከነደጃዝማች ብሩ አሊ ጋር በሚዋጉበት ዘመን ደንበኛ ባልቤታቸውን እቴጌ ተዋበችን ከትውልድ ሀገራቸው ከቋራ ማስቀመጣቸውን አሁንም በእርሳቸው አልገዛም ብሎ የሸፈተባቸውን ለማሳመን ወዲያና ወዲህ በሚባክኑበት ጊዜ ምንም እንኳን በመካከላቸው ልባዊ ፍቅር ባይኖርም በደንበኛ ባለቤታቸው በእቴጌ ጥሩ ወርቅ ላይ እኝህን ወይዘሮ የተመኙን ከልባቸው እንደሚወዷቸውና በመቅደላ ተራራ ለየት ካለ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 12
ቦታ አስቀምጠዋቸው ስለነበርና የተገናኙበትም ጊዜ ረዘም ያል ስላለ ሴትዮዋን ለማጽናናት የተጻፈ ነው።’’TEWODROS AND HIS CONTEMPORARIES 1855-1868 በሚለው መጽሐፍ ላይ ደብዳቤው የተጻፈበትን ቀንና ዓመተ ምህረት እንዲህ ያስቀምጥልናል።እንደሚታወቀው ንጉሱ ከደብረታቦር ተነስተው መድፋቸውን እያስጎተቱ መቅደላ የደረሱት መጋቢት 22 1860ዓ/ም2 እንደሆነ ተክለጻድቅ መኩሪያ ይገልጻሉ።ንጉሱ ራሳቸውን የሰውት በሚያዝያ 1860 በዕለተ አርብ ነው። ከላይ ያየነው ደብዳቤ ደግሞ ተጻፈ የሚለው በጻጉሜ 5 ቀን ነው። ስለዚህ ደብዳቤው ሊጻፍ የሚችለው ከሚያዝያ 1860 ዓ/ምበፊት ነው ማለት ነው። ምናልባት ተክለ ጻድቅ መኩሪያ እንዳሉት ንጉሱ ሰላም ለማስከበር በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ነው ማለት ነው።TEWODROS AND HIS CONTEMPORARIES 1855-1868 በሚለው መጽሐፍ ላይ የተቀመጠው ቀን September 09, 1867 G.C ይላል። ስለዚህ ከላይ ያነሳነውን ሃሳብ ያጠናክርልናል ማለት 2 አቶ ተክለጻድቅ መኩሪያ ዐጼ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ አንድነት ገጽ 373ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 13
ነው።ንጉሱ አትባቢ እያለ እቴጌ የተመኙን የሚያበረታበት ግጥም የተጻፈው ንጉሱ በመቅደላ ከጠላት ጋር እየተፋጠጠ ሳይሆን ከመቅደላ ርቆ በሚኖርበት ወቅት ማለትም በጳጉሜ 5 ቀን 1859 ዓ/ም ነው ማለት ነው።ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም እንደሚለው በመቅደላ ተራሮች ላይ ከጠላት ጋር እየተፋጠጠ ሳይሆን እቴጌ የተመኙን በመቅደላ አስቀምጦ እሱ ግን ከመቅደላ ርቆ ሰላም ለማስከበር በሚንቀሳቀስበት ወቅት የተጻፈ ደብዳቤ ነው ማለት እንችላለን።አጼ ቴዎድሮስ ለእቴጌ የተመኙ የላኩት አንድ ደብዳቤ ብቻ አይደለም። TEWODROS AND HIS CONTEMPORARIES 1855-1868 በሚለው መጽሐፍ ላይ በአጠቃላይ ሰባት ደብዳቤዎች ተካተዋል። ስለሌሎች ደብዳቤዎች ተክለጻድቅ መኩሪያ እንዲህ ይላሉ።“ሌሎች ለእቴጌ የተመኙ የጻፏቸው ዳብዳቤዎች በይዘትም በቅርጽም ተመሳሳይ ናቸው። ባንደኛዋ ደብዳቤ ግርጌ ከሰላምታ ቀጥሎ ‘አይዞሽ የእናቴ ልጅ፣ ነፍስና ስጋዬ ካልተለያየ ሳላይሽ አልቀርም’ የሚል የናፍቆት ዐረፍተ ነገር አለበት። ደብዳቤዎቹ ዓመተ ምህረት የሉባቸውም። ነገር ግን ደብዳቤዎቹን የጻፉዋቸው በመጨረሻ ዘመን ጓዛቸውን ወደ መቅደላ ካወጡና የሚጠረጥሩትን ሁሉ በግዞት መቅደላ ተራራ ላይ ባስቀመጡበት ወቅት ምናልባት እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1856-1860 ዓ/ም መካከል ሳይሆን አይቀርም።” ይላል።ስለዚህ ከላይ ላነሳናቸው ሁለት ጥያቄዎች በድርበቡም ቢሆን መልስ አግኝተናል።አንድ፣ አጼ ቴዎድሮስ እቴ የተመኙን ቁባት አድርገው የያዙት ተዋበች ከሞተች በኋላ ነው።ሁለት፣ ደብዳቤውን የጻፉት መቅደላ ላይ ሆነው ከእንግሊዝ ጦር ጋር እየተፋጠጡ ሳይሆን ሰላም ለማስፈን ከመቅደላ ራቅ ብለው፣ ግን በመቅደላ ለሚገኙት ቁባታቸው ጻፉት ብንል ያስሄዳል።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 14
ከዚያስ?እንዲህ በንጉሱ የሚወደዱ ቁባት ንጉሱ ከሞቱ በኋላ ወዴት ሄዱ? እኒህ በታሪክ ውስጥ ስፍራ ያላቸው ሴት፣ ቴዎድሮስን በሚያህል ቁጡ ንጉስ የሚወደዱ፣ እንዲያ በናፍቆት ደብዳቤ የሚጻፍላቸው፣ ከንጉሱ የህግ ሚስት የላቀ መወደድ የነበራቸው ሴት ወዴት ሄዱ ይሆን?መይሳው ለክብሩ በራሱ ላይ ሲጨክን፣ የመቅደላ አምባ ትርምስምሱ ሲወጣ፣ የናፒር ጦር በአምባው ላይ ሲፋንን እሳቸው ወዴት ሄዱ? በዚያች ቀውጢ ሰዓትስ ምን ነበር ሚናቸው? ለእነዚህና መሰል ጥያቄዎች የሚያረካ መልስ ማግኘት ይከብድ ይሆናል።ጳውሎስ ኞኞ ግን በመጽሐፋቸው ገጽ 313-14 እንዲህ ይላሉ።“እቴጌ ጥሩ ወርቅ፣ ልዑል ዓለማየሁና ወይዘሮ የተመኙ እንግሊዞች ጦር ሰፈር ገብተው ጥቂት ከቆዩ በኋላ የእንግሊዝ ጦር መመለሻ ስለደረሰ የቴዎድሮስ ቤተሰቦችና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ከእንግሊዞች ጦር ጋር አብረው ለመጓዝ ተነሱ። ምንም ዓይነት ክብር ባልጎደለበት ጉዞ እየተጓዙ ዋድላ ሲደርሱ የተከዜን ወንዝ ሳያቋርጡ፣ ሳንጣራ ላይ ወይዘሮ የተመኙ ተለይተው የተሰጣቸውን ስጦታ ይዘው ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ የጁ ሄዱ።” ይላል።ይሄን ጽሑፍ እማኝ አድርገን የእቴ የተመኙ የመጨረሻ ዘመናቸው በትውልድ ቀያቸው በየጁ እንዳለፈ መገመት ይቻላል። እኒያ በውበታቸው ንጉሱን የማረኩ ሴት፣ በመጨረሻ መተማመኛ ንጉሳቸው ሲወድቅ በምን አይነት ስብራትና ሀዘን ወደ ትውልድ ስፍራቸው ተመለሱ ይሆን? ከዚያ በኋላስ ለሌላ ቁባት ሆነው ነበርን? በመጨረሻ ዘመናቸውስ በትዝታ እንደምን ይቆዝሙ ነበር? መሰልና ሌሎችንም ሃሳቦች ያጭራል።ስንቋጨውበአንድ ወቅት የሀገራችን ንጉስ የነበረ ሰው ውድ ሚስቱን አጣ። አባቷን አስሮ ካገባት ሁለተኛ ሚስቱ የሚሻውን ክብርና ፍቅር አጣ። የየጁዋን ውብ ሴት ቁባቱ አድርጎ ያዘ። እሱ አክብሮ እቴጌ ብሎም ይጠራት ነበር። ለደህንነቷ ከመቅደላ አፋፍ አስቀመጣት። ሰላም ሊያሰፍን ከመቅደላ ራቅ ሲል በናፍቆት ደብዳቤ ይጽፍላት ነበር።በመጨረሻም ያ ንጉስ ራሱን ሰዋ። ፍቅሩም በትዝታ እየነጎደች ካደገችበት ቀዬ ከተመች። ይሄ የሚገርም ታሪክ፣ የትናንትናችንም አካል ነው።የዘመናችን ገጣሚ በዕውቀቱ እነዚህን የንጉሱን ደብዳቤዎች አንብቦ ልቡ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 15
ተነካ። ራሱን ከንጉሱ ቦታ አድርጎ፣ ከቁርጠኛነቱ ይልቅ ማመንታቱን በቁባቱ በኩል አሳየን። ንጉሱ ከራሱም አስበልጦ ይወዳት ነበርና ነው ለነፍሱ ሳይሳሳ ለፍቅሩ ያሰቀለለው እያለን ይሆን?እናም የገጣሚውን የመጨረሻ ቃል ተከትለን፣ አስረጂዎች በፈቀዱልን ልክ የእቴጌዋን ማንነት፣ የደብዳቤዎችንም የጽሕፈት ዓመት ለመፈተሽ ሞከርን። ነገም ይቀጥላል። የሰው ልጆች ዛሬ የነጋቸው መስታውት ነውና ከታሪኮቻችን ሰበዝ እየመዘዝን እንዲህ እንጨዋወታለን።ሁሉንም የንጉሱን ደብዳቤዎች ለምትሹ TEWODROS AND HIS CONTEMPORARIES 1855-1868 ከሚለው መጽሐፍ ላይ አምጥተን ከታች አቀምጠናቸዋል። የንጉሱን የፍቅር ቃላት እያነበባችሁ በትዝታ ወደኋላ ትሸመጥጡ ዘንድ እነሆ።መልካም ጊዜ።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 16
አልቱሪዝም ወይስ ምክንያታዊነት?ዮዲት አማኑኤልI am likely to behave altruistically towards individuals who share a high proportion of my genes Or if you scratch my back I will scratch yours!!አንድ መድረክ ነው። ስለ ሰውነት ይደሰኮራል።“ሰው መሆን እንዲህ ነው። ሰው መሆን እንዲያ ነው”አንድ ንግግር ግን ያዘኝ ሰው መሆንን በእናትነት መስሎታል። እናት??እናት በሁላችንም አእምሮ ውስጥ የምትወከልባት ተመሳሳይ ምስል አላት። አዛኝነት፣ ለሌሎች መራራት፣ የራስን ምቾት ህይወት ወደጎን በመግፋት ራስን አሳልፎ መስጠት፣ ለሌሎች መትረፍ... ወዘተረፈ። ይሄ ንግግር ጥያቄ ፈጠረበኝ። ግን እኮ እናት ለልጆቿ፣ ለቤተሰቧ የምታሳየውን ባህሪ ሌሎች ህይወት ያላቸው ነገሮችም በተመሳሳይ ለራሳቸው ዝርያ፣ ለቤተሰባቸው የሚያሳዩት ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። ቤተሰባቸውን እና መሰሎቻቸውን ለመጠበቅ ራሳቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊትን ይፈፅማሉ። በአደጋ ጊዜ ሌሎችን ለማሸሽ ራሳቸውን መስዋዕት ያደርጋሉ። ይህንንም ሂደት አልቱሪዝም (self-sacrifice) ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 18
እንለዋለን። ታድያ ይህ ባህሪ እንዴት የሰውን ልጅ ከሌላው እንዲለይ ያደርገዋል?ለምሳሌ የሌሊት ወፎች ከሁለት ቀን በላይ ካለምግብ መቆየት አይችሉም። ይሞታሉ። ነገር ግን ራሳቸውን ለማቆየት ምግብ ያገኘው የሌሊት ወፍ ላላገኘው የራሱን ደም ይሰጠዋል። በዚህ ሁኔታ ምግብ ያላገኘው የሌሊት ወፍ በህይወት መቆየት ይችላል። በሌላ ጊዜ ደም ለጋሹ ምግብ ሲያጣ ያኔ ደም የተለገሰው በተራው ደም ይሰጠዋል። በዚህ ሂደት ለረዥም ጊዜ በህይወት ለመቀጠል ያስችላቸዋል።ሽኮኮዎች ደግሞ አንድ ጭልፊት በሰማይ ላይ ሲታይ አንድ ሽኮኮ ጭልፊቱን አይቶ ከፍተኛ እና ስለታም የማንቂያ ጥሪ ያስተላልፋል። ይህ ጥሪ ሌሎች ሽኮኮዎችን ጠላት እየመጣ እንደሆነ መልእክት ይሰጣቸዋል። ይህም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና እንዲሸሹ ይረዳቸዋል። የጮኸው ሽኮኮ ግን ራሱን አደጋ ላይ ይጥላል። ምን አልባት በጭልፊቱ የመበላት እድሉን ከፍ ያደርጋል። ግን ራሱን አደጋ ላይ በመጣል ቤተሰቡን እና ዝርያውን መጠበቅ ይችላል።ንብ ቀፎውን የሚዳፈር ጠላት ሊያጠቃቸው ሲመጣ በመናደፍ ሌሎችን ከአደጋ ትከላከላለች። ንብ አንዴ ከተናደፈች እጣፋንታዋ መሞት ብቻ ነው። ቢሆንም ግን ራሷን መስዋዕት በማድረግ የቀፎውን ህልውና ትጠብቃለች። እንደዚህ ያለው ድርጊትም ከአልቱሪዝም ይመደባል።በተመሳሳይ አንድ እናት ከእርግዝናዋ ጀምሮ፣ ልጅ በማሳደግ እና ቤተሰቧን በመንከባከብ ውስጥ የራሷን ፍላጎት እና ህይወት አሳልፋ በመስጠት፣ የልጆቿን እና የቤተሰቦቿን ህይወት እና ምቾት ታስጠብቃለች።አንድ አባትም ቤተሰቡን፣ አካባቢውን፣ ሀገሩን ከጠላት እና ከአጥቂ ለመጠበቅ ራሱን ለአደጋ ያጋልጣል።ሰዎች እና ህይወት ያላቸው ነገሮች የአልቱሪዝም ባህሪን ያሳያሉ። በግለሰብ ደረጃ ሲታይ ይህ ሞኝነት የተሞላበት፣ ራስን መስዋዕት የሚያደርግ ተግባር እና የዳርዊንን survival of the fittest የሚፃረር ባህሪ ይመስላል። ዝግመተ ለውጥ ከሚከናወንባቸው መንገዶች አንዱ ተፈጥሮአዊ ምርጦሽ (natural selction) ነው። ታድያ ይሄ ተፈጥራዊ ምርጦሽ የሚከናወንበት ዋነኛ እና የመጀመሪያው መሳሪያ ዘረመል (gene) ነው የሚለው ሪቮሊሽኒስቱ ሪቻርድ ዳውኪን ጂን ተኮር ህልዮቱን The selfish gene በተሰኘ ስራው አብራርቷል።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 19
በዚህም ስራው የተፈጥሮ ምርጦሽ ተፃራሪ የሚመስለው የአልቱሪዝም ባህሪ፣ በሁለት ስኬታማ መንገዶች ኢ-ንቅ በሆነው ራስ ወዳዱ ጂን አማካይነት ራሱን ለማሰራጨት እና ለማስቀጠል እንደሚጠቀም ገልጿል።አንደኛው kin selection (selfish gene)አንድ ግለሰብ የቅርብ ዘመዶቹን (ልጆቹን፣ ወንድሙን፣ እህቱን...) በመርዳት የራሱን ዘረመል ህልውና ማረጋገጥ ይችላል። ልጁን ለማዳን የሚሞት ወላጅ ወይም ዘመዶቹን አዳኝ መምጣቱን በመጮህ የሚያስጠነቅቅ ሽኮኮ፣ ዝግመተ ለውጡን ያሳልጡታል። ምክንያቱም በዛ መንገድ ከዘመዶቹ ጋር የተጋራውን የዘረመል ኮድ ህልውና ይጠብቃል።ይህንንም የHamiltonን ህግ ተጠቅሞ ያብራራዋል።rB>Cr = የጄኔቲክ ዝምድና (ሁለት ግለሰቦች ከአንድ የጋራ ቅድመ አያት በዘር አንድ አይነት ጂን የመጋራት እድል)ወላጅ እና ልጅ - 0.5 (50%)እህት እና ወንድም - 0.5(50%)አያት እና የልጅ ልጅ -0.25(25%)የአጎት እና የአክስት ልጆች- 0.125 (12.5%)B = ለተቀባዩ ያለው ጥቅም (ራሳቸውን በማባዛት የሚጨምርላቸው ስኬት)C = በአልቱሪዝም የሚወጣው ወጪ (ራሳቸውን በማባዛት ረገድ የሚያጡት) በዚህም አግባብ ለአልቱሪዝም የዋለው ጂን ለተቀባዮ ካለው ጥቅም ያነሰ ሲሆን ስርጭቱ ከዘመዶቻቸው ጋር ባላቸው የጄኔቲክ ዝምድና ይባዛል። ይህም ለጂኑ ከፍተኛ ስኬት ነው።የቅድሙን ምሳሌ እንይ ሽኮኮ እነሱን ሊያጠቃ የመጣውን ጭልፊት የማንቂያ ጩኸት አሰምቶ እህትና ወንድሞቹን ይታደጋል። በዚህ ሂደት እሱ በጭልፊቱ ሊበላ ይችላል። ያንን C እንለዋለን። ከእህት እና ከወንድሞቹ ጋር ደግሞ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 20
0.5% ተመሳሳይ ጂን ይጋራሉ። በዚህ ሂደት ያተረፋቸው የእህት እና ወንድሞቹ ያገኙት አንፃራዊ ጥቅም(B) ከሚጋሩት የጄኔቲክ ዝምድና ጋር ይባዛል።ሁለተኛው Reciprocal Alturism ነው። Scratch my back I’ll scratch yours!ይህ አልቱሪዝም ዛሬ ሌሎችን በመርዳት ነገ ውለታው እንደሚመለስለት በማሰብ የሚደረግ መስዋዕትነት ነው። በዚህ መሀል ውለታው ከተመለሰለት ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህን ማህበራዊ መዋቅሮችን፣ ትውስታን እና አጭበርባሪዎችን (Cheaters) የመለየት ችሎታን ይጠይቃል። ደም የሚጋሩትን የሌሊት ወፎችን እንደምሳሌነት ማንሳት ይቻላል።ሰዎችም በማህበራዊ ህይወታቸው ውስጥ እንዲህ አይነቱን የአልቱሪዝም ባህሪ ያሳያሉ። ዳውኪንስ እኒህ ተግባራት የሚዘወሩት ኢ-ንቅ በሆነው ራስ ወዳዱ ጂናችን አማካኝነት እንደሆነ ይነግረናል። ይኼ ባህሪ ሰዎች ከሌሎች የሚለዩበት ሳይሆን የሚጋሩት ባህሪ ነው።አልቱሪዝም ከማህበረሰብ እሴት አንፃር ለሌሎች ጥቅም እና ምቾት የራስን ፍላጎት፣ ምቾት አሳልፎ መስጠትን እንደቅዱስ ሞራል ይቆጥራል። ከፍ ሲልም ለሌሎች መኖር ህይወታቸውን አሳልፈው የሚሰጡ፣ ራሳቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ግለሰቦች እንደጀግና እና መልካም ሰው ይቆጠራሉ።በፍልስፍናው ጎራ አልቱሪዝም እንዴት ይታያል? ፍልስፍናው ከዝግመተ ለውጣዊ አተያይ በተለየ ንቁ በሆነው ህሊና በሰዎች ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ድርጊት አድርጎ ይመለከተዋል። ለዚህም ብዙ የሞራል ፍልስፍና ጥያቄዎችን ያስነሳል። ግለሰቡ በፍቃዱ ለሚያደርጋቸው ድርጊቶች ተጠያቂም፣ተሸላሚም ነው።እስኪ ፈላስፎች አልቱሪዝምን ከሞራል ፍልስፍና አንፃር እንዴት እንደሚመለከቱት እንይ…የፕሮታጎረስ “Man is the measure of all thing” የሚለውን እሳቤ የሚቃወመው ፕሌቶ ትክክል ወይም ስህተት ከሰው ሚዛን ውጪ ራሳቸውን ችለው ያሉ ነገሮች እንደሆኑ ያምናል። “virtue is ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 21
knowledge” በማለት የሞራል ልዕልና ከሰዎች የእውቀት ደረጃ ጋር ያገናኘዋል። ሰዎች ጥሩ ወይንም መጥፎ የሚሆኑት ባላቸው እውቀት ልክ ነው የሚል እሳቤ አለው። The Republic በተሰኘው መፅሐፉ ላይ “just life is better than unjust life” ይላል። መልካም የሆኑ ሰዎች ህይወት መልካም ካልሆኑ ሰዎች የተሻለ ነው እንደማለት። እዚሁ መፅሐፉ ላይ ሶቅራጠስን ሁለቱ ወንድማማቾቹን Glaucon እና Adeimantus ለመሆኑ መልካም ሰው እንዴት ያለ ነው? ብለው ይጠይቁታል። ማህበረሰቡ መልካም ለሚለው ሰው የሚሰጠውን ክብር ወይም ሽልማት ቢያነሳ፣ ለመጥፎውም ሰው ምንም ቅጣት ባይኖረው፣ እውን ያ ሰው መልካም ሰው መሆንን ይመርጥ ነበር? በተቃራኒው መልካም የተባለ ሰው በማህበረሰቡ እንደ አጭበርባሪ ቢቆጠር፣ ቢጠላ፣ ብዙ እንግልት ቢደርስበት? በተቃራኒው መጥፎ የሚባለው ሰው ደግሞ መጥፎ ነገሩን ደብቆ በማህበረሰቡ የተከበረ፣ የተወደደ ምስጉን ቢሆን። ታድያ እንዴት ነው የመልካም ሰው ህይወት መልካም ካልሆነው የተሻለ የሚሆነው ብለው ይጠይቁታል።Galucon “For the extreme of injustice is to seem to be just when one is not. So to the unjust man I must assign the most perfect injustice and not take it from him, but allow him while doing the greatest wrong to have secured for himself the greatest reputation for justice... Then let him be thus established in our argument, and now in his case let us set alongside him in our argu- ment the just man in his simplicity and nobility... the just man who is thought to be unjust will be scourged, racked, bound... and at last, after suffering every kind of evil, he will be impaled...”therefore “And when we have set them in this way, we can then judge which of the two is the happier.”ይህንንም ፕሌቶ ሲመልስ እውነተኛ ደስታ ከስጋ ሳይሆን ከነፍስ እንደሆነ ይገልጻል። ነፍስንም በ3 ይከፍላታል።፩. Reason፦ ይህ የነፍስ ክፍል ምክንያታዊ ሲሆን የግለሰቡ የመጠየቅ፣ የመመርመር እና የማወቅ ፍላጎት የሚመራው በዚህ በጠቢቡ የነፍስ ክፍል አማካኝነት ነው ይላል።፪. Sprit፦ አዛዡ ክፍል። ይህ የነፍስ ክፍል ሰዎች ስራዎችን ለመስራት፣ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 22
ድርጊቶችን ለመፈፀም የሚነቃቃው፣ ድልን፣ ክብርን፣ ኩራትን የሚፈልገው ክፍል ነው።፫. Appetites፦ ይህ በስጋዊ ፍላጎትን፣ በምቾት፣ በሀብት ፍላጎት የሚመራው ክፍል ነው በማለት ያብራራቸዋል። የሰው ልጅ እውነተኛ ደስታ የሚያገኘው ምክንያታዊ በሆነው የነፍስ ክፍል ሲመራ እንደሆነ በመግለፅ ይህ የነፍስ ክፍል ስጋዊ ፍላጎቶችን በማሟላትና እና ምቾት በማስጠቅ ደስታን ማግኘት እንደማይችል ያብራራል።እንደፕሌቶ ሀሳብ አንድ ሰው መልካም ስራን እስከሰራ ድረስ ምንም አይነት ስቃይ እና እንግልት ቢደርስበትም ከመጥፎው ሰው የተሻለ ህይወት እንደሚኖረው ይከራከራል። ስለዚህ ሰዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መልካም እና በጎ መሆን ይጠበቅባቸዋል የሚል ሀሳብ አለው።አንድ ምሳሌ እናንሳ የሆነ ሰሞን በሀገራችን ተከስቶ የነበረውን የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ተከትሎ የስራ አድማ ተካሄደ። እነዚህ የጤና ባለሞያዎች የሙያው ባለቤት ለመሆን ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ፣ ወደ ስራ ከተሰማሩም በኋላ ለአደጉበት ማህበረሰብ እሴት እና ለሙያ ስነምግባራቸው ተገዝተው ማህበረሰቡን የሚያገለግሉ ናቸው። ነገር ግን ብዙ የከፈሉበት እና ሙሉ ጊዜያቸውን የሰጡት ሙያ መልሶ የሚገባቸውን እየከፈላቸው አልነበረም። የሚያገኙት ገቢ ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድር አይደለም። እነዚህ ባለሞያዎች ለሰፊው ህዝብ ሲባል ከራሳቸውን አልፈው ቤተሰባቸውን ከፍለዋል። ለረዥም ጊዜ ቢያገለግሉም ከዚህ ቀደም በመልካም ግብራቸው የሚያገኙት የነበረው ክብር እና ትልቅ ቦታ በየጊዜው እየተሸረሸረ መጥቷል። በአንፃሩ በቀላሉ ጥቅም ለማግኘት አቋራጩን የሚጠቀሙ፣ ለማህበረሰብ እዚህ ግባ የማይባል አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሰዎች በኑሮም በክብርም ማህበረሰቡ ከፍ ያለ ቦታ ላይ አስቀምጧቸው መመልከት እየተለመደ መጥቷል። የጤና ባለሞያዎች እንደ ምሳሌ ተነሱ እንጂ መምህራኖችን፣ ደራሲዎችን ጨምሮ ለማህበረሰቡ ትልቅ አበርክቶ ያላቸው ሰዎች ማህበረሰብ የሚገባቸውን ቦታ አልተሰጣቸውም። ኑሮዋቸው ከእለት ወደ እለት አስቸጋሪ እየሆነ በመምጣቱ ለተወሰኑ ቀናቶች የስራ አድማ ሲያደርጉ ብዙ አስተያየቶች በጤና ባለሞያዎች ላይ መሰንዘር ጀመሩ።ህዝብ የጣለባቸውን ሀላፊነት ጥለው እንዴት እንዲህ አይነት ኢሞራላዊ ውሳኔ ይወስናሉ?ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 23
የእነሱ ክፍያቸው ከአገልግሎታቸው የሚያገኙት የነፍስ እርካታ ነው። የሚሉ ፕሌቶኒዝም እሳቤዎች መሰማት ጀመሩ።ግን እነዚህ የጤና ባለሞያዎች ኢሞራዊ ተግባር ነው እንዴ የፈፀሙት?የገዛ ቤተሰባቸውን አደጋ ውስጥ ጥለው ለህዝቡ ራሳቸውን አሳልፈው መስጠት የሚያስገድዳቸው የትኛው የሞራል ህግ ነው?ከላይ ያነሳነውን ዝግመተ ለውጣዊ አልቱሪዝም የሚካሄድባቸውን ምክንያቶች እያሰብን አንድ ግለሰብ ከተፈጥሮአዊ ባህሪው እና ከምክንያታዊነት ውጪ የሚፈፅመው መስዋዕትነት አግባብነቱን ለራሳችን እንጠይቅ። ይህን ጉዳይ ይዘን አርስቶትል ጋር ስንሄድአርስቶትል ለሞራል ፍልስፍናው መሰረት ሲያበጃጅ እንዲህ ይላል። የሰው ልጅ የመጨረሻው ግብ ምንድነው? ሲል ይጠይቃል። ገንዘብ?፣ ዝና?፣ ክብር? እያንዳንዱን ከፈተሸ በኋላ የሰው ልጅ ግብ እነዚህ ነገሮች ሳይሆኑ ‘’Eudaimonia’’ ደስታ ነው ይላል። ይህንንም ለመረዳት የሰው ልጅ ከሌላው የሚለየው ነገር ምንድነው የሚለየውን ማወቅ ያስፈልጋል ይላል። Nichomachean ethics መፅሐፉ ላይ እንዲህ ይላል።if we declare that the function of man is a certain form of life, and define that form of life as the exercise of the soul’s faculties and activities in association with rational principle, and say that the function of a good man is to perform these activities well and rightly, and if a function is well performed when it is performed in accordance with its own proper excellence... human good turns out to be activity of the soul in conformity with excellence.የሰው ልጅ ከሌሎች በምን ይለያል? ለሚለው ጥያቄ አርስቶትል በምክንያታዊነት የሚል ምላሽ ይሰጣል። ስለዚህ Eudaimonia የሰው ልጅ ድርጊቶቹን በምክንያት ሲመራ የሚፈጠር ነው።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 24
አርስቶትል ወርቃማው አማካይ (The Golden mean) የሚል ፅንሰ ሀሳበ አስተዋውቋል። ሁለት የምጣኔ ሀብት ጫፎችን እንደምሳሌ ያስቀምጥ እና ፅንሰ ሀሳቡን ያስረዳል። አንዱ ጫፍ ላይ መትረፍረፍ (Excess) መሀከሉን አማካይ (mean)፣ ሌላኛው እጥረት (Defi- ciency) ያስቀምጥ እና ሁለቱን የምጣኔ ጫፎች ጎጂ ሲላቸው፣ አማካዩን ስፍራ ወርቃማው አማካኝ ይለዋል። አማካኙ ለአርስቶትል ምክንያታዊ ውሳኔ አሰጣጥ ስለሆነ ደስታን ያመጣል ይላል። ከፕሌቶ በተለየ ደስተኝነት በልዕልና (virtue) ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን አካላዊ በረከቶች External Goods አስፈላጊ እንደሆነ ያምናል። አንድ ሰው መልካም ስለሆነ ብቻ ህይወቱ ምንም ያህል የተመሰቃቀለ እና በመከራ የተመላ ከሆነ ደስታን ማግኘት አይችልም ይላል። ለአርስቶትል የእነዚህ ባለሞያዎች የእጥረት ጫፍ ላይ በመቆማቸው ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ቤተሰባቸውን አደጋ ላይ ጥለው ማገልገላቸው ምክንያታዊ ተግባር ስላልሆነ ደስተኛ ሊያደርጋቸው አይችልም። ይህንን ሀሳብ የኢማኑኤል ካንት ዲኦንቶሎጂካል- Duty based ethics ጋር ይዘን ብንሄድ እንዲህ ይለናል።Morality is a matter of duty wether something is right or wrong doesn’t depend on its consequences. Actions are right or wrong in themselves.አንድን መልካም ተግባር የምንፈፅመው ውጤቱ ጥሩ ስለሆነ ወይም ጥሩ ስሜት ስለሚፈጥርልን አልያም ደስተኛ ስለሚያደርገን ሳይሆን ግዴታ ማድረግ ስላለብን መሆን ይገባዋል ይላል።ለካንት፣ እውነተኛ የሞራል እርምጃ ከስሜቶች፣ ዝንባሌዎች ወይም ከተፈለገው ውጤት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በምትኩ ለሞራላዊ ግዴታ እና ከድርጊቱ በስተጀርባ ስላለው ምክንያታዊ መርህ ነው። አንድን ተግባር ጥሩ ወይም መጥፎ የሚያደርገው ውጤቱ ሳይሆን በራሱ መጥፎ ወይም ጥሩ ስለሆነ ነው። አንድ ሰው በመንገድ ላይ ሲሄድ ላገኘው የኔ ቢጤ ሀዘኔታ ተሰምቶት ምን አልባት ሰው ስለሆነ አልያም ዘመዱ፣ ጎረቤቱ ስለነበር አንዳች ነገር አነሳስቶት የሚያደርገው ምፅዋት ትክክለኛ የሞራል ዋጋ የለውም። ይልቅስ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 25
ምክንያታዊ መርህ ላይ ተመስርቶ ያንን ቢያደርግ ድርጊቱ ትክክለኛ ዋጋ ያገኛል።ከላይ ያየናቸው የፕሌቶ virtue ethics ሆነ የካንት Deontogical ethics ካለምንም ምላሽ የጤና ባለሞያውን መስዋዕትነት የሚጠይቁ ናቸው። አርስቶትል ከነሱ በተለየ ወርቃማውን አማካይ ይጠቁመናል።ራስን ዋጋ የሚያስከፍለውን የአልቱሪዝም እሳቤ እንደቅዱስ ተግባር የሚሰብኩትን የሞራል ፍልስፍና አብዝታ የምትፀየፈው አያን ራንድ አልቱሪዝም ሌሎችን ስለመርዳት ብቻ አይደለም። ሰው ለራሱ ጥቅም የመኖር መብት እንዳይኖረው፤ ለሌሎች ማገልገል የሕልውናው ብቸኛው ማረጋገጫ እንደሆነ፤ የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ ከፍተኛው የሞራል ግዴታው እንደሆነ የሚሰብክ እና በጎነቱ እና እሴቱ ሌሎችን በማገልገል የሚለካ የሥነ ምግባር መርህ ነው ትለዋለች።ለራንድ አልቱሪዝም የክፋት ተግባር ነው። ይህ አስተምህሮ በመሠረቱ አጥፊ እና ክፉ ነው። ምክንያቱም ግለሰቦችን ለሰነፎች እና ምክንያታዊ ላልሆኑት ብዙሀኑ መስዋዕት እንዲሆኑ ይጠይቃል። ይሄ ፍፁም ህይወትን የሚፃረር እና የግለሰብን ሉዐላዊነት የሚክድ መጥፎ ተግባር እንደሆነ ትገልፃለች።The Atlas shrugled ላይ ገፀባህሪዋ Jhon Galt ‘’ The altruist morality is the source of all human evil. ... I swear, by my life and my love of it, that I will never live for the sake of anoth- er man, nor ask another man to live for mine.” ይላል። በኋላም ይህን ሀሳብ the virtue of selfishness ላይ አስፋፍታ እና አብራርታ ፅፋዋለች።ራንድ ምክንያታዊ የራስን ጥቅም (Ratio- nal egoism) ትደግፋች።The virtue of selfishness ሰዎች ምክንያታዊነት ላይ ተመስርተው የራሳቸውን ሕይወት እና ደስታ እንደ ዋነኛ ግባቸው ሊያደርጉ እንደሚገባ ትከራከራለች።ምክንያታዊ ራስ ወዳድ ግለሰቦች ባሉበት ማህበረሰብ ውስጥ የሌሎችን አላስፈላጊ መስዋዕት አይጠብቁም። ራሳቸውን ምክንያታዊ ባልሆነ ጉዳይ ላይ ለመስዋዕትነት አያቀርቡም።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 26
በዋናነት ራንድ ሌሎችን መርዳት እና አልቱሪዝም መካከል ያለውን ልዩነት ለማብራራት ትሞክራለች።ለቤተሰብህ፣ ለጓደኛህ፣ ለምትወደው ሰው ዋጋ ስለሰጠህ የምትወደውን ሰው መርዳት የራስን ጥቅም የሚያሳይ ተግባር ነው። ደስታን ያመጣልሃል። ከሌሎች ጋር በፈቃደኝነት ለጋራ ጥቅም መተጋገዝ እና መተባበር ምክንያታዊ እና ራስ ወዳድነት ነው። ነገር ግን ከዛ ውጪ ያለ የራስን እሴት እና ዋጋ ወደ ጎን የሚገፋውን self sacrifices አብዝታ ትቃወመዋለች።ከላይ እንደምሳሌነት ያነሳነው የጤና ባለሞያዎች ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን አደጋ ላይ የሚጥል መስዋዕትነት፣ ዋስትና በሌለው ሁኔታ ውስጥ በሀይማኖት ስም፣ በብሄር ስም፣ በሀገር ስም በስሜት በመነዳት የገዛ ቤተሰብን ሜዳ ላይ በትኖ፣ የራስን ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ ለጦርነት ፊት መሰለፍ፣ ለራንድ መጥፎ እና በራስ ላይ የሚፈፀም ኢሞራላዊ ተግባር ነው። ከሌሎች ፈላስፎች በተለየ ራንድ ሞራላዊ ድርጊቶች ዋጋ የሚኖራቸው የግድ በዙሪያችን ስላሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ብቻችንን ብንሆን እንኳን ዋጋ አለው ብላ እንዳለው ትገልፃለች።እንደማጠቃለያ አልቱሪዝም የሰውን ልጅ ከሌላው እንስሳ የሚለየው ልዩ ባህሪው አይደለም። ይልቅስ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥለትን ጉዳይ መጠየቁ፣ መመርመሩ እና ለሚያደርጋቸው ድርጊቶች ምክንያታዊ መሆኑ ነው የሚለየው። ራንድም የምትቃመው ሌሎችን መርዳትን አይደለም። ግን ያንን የምናደርገው በምክንያት ይሁን፤ ምክንያታችን ደግሞ ራሳችን እንሁን ነው። ለገዛ ራሳችን፣ አላማችን፣ ዋጋችን ሞራላዊ እንሁን ነው የምትለው። በደመነፍዊ ራስ ወዳዱ ጂን የሚዘወረው አልቱሪዝም እንኳ ምክንያቱ ራሱና ራሱ ነው።ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 27
በእኔ የዘመን መንገድ ላይ ፍቅር ብቻውን ቆሞ አልታየም። መተማመን ከቃል ይልቅ በህግ አንቀፅ ታስሯል። ሰው የአፉን ወለምታ በመታከክ የነፋስ ፊርማ ውሉን እያፈረሰ ስግብግብነቱን አደርጅቷል። ዋሾነቱን እየሳበ መልካም ስብዕናዎቹን አፈራርሷል።በእኔ መንደር ሞቅ ያለ ሳቅ የሚስቁ ሰዎችን ሳይ እደነግጣለሁ። በሌላው የእምባ መስዋዕት የቆመ ሀውልት ይመስለኛል። ከስሩ ነብስና ስጋው በስቃይ ተላቆ የተጋደመ ሰው ይታየኛል። አንገቱን የደፋ ምስኪን መልኩ ያንፀባርቅብኛል። ልክ የሌላውን ጉስቁልና የእሳት ‘ራት አድርጎ ከበላ በኋላ የሰባ የደስታ ገላ . . .!ካለምንም ከልካይና እውነታ እንደበረድ በነፁ ቃላቶቻቸው አምሳለገነት የሆነች ዓለምን የሚስሉ ሰዎችን ሳደምጥ ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል። ከቃላቶቻቸው ጀርባ ደባ ይሸተኛል። በእብለት ተብለጥልጠው የትም በረጩት የሀሳብ ጠበል - ብርሃን ናፋቂ ምስኪን ልቦችን ለጭላንጭል ተስፋ ቢያጩ እንጂ ፈውሶ ማቆምን አያውቁበትም። እውነቱ የታወቀ ቀንም ጭላንጭል ተስፋው ወደ ጥልቁ ጨለማ፣ አንካሳ ልብም ወደ ቁጭት ዜማ መምዘግዘጋቸው አይቀርም። የነፋስ ፊርማ(ሰው ማነው?)ሲራክ ወንድሙባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 28
በሴራ የተመሰረቱ በጣዋዥ እጆቹ የሚወረውሩት ምንዳዎች ከእዝነታቸው ይልቅ የስላቅ ቀለማቸው ይደምቃል። ራሳቸውን ያሰሩበት መሠረት የአንድ ጎን አንጃን ያቀፈ ነው። (መርዝ እያጎረሰ ሳቅን ያፀደቀ የለም። በሞት ድግስ ላይ ሕይወት አልታደመም።)በእያንዳንዳችን የነፍስ መቅረዝ ላይ ከብርሐን ጋር ሲደንሱ የነበሩ ሻማዎች፣ ከማን ጋር በፍቅር ወድቀው እንደነበር የሚገባን አርግዘው ከሰነበቱ በኋላ ነው። ለጋ ቀንበጥ እድሜያቸውን ለደራሽ ጊዜ እያሰቡ መልካም ስብዕናዎቻቸውን በሕይወት የክረምት ጎርፍ ያስወሰዱ ነፍሶች፣ የነገ ሙላታቸው በምናልባት ተስፋ የታጠረ ነው።የዚህ ዘመን ወረርሽኝ ሰው ነው። ከሰውም ራሱን ያልሆነ፣ ለራሱ ያልታመነ ባካኝ ነፍስ ያለው ወልመካ. . . !ነጋ ስለው የሚመሽ . . . ወጣ ስለው የሚገባ! ከፉከራው ስር በፍርሃት ቆፈን የሚንዘፈዘፍ ሰንደቁን ይዞ የውሸት የኮራ የደራ . . . አሳዛኝ ግን ደግሞ ራሱን ጀግና አድርጎ የሚቆጥረው ሰው የዚህ ዘመን በሽታ ነው።ካልረጋ ጠባዩ ማዶ የአብሮ መኖር አጥሩን እየነቀለ እሳት የሚሞቅ! በአጉል ሽንገላው ታጥሮ ስለእውነተኝነት ካላወራሁ እሞታለሁ የሚል ነው።ገላው በክፋት ላብ ደክርቷል። አይደለም በኩሬ ውሃ በባህር ልፅዳ ቢል እንኳን ባህሩ ይቆሽሻል። ለዘመናት በፈጠረው ጦርነት የልጅ ልጆቹ ተሰውተዋል። ለእነሱ ሀውልት እያቆመ በሀውልታቸው ስር ለቀጣዩ የእልቂት ቁማር ካርታ መደበቅ ይዟል። ሰውን ስመለከት የዚህ ዘመን ሀይማኖትና የእምነት ሰበካ ያንስብኛል። ከዳርዊን ጋር ተሻርኬ እግዜርን ማሳጣት ያምረኛል። እስካሁንም አለማሳጣቴን እንጃ!ከኒቺ ጋር ተመሳጥሬ እግዜራችንን ፍለጋ ለአርባ ዓመታት ባህር ማቋረጥ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 29
ያሰኘኛል። እስካሁንም በልቤ መሀል ያለውን ባህር አለማቋረጤን እንጃ!ሰውና ልማዱ ገደል ነው። አይሞላም። ምናቡ በፈጠረው ዲበሰብ (ሰይጣን) እያታለለና እየሸወደ ለዘመን ዘመናት ምድርን በድሏል። ለተቃረኑት መቃብር ምሷል።እኔና ምናቤ መልካም ስብዕናዋን ለዘነጋች ዓለም ሁሌም በየምሽቱ ሻማ እንለኩሳለን። ለህሊና ፀሎት እንማልዳለን። የሞራል ከፍታዋን እንደ እቃቃ ኮተት የትም ጣጥላ አለሁ በማለቷ አንብተናል።ስግብግብነት፣ ራስን ማስቀደም፣ ተንኮልና ክፋትን ፍራቻ - እግራችን ጥጋት ፈልጓል።ሸታ ለምትከረፋዋ ዓለም ማቅ ለብሰናል። ደረት ልንደቃ፣ ሙሾ ልናወርድ አደባባይ እየፈለግን ነው። ልክ እንደዲዮጋን ፋኖስ ይዤ መዞር ያምረኛል። ነገር ግን ማንን ላገኝ እያልኩ እገረማለሁ። ባገኝስ ማን የተቀማ ጩኸቴን ሊመልስልኝ ስል አመነታለሁ።ጠርጣራነቴን በብብቴ ስለያዝኩ ቆጥ ላይ ሰቅለው አንሳ ውሰደው የሚሉኝ ሰዎች ያስኮርፉኛል። ከእኔ ጋር የመተዋወቂያ ወቅቱ ምን ያህል እንደሆነ ላላወቅኩት ስጦታ እጄን አንስቼና ወስጄ ጥርጣሬዬን መጣል አልፈልግም።ያኔ የተቅበዘበዘ ሆኜ ብቀር የሀሜት መጅ ይሰልቀኛል። በአስመስሎ አደሮች ከንፈር ላይ የዋለች ጅራፍ ታደቀኛለች።ልዘንልህ ተብላ የተላከች እንባ ከፈረሰኛ የወንዝ ሙላት ከብዳ ትወስደኛለች። ለእድል ምርጫ ተብላ በህፃናቶች መዳፍ ላይ እንደተቀመጠች በኋላም ወዴት እንደምትሄድ ተመትታ እንደተከፈለች ምራቅ አማራጬ ምንም ነው። ለግራው ባደላ ባዶ ለቀኝም ባደላ ባዶ ነኝ።(ስንፍና ባያውቀኝም ትጋት ባይክደኝም ብኩንነት ግን ዘመዴ ነህ ብሎ በሻከረ ከንፈሩ ለጋ ጉንጬን ሊስም አሰፍስፏል።)ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 30
ማነኝ ስል የጮህኩባቸው ኮረብታዎች መልስ አልሰጡኝም። ስቃዬን የነገርኳቸው ወፎች ጨለምተኛ ብለው ተሳልቀውብኛል። በሽሽት የተጠለልኩባቸው ዋሻዎቼ በሸረሪት ድር ኮስምነዋል። ብቻዬን ነኝ እፈራለሁ። ሞትን ሳይሆን ሰው ‘ሸሻለሁ።የግፍ ቀንበር የተጫነባቸው ዘመናት በቁጥር ስም ተተክተው ሲሸሹ እኔን ለማስታወስ አልወደዱም። ሁሉ ግራ በሆነበት በዚህ ዓለም ከማን ጋር ለመኖር ተፈጥሬ እዚህ እንደተጣልኩ አላውቅም። የጥያቄዬህን መልስ የሚፈታልህ እሱ እግዚአብሔር ነው ያሉኝ ሰዎች ለእግዚአብሔራቸው አለመታመናቸውን ባየሁ ጊዜ እግዚአብሄራቸውን ፈራሁ። ሳቅ ለብሼ ቀን ደግሼ የምታይበት ቀን እንደሩቅ ዘመድ ይናፍቀኛል። ከዛሬ ይልቅ በነገ መንጋት ፍርሃት አለብኝ። ከዚህ ማለዳ በላይ ነገ ማን እንደሚቀበለኝ ወዴት ሂድ እንደሚለኝ አላውቅም። ብቻዬን ነኝ እሸሻለሁ። ሞትን ሳይሆን ሰው እፈራለሁ። ምናልባት ዛሬ በፈጣሪ ስም የተጋለቡ ሰዎች፣ ነገ ብቻቸውን ሲቆሙ ዛሬ በገነት ናፍቆት ደግነት የተያዘች ዓለም ከሞራል እሳቤ ውጭ ሆና ስትታይ ምን እንደምትመስል ሳስብ ስጋት እንቅ ያደርገኛል። ከሰዋዊ አጉል ኩራትና ቅዠት ወጥቼ አይደለም አለምን ራሴን ታግዬ የምጥለው መች ነው ብዬ መጠየቅ ያምረኛል። ለዘመን ለጊዜ ጥያቄ ከመሆንና አንድ ራሴን መደበቂያ ከማጣት ባለፈ ማነኝ ብዬ መታዘብ ይቀናኛል።(ከአፀድ ዛፉ ስር የጮህኩት ጩኸት አልፀደቀም።)አቅሜ መጎርመሱን ያዩ ባለቅስ እንኳን እንደልጅነቴ ሁሉን እንደማላገኝ ገብቷቸዋል መሰለኝ እኔ ማልቀስ ስጀምር ሳቃቸው ካለበት እየሮጠ ይመጣል።(እፈራለሁ።)ጊዜ ቁጥር ነው አውቃለሁ። በለውጥ ሂሳብ ቢሰራም የቅርፅ መለዋወጥና ዙረት እንጂ ዓለም ያው ዓለም ነች። ሰውም ያው ሰው ነው። ከቅዠት እቅፍ ራሱን መንጭቆ ሊያወጣ ይቸግረዋል። ኖሬ ስለእሱ የተነገረኝን ሳስብና ኖሬ ሳየው ለየቅል ነው። እምነቱ ረክሶብኛል። እሴቴ ያለኝ ተረት ተረት ሆኖ ታዝቤያለሁ። በእግዜሩ ውስጥ ካለው ዝምታ የዘለለ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 31
ምንም ነገር እንደሌለ ታውቆኛል።(የመተማማን ጀምበር ጠልቃለች። ማንም ማንንም አምኖ ሊተኛ አይችልም።)ልማዱን ሲል ለመግደልና ለማጥፋት በእጁ ስለት በልቡ ደባ ይዟል። እነዚያ ወፎች ለአንድ ቀን ሰው ሆነው የኔን ኑሮ ቢታዘቡ በዘበቱብኝ ዘበት ንሰሀ ይገቡ ነበር። ዋሻዬን በትቢያ ሞልተው የተራቀቁብኝ ሸረሪቶች ዘመኔን ቢረዱት በራሳቸው ድር ገመድ ገምደው ራሳቸውን ከመስቀል አይመለሱም። ሰውን አለመፍራት ሌላ ተዓምር ይመስለኛል። የሰራቸው የነፋስ ፊርማዎች አፍታ አይቆዩም ዓይኔ እርግብግቢቱን ሳይፈታ ይፈርሳል። የዚህ ሁሉ ሰበብ ድህነት ነው እንዳልል ሀብት በሚባለው ኑሮ ውስጥ ከመሰብሰብ ባለፈና ውል የሌለው የምቾት ቀለበት ከመክበብ ውጪ ያኛው አለም ምን እንደሚሰጠን አይገባኝም። ሀብት ያላቸው ሀገራትና ግለሰቦች በረቀቀ መንገድ ሌላ የበላይነትን ለመቆናጠጥ የሚሰፍሩትን ሴራ ሳይ እሸበራለሁ። ከሁሉም በላይ ግን ለእኔ ትልቁ ጥያቄ “ሰው ማነው?” የሚለው ነው። ሰው ማነው?ጥቅምት 2018ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 32
ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ በአድዋ አውራጃ ማይ ምሻም በምትባል መንደር በሐምሌ 24, 1878 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው ሻለቃ ባይከዳኝ የ አፄ ዮሐንስ ባለመዋል ሲሆኑ ገብረሕይወት የ 3 ዓመት ልጅ ሳሉ ነበር በመተማው ጦርነት ከንጉሱ ጋር የተሰዉት። የንጉሱን ሞት ተከትሎ በትግራይ አካባቢ በነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የተነሳ ገብረሕይወት ከጥቂት ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በሰባት አመታቸው ወደ ኤርትራ ተሰደዱ።ከምጽዋ ትይዩ በሚገኘው የስዊድን ሚስዮን ውስጥም ተጠለሉ። አንድ ቀን የምፅዋን ወደብ ለመጎብኘት ከጓደኝዕቻቸው ጋር ተያይዘው ወጡ።በወደቡ መልህቁን ጥሎ ከቆመ መርከብ ውስጥ ገብተው ይጎበኙ ዘንድ የመርከቡ ካፒቴን ፈቃዱን ለገሳቸው። መርከቡን ውስጥ ለውስጥ ተዟዙረው ይጎበኙ በነበረበት ሰዓት ገብረህይወት መርከቡ የሚነሳበትን ሰዓት ጠብቀው ውስጥ ተደበቁ። ሩቅ ከተጓዙ በኋላም ጀርመናዊው የመርከቡ ካፒቴን ገብረህይወትን ከተደበቁበት አገኛቸው። ሩቅ ተጉዘው ነበር እና በጉዞው ከመቀጠል ውጪ አማራጭ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝአልነበራቸውም። የጉዞአቸው መዳረሻ ባይራታልዑልሰገድ አስማማውባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 34
ወደሆነችው ኦስትሪያም ተጓዙ። ኦስትሪያ በደረሱ ጊዜ የመርከቡ ካፒቴን ገብረህይወትን ለሀብታም ቤተሰብ በማደጎ ሰጣቸው። ገብረህይወት ከዚህ ቤተሰብ ከተቀላቀሉ በኋላ ጀርመንኛ ቋንቋ ተማሩ። በርሊን ዩኒቨርሲቲ ውስጥም የህክምና ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ ገብረህይወት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው መጡ። ገብረ ህይወት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ከመጡ በኋላ በ ደጃዝማች ይገዙ በሀብቴ አማካኝነት ንጉሥ ምኒልክ ዘንድ ቀርበው የአማርኛ ቋንቋን እንዲማሩ ሰው ተመደበላቸው። በዚህም አማርኛ ቋንቋን በደንብ የመማር ዕድል አግኝተዋል። ነጋድራስ ገብረሕይወት እ.አ.አ በ 1907 በደጃዝማች መሸሻ ወርቁ መሪነት ወደ ጀርመን የተጓዘው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድንን አጅበው ሄደዋል። አጼ ምኒሊክ በታመሙ ጊዜ የሐኪም ሽታይንኩለር ረዳት ሀኪም ሆነው አገልግለዋል። ራስ ተፈሪ (አፄ ኃይለሥላሴ) አልጋ ወራሽ ከሆኑ በኋላ ደግሞ የአዲስ አበባ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ኢኒስፔክተር ሆነው አገልግለዋል። በኋላም የድሬዳዋ ነጋድራስ ለመሆንም በቅተዋል። ሆኖም ብዙም ሳይቆዩ ሰኔ 24፣ 1911 ዓ.ም በ 33 ዓመታቸው አርፈዋል። ነጋድራስ ገብረህይወት ኢትዮጵያ በሰዓቱ የነበረችበትን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዎ ሁኔታ በማመዝዘን፣ ኢትዮጵያ ታድግ እና ራሷን በሚገባ ትችል ዘንድ ያግዛታል ብለው የሚያስቡትን በተለያየ ጊዜ በመጽሐፍት መልክ ጽፈው አበርክተዋል። የመጀመሪያው “አጤ ምኒልክ እና ኢትዮጵያ” ሲሰኝ፣ ሁለተኛው ደግሞ “መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር” ይሰኛል። ከ “ፋና ወጊ የለውጥ አቀንቃኞች በኢትዮጵያ፤ በሃያኛው መቶ ዓመት መባቻ” ከሚለው የፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ መጽሐፍ ከ74-77 ካለው ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ። ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 35
፨ ሁለት መንገድ ነው ያለው፤ ከላይ እና ከታች በኩል ሲመጣ። የምታዋስነው እሷ ነች። አብዛኛውን ጊዜ እግሬ የሚመራኝ በታችኛው ነው። መንገድ ቀይሬ ተመልሼ ከላይ እመጣለሁ... “አረንጓዴ ሰፈር” ይሉታል። እነሱ ባይሉት እንኳ እኔ እንደዚሁ ብዬ እሰይመው ነበር። ምክንያቱን አላውቀውም... ብቻ የአረንጓዴነት ድባብ አለው። ጀንበር ለመጥለቅ ካኮበኮበችበት ሰዓት አንስቶ የቦታው ግርማ ይነግሳል። የሚታየው ሁሉ ያሳሳል። በዚህ እና በዚያ በኩል በተቃራኒ አቅጣጫ ተሰልፈው የሚመጡት መኪናዎች፣ ቸርቹ ዙሪያ እስከ-ታች የፈሰሱት ትላልቅ ባህር-ዛፎች፣ ከባባድ ቦርሳቸውን አንግበው ዳገቱን እየተሳሳቁ የሚወጡ ተማሪዎች፣ ጀበና እና ሲኒ ደርድረው “ቡና ጠጡ” ሲሉ የነበሩ እናት ዕቃቸውን ሲሸክፉ፣ እዚያ ባህር-ዛፎቹ መኻል ሲጋራ ለኩሶ በሃሳብ የሔደው ወጣት፣ መኪናቸውን ጥግ አስይዘው ውስጡ የሚቅሙ ‘አራዳዎች’፣ ቀያቴው ሰማይ፣ ከየት እንደመጡ የማላውቀው ብዙ አሞራዎች የሰማዩን አንድ ክፍል ሲያጠቁሩ፣ እየገባች ያለች ፀሐይ ፊት ላይ ስታበራ፣ የሷን ቤት ከሩቅ እያሰቡ መጓጓት... እነዚህ ሁሉ የጀንበሯን መጥለቅ ጠብቀው የሚያባባ ስሜት ለመልቀቅ ሰፈሩ ላይ የታሰሩ ጌጦች ናቸው። ያለ ምንም ሥራ እና ቀጠሮ ከአረንጓዴ ሰፈር ጀምሮ ወደ’ሷ ቤት ያለውን ቁልቁለት መውረድ ለይል ከመሥገድ ይተካከላል።(“እዚህ ሰፈር ለቅሶ አለ” ከታች ወደ ላይ እየወጣን ነው።የዕምነት መንገድ [ከአደም በዳኔ እስከ ጽዮን ማርያም]ነቢል አዱኛባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 37
“አንቺ ደግሞ እንደ አሮጊት ለቅሶ ማነፍነፍ”“ያምሃል እንዴ? የጓደኛዬ አባት እኮ ነው ያረፈው”በባህር-ዛፎቹ ሰንጥቀን በኮብልስቶኑ ላይ እንሔዳለን። ደመቅ ያለ የቀረፋ ሽታ ናኝቷል። “በዚህ ሰዓት ማነው ሻይ የሚያፈላ?” ከውጭው የላቀ በምንሔድበት ውስጥ ይጨልማል። የቀረፋውን ሽታ የሚገዳደር ዳር-ዳር ላይ የቆሙ አጫሾች ጢስ አለ። “ግን አንቺ ትገቢያለሽ። እኔ ውጭ እጠብቅሻለሁ”“ምን ሆነሃል? አብረን ነው እንጂ የምንገባው”“አልገባም”“ለምን?”“በሰላም ቀን የምን ሞት መጥራት ነው”“በስመዓብ!” ታማትባለች። እንዲህ ስትሆን ከሰፈሩም የላቀ ታባባኛለች። በመናደድ እና በመሳቅ መኻል ላይ ስትኾን... ምንም ሳልላት ፊቷን ማየት ብቻ...“ሆሆ!”“ታምሪያለሽ”ፈገግ ትላለች። ጥርሷ ሳይታይ የላይኛው ከንፈሯን ከፍ ታደርጋለች። ‘ከየት ያመጣሁት ጠላቴ ነው እየሳቅሽ ግደዪው ያለሽ?’አልነግራትም ስትስቅ እንደምታምር... እንዲሁ ‘ታምሪያለሽ’ ብቻ እላታለሁ። ለቅሦ ያለችውን ረሳች ወይም ለኔ ብላ ተወች። የቱም ቢኾን ግድ የለኝም - አብራኝ መኾኗን ነው የምፈልገው። ወጣንወረድን፣ ዞርን-ተመለስን። ስለምን እያወራን እንደኾነም ግድ የለኝም - አብራኝ መኾኗን ነው የምፈልገው። “ይሄ ቦታ ምን እንደሚባል ታውቃለህ?”“ምንድነው የሚባለው?”“የሌቦች ቦታ እኮ ነው... አይደለም እንዲ ጨልሞ በቀን ራሱ አይምሩህም”እሷ ካለች ስለ መ’ማር አለ’መማር ምን ያገባኛል? ዘራፊ ቀርቶ ፈጣሪም ባይምረኝ ግድ የለኝ)ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 38
ከቤቷ ምናልባት ሃምሳ እርምጃ በኋላ መሥጂድ አለ። ያለምንም ሥራ እና ቀጠሮ (ውስጥ እየተሰገደ ቢኾን እንኳ ሳላስተውል) ገብቼ እቀመጣለሁ። በረንዳ ላይ ኾኜ የተነጠፈው አርቴፊሻል ሳር ላይ የደመቀች ፀሐይ እሞቃለሁ (ምኑ ጀብራሬ ነው ጠራራ የሚሞቀው?)። አስባታለሁ… ‘ቦታው ፀጥ ቢል፣ እሷ ድምጿን ከፍ አድርጋ ብታወራ እኮ እሰማታለሁ’ እላለሁ። አደምጣለሁ... ወደ ቤቷ መሔድ ግን አልችልም። ያው እዚያ ጋር እናቷ ከሰው ጋር ያወራሉ። ‘የታደሉ እናት!’ እላለሁ... አሁን ምን እያደረገች ነው? እያወራች? እያሰበች? ሥራ እየሰራች? ተኝታ? እየበላች? እየጠጣች? እየሳቀች?... ከቤቷ ጓሮ ባሉት እፅዋት እቀናለሁ። ተደስታ ስትስቅ የተፈናጠቁ ፈገግታዎቿን ሰብስበው ነው ያደጉት። ‘ሰዎች ሆይ! የሚስቅ ጎመን ብትበሉ አይግረማችሁ!’። (ስትለብሰው የምወደውን ልብስ ነው አድርጋ የመጣችው። እንደምወደው ግን አልነገርኳትም።“ቤት እኮ ሳልነግራቸው ነው የወጣሁት። ቶሎ እመለሳለሁ እሺ”የመውሊድ ቀን ከሚሸተን እጣን የበለጠ መሀዛዋ እሷ ሳትደርስ ደርሶኛል። “ሰው ያየኛል እኮ በዚህ በኩል ና”ከመሥጂዱ ጀርባ ሔድን። መግሪብ እየተሰገደ ነው። አንገቴ ጋር ለመድረስ በመጠኑ ተንጠራርታ ስታቅፈኝ ታሳሳለች።“አረፈድኩብህ?”“አዎ” እላታለሁ ለአመል። የጠበቅዃት ሰዓታት በጠረኗ ከተሻረ፣ በድምጿ ከተፋቀ ቆየ። አሰጋጁ በተመስጦ እየቀራ ነው። ከጌታ ቃል በላይ ጣፋጭ ከንፈር አላየምና!)ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 39
ይህኛው መንገድ የመጀመሪያውን አይሽርም እንዲል አዳም ረታ... እኩያ ናቸው መንገዶቹ፤ የሚበልጥ የለም። ይህኛው ከበሬታ የሚያስቸረው ከጀንበር መጥለቅ ጋር ተያይዞ ነው። ቢሆንም ፥ የሁለቱም ንግሥና በጋ ሲኾን እንጂ በክረምት አይደለም (በዝናብ ከቤት ባይወጡ ይመከራል)። ከቀይ የፈዘዘ ሸሚዝ ከጥቁር ሱሪ ጋር አድርጌያለሁ። ለ ‘እመጣለሁ’ ሰዓቷ ጥቂት ደቂቃዎች ይቀራሉ። ከዋናው መንገድ ጀርባ በ ‘አሮጌው አስፓልት’ ነው ቀጠሯችን። እየናፈቅዃት እጠብቃታለሁ። ከስፋት ማነስ በስተቀር ‘አሮጌ’ነቱ የማይታይ መንገድ ላይ እመላለሳለሁ። ሰዓት ማየት አልፈልግም። አንድም-ሁለትም ደቂቃ ካረፈደች ቀረች ብዬ መጨነቅ ነው የሚኾነው። እያየሁት ልብ ብዬ ስለማላነበው ሥሙን ከማላስታውሰው ባር ጮህ ያለ ዘፈን አለ። ‘ጀንበር ወደ ዓለም አጎንብሳየዓይንሽን ብሌን ዕንባ ለብሳ’ እያለ ነው ቴዲ አፍሮ። (በዚሁ መንገድ... የመብራት መጥፋት፣ ከጀንበር መግባት ጋር ኾኖ ‘ዓዚም’ (ከመ ዓረብኛ - ታላቅ) ማታ ውስጥ ከጓደኛዋ ጋ ኾነው... በነጠላ ተሸፍነው ሲመጡ ዐያቸዋለሁ። በየ-ቦታው የፀሐይ መጥለቅን የቀባ የመሰለ ቀያቴ ብርሃን ተደምሯል።“የት እየሔዳችሁ ነው?”“ደመራ ነዋ”ደስ ብሏታል። ወደ ልቧ ማረፊያ እየሔደች ነው።“የት?”“እዚህ ጺዮን ማርያም” )ቶሎ-ቶሎ እየተራመደች ደረሰች። ሙቅ እጇን አልቧታል። በነጠላ የተሸፈነ ፊቷ ያበራል። ‘ሰላም ለኪ’ ልላት ዳዳኝ። “ቤተ-ክርስትያን እኮ ትምሕርት አለኝ። ካንተ ጋር ልቆይና አርፍጄ እገባለሁ”ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 40
የሚያባርረን ያለ ይመስል በፍጥነት ነው የምንራመደው። መልሼ የማላስታውሳቸው ውስጥ-ለውስጦች ታጠፍን። ስለምን እንደምናወራ አላውቅም። እግራችን መርቶን ጺዮን ማርያም ፊት-ለፊት ተጋጠምን። ከዚህ ጋር፣ በዚህ አየር፣ ከሷ ጋር፣ በዚህ ሰዓት ሲታይ ግርማው የአንበሳ ነው። ዝም ብሎ ተቀምጦ ማየቱ ብቻ ያፀድቃል። ሌላ መታጠፊያ ቀይረን ተራመድን -- ተራመድን።“ደከመኝ” አለች። መንገድ ዳር ተቀመጥን። ላስያዘ በየአምስት ደቂቃው የሚያልፍ ሰው አለ። ብቻችንን ነን። መሀዛዋ ‘ጺዮን ማርያም አንቺ ነሽ!’ የሚያስብል ነው (ከዚያ በኋላ ታጥቦ እንኳ ለአሥራ ስምንት ቀን ያልለቀቀ ጠረን አትማበታለች)።“ይቀዘቅዛል” አለች ከተቀመጠችበት እየተነሳች።“እኔ ላይ ቁጭ በይ”ከደጀ-ሰላሙ የሚመለሱ ምዕመናን ያልደረሱበት የዕምነት ጫፍ አሳለፍኹ። እኔ ላይ ስትቀመጥ አንድ እግሯን አንስታ ሌላኛው እስክታስከትል ያለውን ስሜት ታዝበዋል?ከሽንሽን ሥር የውስጥ ሱሪ ብቻ የለበሰ ሙቅ ታፋ ነክተዋል?ከበሮ አስይዞ የሚያስሸበሽብ ጠረን ምገዋል?የፓንቷን ጠርዝ መንካት ምን እንደሚመስል ዐይተዋል?ከርቤ የሚወጣው ከንፈር ስመዋል?ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 41
ወለል ባለ ሰማይ...ንቡ እንደ ደመና ሲያረብ በደስታ፤የማር ዝናብ መታኝ እንደገባሁ ላስታ፤እንኳን አዛውንቱ፥ሽበታሙ ድንጋይ መንኩሶ መንኩሶ፤አለቱ ግንባሩን፥የመስቀል ምልክት ተነቅሶ ተነቅሶ፤አይኔ አለሙን አየ እግሬ ሮሐ ደርሶ፤አወይ ደብረ ሮሐ እጄ ወርቅ ቅዱስእግረ ወርቅ ንጉስእፁብ ሩጫውን ሩጦ ጨርሶ፥ይዞ ክብረወሰን የቃል መወድሱን፤ጊዜ እንኳን ሩጦ አልቀደመም እሱን፤ደግሞ አየሁኝ ተዓምር፤ደብረ ሮሐሲልአምላክ አሰፋባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 43
አስነጥሶ እሚያስምር፤ከአሸተን ብልባላ እስከ ሰባት ወይራ፤ቁልቁል አቀበቱ የአማኝ እሙን ስራ፤የሚቀመስ አፈር የሚሳም ተራራ፤አሻግሮ የሚያይ ሰው የጎፈሬ ድምድም፤ተሸግራ እምትታይ፥ውብ የፅሀይ ግባት ቀይ የሰማይ ግልድም፤ይሄንን እያየ፥የቅዝበት ወዠቦ ዘመኑን ቢያርድም፤ላስቴ ስጋው እንጅ ነፍሱ አትበረድም፤በበአል በአዘቦቱ፤ልክ እንደ ታቦቱ፤ፀያይም ህፃናት ጎንበስ ብሎ መሳም፤አወይ ደብረ ሮሐ ይሄም አይረሳም፤“ሶለላይ መገናይ “ የምትል ልጅ ውበት፤ጨዋ ጨዋታዋ መንፈሴን ናኘበት፤እንደ መሶበ ወርቅ እንደ ኬርወርና፤እንደ ቅድስት ህዝባ እንደ መስቀል ክብራ፤ታንግሰኝ በልቧ ፍቅሯ መንገድ ይምራኝ፤አለት ነፍስያየን ስቀርፅ እንድገራኝ !!
ሰሎሞን ዴሬሳ በልጅነት የግጥም መድብሉ መግቢያ ላይ (እሱ እሽቅድምድም ብሎ የሰየመው) “አንዳንድ ጥያቄ አለ ፥ አስሬ ተጠይቆ፣ አስሬ መልስ አግኝቶ፣ ዳግመኛ አስሬ የሚጠየቅ። ከየት መጣን? ለምንስ መጣን? ወዴት እንሄዳለን? ለምንስ እንሄዳለን?” ሲል ይጀምራል። እኔ ደግሞ እላለሁ አንዳንዱ ጥያቄማ መቼ በአስር ጊዜስ ያበቃል። ሚሊዮናት ጊዜ ተጠይቆም መልስ ባገኘ በጄ ነበር። ግን ይኸው እንደአዲስ ስንጠይቀው እንውላለን እንጂ ይሄ ነው የሚባል አስማሚ ነገር የተገኘ አይመስልም።በርግጥ “አይ የለም! የለም! አስሬም የሚያደርስ ነገር የለም። ከየት መጣን? ከዚህ(----) ለምንስ መጣን? ለዚህ(----) ወዴት እንሄዳለን? ወዲያ(----)” ብሎ ወደቀረው የህይወት ጉዳይ የሚጣደፈውም ብዙ ነው። አንድም የምር ጥያቄው ቀሎኛል ብሎ አስቦ፣ አንድም ደግሞ ጥያቄው ሲያሰለቸው፣ በችኮላ ለማረፍ ካለ ጉጉት። ዛሬ ስለነገረ ሃይማኖት ላነሳሳ ስለሆነ ነው በዚህ መልኩ መንደርደሬ። ሃይማኖቶች ከላይ ለተነሱት ጥያቄዎች በየፊናቸው መልስ ሊሰጡ ይሞክራሉ። ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች መልስ የሚሉትን ደግሞ እውን መልስ ስለመሆኑ ለመገምገም ፍልስፍና የበኩሏን አስተዋፅኦ ታበረክታለች። እኔም የሃይማኖትን ጉዳይ ፍልስፍናን እንደመመልከቻ መነጽር በማድረግ ለማቅረብ እሞክራለሁ።የሃይማኖት ፍልስፍናሐብታሙ ውበት (ካሙ)ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 46
ወደዋናው ጉዳይ ከመግባታችን በፊት የሃይማኖት ፍልስፍና ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት። የሃይማኖት ፍልስፍና ከፍልስፍና ክፍሎች አንዱ ሲሆን፣ ጉዳዩም አንድን ሃይማኖት አጣጥሎ ሌላውን ከፍ ከፍ የማድረግ ሳይሆን በሃይማኖቶች ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሚዛናዊ ሆኖ የመመልከት፣ የመመርመር እንዲሁም የማጥራት ነው። ይህን ምርመራውም ከማመን እስከ አለማመን ድረስ ያሉትን ሃሳቦች ያካልላል። የሚያምነው ምን ይላል? ሲያምንስ የትኛውን ሃይማኖት እያለ ነው? ያ የተባለውስ ሃይማኖት ምን ይላል? ነው ወይስ በሃይማኖት ማዕቀፍ ሳይኮን ይታመናል? ደግሞ አለማመንስ እንዴት ያለ ነው? ምን ምን ጉዳዮች ወደ አለማመን ያቀርባሉ? እያለ በሁሉም አቅጣጫ የጥያቄ አረሮችን እየተኮሰ ማወያየት ነው አላማው - የሃይማኖት ፍልስፍና። ወይም በቀላሉ እንደሚከተለው ብናስቀምጠውም ገላጭ ይሆናል።“The branch of philosophy called the “philosophy of religion” is not necessarily concerned with either jus- tifying or disparaging any particular claims of any par- ticular religion. Rather, the interest of this aspect of philosophy is to examine the intellectual questions that arise in considering religious views. These questions are usually either special problems connected with the theory of knowledge as applied to religious knowl- edge, or metaphysical problems involved in efforts to construct a satisfactory and consistent explanation of certain concepts employed by various religions.” ¹ፍልስፍና እና ሃይማኖትፍልስፍና ከጥንት ጀምሮ ሃይማኖቶች የኔነው ብለው የያዙትን ሃሳብ ስትጠይቅ ኖራለች። ይህ የያዛችሁት ሃሳብ ትርጉሙ ምንድን ነው? እንዲህ ለማመናችሁ ማስረጃችሁስ ምንድን ምንድን ነው? ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 47
ያስተምሯችሁ ጥቅሙስ ምንድነው? እያለች ተከታታይ ጥያቄዎችን ታነሳለች። ምክንያቱ ደግሞ የነገሩን ውል ለመጨበጥ ካላት ቀናዒነት፤ አንድም ደግሞ ሁለንታውን በጋራ የሚገልጽ ፅንሰ ሃሳብ ለማዋለድ ከሚሻ ፅኑ ፍላጎት። ወይም በሌላ በኩል የፍልስፍናን ስነዘዴ ተጠቅመን የያዝነውን ሃይማኖት እናረጋግጥ ከሚል መሻት ነው። በተቃራኒው ጎራ ያሉት ኢ-አማንያንም ለአለማመናቸው የ “ለምን” ጥያቄ ሲወረወርባቸው፣ ፍልስፍናዊ ጥያቄዎቹን በማንሳት መፍትሄ ያሉቱንም በመጨበጥ አተያያቸውን ሲያስረዱ ኖረዋል። ከማመኑ ወይም ካለማመኑ ላልረገጡትም ማጠየቂያቸው ሆና አገልግላለች - ፍልስፍና።The problem of religious knowledge የተለያዩ ሃይማኖቶች ስለተፈጥሮ፣ እንዲሁም በውስጧ ስላለው የሰው ልጅም ሆነ ሌሎች አካላት የተለየና ጠቃሚ እውቀት አለን ይላሉ። ነገር ግን ይህ አለን የሚሉት እውቀት ከሃይማኖት ሃይማኖት የመለያየቱ ነገር ገለልተኛ ሆኖ ለሚመለከተው ታዛቢ ግርታን መፍጠሩ አልቀረም። ለታማኝነቱ የሚያቀርቡትም ማስረጃ እንዲሁ ይለያያል። እኒህን ልዩነቶች በደንብ የመረመረ ሰው የሃይማኖት እውቀት የመፈለጊያ ዘዴ ከሌሎች- እንደ ሳይንስ እና ከታሪክ ካሉት ዘርፎች ፍጹም የተለየ ስለመሆኑ ማሰቡ The problem of revelationብዙ ሃይማኖቶች አለኝ የሚሉት እዉቀት ከፈጣሪ በቀጥታ የተገለጠ እንደሆነ ይናገራሉ። አንድ ሰው ይህን እውቀት እንዴት የሰው ልጅ ሊያገኘው እንደሚችልና ምን ያህልስ እውነት ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን እንደሚቻል ቢጠይቅ፣ ተገለጠ በተባለውና እኛ ባለን መደበኛ እውቀት መሃል እጅግ ሰፊ ልዩነት እንዳለ ይረዳል። በመደበኛው እዉቀታችን ረገድ ስላሉት የሳይንስ፣ የታሪክ እና መሰል ጉዳዮች ጥያቄ ብንጠይቅ ስለነገሩ ሃቲት ለማቅርብ እንችላለን።ለሳይንስ እና ለታሪክ ምርምር የምንጠቀመውን ዘዴ ግን የመገለጥ እውቀት ለተባለው ማዋል አዳጋች ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው የትኛውንም አይነት የእውቀት ትወራ(theory) ቢይዝ ውሃ ከሁለት ሃይድሮጅንና ከአንድ ኦክስጅን ስለመሰራቱ እንዲሁም ጁሊዬስ ቄሳር ስለመገደሉ ያን ያህልም አይጠራጠርም፤ ወይም ቢያንስ እንዲያ የመሆን እድሉ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 48
በጣም ከፍተኛ ስለመሆኑ ይስማማል። እንዲህ ያለውን ስምምነት ግን የፈጣሪ ቃል ተገልጦልን ነው ወደሚሉ ሃይማኖቶች ብንወስደው በጣም አስቸጋሪ ብሎም ለመስማማት ከባድ ያደርገዋል።እሺ ልዩነታቸው ምንድን ነው? ያልን እንደሆነ ሳይንሳዊ ወይም ታሪካዊ መረጃዎች ላይ ከስር ከመሰረቱ ደርሶ መስማማት ባይቻል እንኳ የቀረቡትን ማስረጃዎች አይተን ነገሩ የመሆን ከፍተኛ እድል እንዳለው እንስማማለን። ለዚህም ሙከራዎች የተጠናከሩበትን ወረቀት፣ ያለፉ ሁነቶች የተመዘገቡበትን የታሪክ ማስረጃ እንዲሁም በህዝቡ ዘንድ ያለን ተጨባጭ ልምድ እንደግብዓት እንጠቀማለን። ይህን አይነቱን የማስረጃ አጠያየቅ በመገለጥ መጣ ወደተባለው መረጃ ስናመጣው ግን ማጣፊያው ያጥረናል። ለምሳሌ አንድ ሰው መጽሃፍ ቅዱስ እውን ሃይማኖታዊ መረጃዎችን ይዟል ወይ? ብሎ ቢጠይቅ ይህ ጥያቄ ሳይንሳዊም ሆነ ታሪካዊ ጥያቄ አይደለም። ታሪካዊ ጥያቄዎችን ስናነሳ የታሪክ ባለሙያዎች ታሪክን ለመፈተሻነት የተቀመጡ ደንቦችን (standards) ተከትለው ይመረምሩና ስለነገሩ ይነግሩናል። ሃይማኖታዊ ጥያቄ ሲሆንስ? በምን መመርመሪያ ዘዴ? የሚለው ጥያቄ መልስ አያገኝም።ከሁለት ወይም ሶስት ሚሊዬን አመት በፊት የነበረውን የፍልስጤም ታሪክ፣ የሶሎሞን ቤተመንግስት ያረፈበት ቦታን እንዲሁም ምን ይመስል እንደነበር ብንመረምርና ከዛሬው የታሪክ እውቀታችን ጋር የሰመረና የተጋጠመ ቢሆን ስንኳ መጽሃፍ ቅዱስ ሃይማኖታዊ መረጃን (እውቀትን) ይዟል ወይ የሚለው ጥያቄ ግን መልስ ሳያገኝ ይቀጥላል። ለዚህም ነው ሃይማኖትን ከመገለጥ (revelation) አንጻር ብቻ የሚቀበሉ አማኞች “እኛስ መቼ ሃይማኖት በአለማዊው የእውቀት ሃሰሳ መንገድ ይገለጣል አልን” የሚሉን። ይልቁንስ ሃይማኖት በእምነት እና በግል ቅምምሶች (physical experience) የሚገኝ ነው ይሉናል። ከአማኞች ወገን ሆነውም ሃይማኖት በrevelation ብቻ የሚያምኑበት እንዳልሆነም ለማስረዳት የተጉ ብዙ ፈላስፎችም ነበሩ። ቀጥለን የተወሰኑትን እንመለከታለን።Natural Relgion ተፈጥሮን በማስተዋል ሃይማኖትን በተጨባጭ ለማስረገጥ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች፣ ማስረጃዎች፣ እንዲሁም አመክንዮዎች አሉ ብሎ የሚሞግት ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 49
ዘርፍ ነው። ይህ ሲባል በመገለጥ የሚገኘውን ሃይማኖት ነቃፊ ሆነው አይደለም። እንዲያውም እርስ በእርስ የሚስማሙ፣ሚደጋገፉ አድርገው የሚያቀርቧቸው ትንሽ የሚባሉ አይደሉም።Natural Religion: The Argument from Design ለብዙ አመታት ተፈጥሯዊ ቅደምተከተልን በመከተልና በማጤን የሃይማኖት እውቀትን እናገኛለን (discover እናደርጋለን) ብለው ያመኑቱ ሁሉ የልዕለ ሃያል አካል መኖርን ለማረጋገጥ ቁጥራቸው የበዛ ማረጋገጫዎችን ለማቅረብ ሲሞክሩ ኖረዋል። ከነዚህም መካከል ከተፈጥሮ ንድፍ አንጻር (argument from design) የሚቀርበው መከራከሪያ ዝነኛው ነው። ይህንን መሞገቻ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በርካቶች እናውቀዋለን። እንዲሁ ዞር ዞር ብለን ተፈጥሮን እና እራሳችን አይተን ከሚፈጠርብን መገረም ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ የተፈጥሮን ውስብስብ ዝርዝሮች አርቅቆ ከማስተዋል ሊሆንም ይችላል። ዘመናዊ ሳይንስ በፍጥነት መመንደጉና ስለተፈጥሮ እና አካባቢያችን ያለን እዉቀት መጨመሩ ደግሞ የዚህ መከራከሪያ ሌላኛው በረከት ነው።Hume’s Argument (የሂዩም መከራከሪያ) CየNatural Relgion ሙግትን በማፍታታትና ሂስ በማድረግ ግንባር ቀደምት ከሆኑት መካከል ስኮትላንዳዊው ፈላስፋ ዴቪድ ሂዩም ይገኝበታል። Dialogue on Natural relgion ሲል ባቀረበው ዘመን ተሻጋሪ ስራው የሃሳብ ሃቲቱን በሰፊው ለማስቀመጥ ሞክሯል። ክሊንቴስ (Cleanthes) በተባለው ገጸባህሪው አማካኝነት ከተፈጥሮ ንድፍና አወቃቀር አንጻር (from design) የሚቀርቡትን ሃሳቦች አስኳል አስረድቷል፣ አወያይቷል፣ አሟግቷል እንዲሁም ሞግቷል።በርጋታ ብታስተውሉና ብትመረምሩ ሌላ ምንም አይደለም የምታገኙት፣ ይልቁንስ አንድ ትልቅ ማሽን እንጂ። ይህም ማሽን ተቆጥሮ ወደማያልቅ ትንንሽ ማሽኖች ይከፋፈላል። እኒህ ትንሾች ደግሞ በተራቸው ወደሌሎች እጅግ ትንንሾች እና እንዲሁም የሰው ልጅ እውቀት እና ስሜት ወደማይደርስባቸው ትንንሽ ማሽኖች ይከፋፈላሉ። ስለዚህ በመላ ተፈጥሮ ያለውን የምክንያትና የውጤት ትስስር በከፍተኛ ጥንቃቄ ያስተዋልን እንደሆነ ከሰው ልጅ ሃሳብ፣ እውቀት፣ ጥበብ እንዲሁም የነገሮች አነዳደፍ ብቃቱ ጋር እጅጉን ይመሳሰላል። ይህን ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 50