ምስስል (analogy) በመጠቀም ተፈጥሮን የደረሳት (author) የበላይ አካል በሆነ መንገድ ከሰው ልጅ አዕምሮ ጋር መመሳሰሉን ማስተዋል ይቻላል። እናም ይህን መከራከሪያ ብቻ በማየት እንደሰው ልጅ ሁሉ እዕምሮና የማሰብ ችሎታ ያለው አምላክ መኖሩን ማረጋገጥ ይቻላል።” ወይም እንደሚከተለው ቀጥታ የእሱን አፍ እንዋስ :Look around the world, contemplate the whole and every part of it: you will find it to be nothing but one great machine, subdivided into an infinite number of lesser machines, which again admit of subdivisions to a degree beyond what human senses and faculties can trace and explain. All these various machines, and even their most minute parts, are adjusted to each other with an accuracy which ravishes into admiration all men who have ever contemplated them. The curious adapting of means to ends, throughout all nature, resembles exactly, though it much exceeds, the productions of human contrivance—of human design, thought, wisdom and intelligence. Since therefore the effects resemble each other, we are led to infer, by all the rules of analogy, that the causes also resemble, and that the Author of nature is somewhat similar to the mind of man, though possessed of much larger faculties, proportioned to the grandeur of the work which he has executed. By this argument a posteriori, and by this argument alone, do we prove at once the existence of a Deity and his similarity to human mind and intelligence.²? ተፈጥሮን የበለጠ ባጠናንና በመረመርን ጊዜ እጅግ አስደናቂ የነገሮችን ቅንጅትና ህብረት እናስተውላለን። አሁንም የበለጠ በተጠጋን ቁጥር አዕምሯችንን ባንዳች መደነቅ የሚሞላ የነገሮች መጻመርን እናያለን። የተፈጥሮ ንድፏ ደግሞ የሰው ልጅ ለሆነ አላማ ከሚፈጥራቸው ልክ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 51
እንደ ቤት፣ ሰዓት፣ መኪና፣ መርከብ ወዘተ ጋር በጣም ይመሳሰላል። እንደ ሰዓትና ቤት የመሳሰሉትን ነግሮች የሚፈጥር አዕምሮ ደግሞ አለ። ስለዚህም ለተፈጥሮም እንዲሁ ፈጣሪ አላት። የሚል ነው የ natural relgion ዋና መሰረታዊ ጽንሰ ሃሰብ። በ natural relgion በኩል ይህ ይባል እንጂ መከራከሪያው ህጸጽ አለበት ከመባል አልዳነም ። ቀጣይ እሱ ላይ የተሰነዘሩ ሂሶችን እናያለን።የሂዩም (Hume) ሃሳብ ላይ የቀረበ ትችት ዲዛይን ላይ ተመስርቶ የሚቀርበው መከራከሪያ ላይ ከሚሰነዘርበት ትችት መካከል አንዱ የተፈጥሮ ዲዛይን ምክንያት (cause) ነው ስለተባለው ነገር ምንም ልምምዱ የለንም። ምን ማለት ነው? ይህ...ሰው ሰራሽ ለሆኑ ንድፎች ምክንያት የሚሆነውን አካል እናውቀዋለን። ይሁነኝ ብሎ ዲዛይን የሚያደርጋቸውን ቁሶች ሲሰራ በማየት ቀጥተኛ የሆነ ልምምድ አለን። ተጨባጭ ነው። በአስገኚ ተገኙ ስለተባሉት ተፈጥሯዊ ዲዛይኖች ምክንያት (cause) ግን ከግምት ውጪ ምንም የምናውቀው ልምድ የለንም። ስለዚህ ተፈጥሮን ያስገኘ እንደ ሰው አዕምሮ ያለው አካል አለ ማለት ከግምት የዘለለ አይሆንም የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሳል።ሂዩም በዛው መጽሃፉ (Dialogue on Natural Relgion) ላይ በተጠራጣሪው Philo በኩል የሚያቀርበው ትችት አለው። ይኸውም በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ ዲዛይኖች መካከል ስላለው ልዩነት ያለው ነው። የሰው ልጆች የሚሰሩት ዲዛይንና የተፈጥሮ ዲዛይን በበቂ ሁኔታ አይመሳሰሉም ። ስለዚህ ምክንያቱም ይመሳሰላል ማለት አንችልም የሚል ነው ። ያ ማለት የሰው ልጆች የሚፈጥሯቸው የዲዛይን ዉጤቶችን (ቁሶችን) አይተን የሚያስብ አዕምሮ ፈጠራቸው ስንል ለተፈጥሮ ግን ያን ማለት አንችልም እንደማለት ነው። ምክንያቱም ውጤቱ የተለያየ ነገርን አነጻጽረን ምክንያቱ አንድ አይነት የሚያስብ አዕምሮ ነው ማለት ከባድ ስለሚሆን። ወይም በ አመክንዮ ቋንቋ የቀረቡት ምስስሎች(analogies) እኩል ወይም ስም’ም አይደሉም ማለት ነው። በሂዩም(hume) መጽሃፍ philo ከ ክሊንቴስ (cleanባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 52
thes) ጋር ሲከራከር እንዲህ ይላል:If we see a house, Cleanthes, we conclude, with the greatest certainty, that it had an architect or builder because this is precisely that species of effect which we have experienced to proceed from that species of cause.But surely you will not affirm that the universe bears such a resemblance to a house that we can with the same certainty infer a similar cause, or that the analogy is here entire and perfect. The dissimilitude is so striking that the utmost you can here pretend to is a guess, a conjecture, a presumption concerning a similar cause. ³ሌላው ደግሞ፥ እሺ ለተፈጥሮ ምክንያት አለው ስንል ለምን ሰው መሰል አሳቢ ፈጣሪ አሰብን? እንስሶችም እኮ ውስብስብ ነገሮችን ያከናውናሉ- ስነ-ስርዓት እና ቅደም ተከተል ባለው መልኩ። ስለዚህ ለምን ያ ፈጣሪ ከእንስሶች መሃል አንዱን ሊሆን አይችልም? ወይም ደግሞ ህይዎት የሌላቸው ቁሶችም ድንቅ በሆነ መስተጋብር እርስ በእርስ አንዱ አንዱን cause እያደረገ ወይም እየፈጠረ ስለሚኖሩ የተፈጥሮ ደራሲ ነው የተባለው አካልም ለምን ቁስ ሊሆን አይችልም? እያለ ይቀጥላል ሂዩም። ይህን ሲል ሰውን አስበን ፈጣሪን እንዳሰብን ሁሉ ለምን ሌሎችንም አካላት እንደፈጣሪ አናስብም!? ምክንያቱም የምክንያት ና ውጤት (cause and effect) ተዋረድን ስንከተል ንፅፅሩ (analogy ው) ብዙ አማራጭ ስለሚኖሩት ነው።አይ ግድ የለም እንደ ሰው የሚያስብ ፈጣሪ አለ ብለን እናስብ። እሺ አስቦ ፈጠረ ማለትስ አለምን ፍጹም አድርጎ መፍጠር ማለት ነው ወይ? የሰው ልጅ ሲሰራ ከብዙ ስህተቶች በኋላ ነው የሚሳካለት። ይህ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 53
ማለት የሰው ልጅ ፍጹም አይደለም ማለት ነው። ንፅፅሩን ከተከተልን ደግሞ አምላክም ፍጹም አይደለም ማለት ሊሆን ነው። የአለም ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች ደግሞ ፈጣሪ ፍጹም ነው ይሉናል። ይኼስ እንዴት ይታረቅ?እንዲሁ ፍጹም ነው ብለን አጠጋግተን ብናስበው እንኳ አለሙን ዞር ዞር ብለን ስናይ ብዙ ጎደሎዎች ይታዩናል። አካላቸው ጎድሎ የሚወለዱ ህጻናት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ በዘር የሚወረሱ በሽታዎች፣ ብዙ ብዙ... ታዲያ ይህ ፍጹም የሆነ አካል ከmorality አንጻር እንዴት ነው የሚታይ? እኒህ ሁሉ መጥፎ ነገሮች ሲከሰቱ አምላክ ምንም አይሰማውም? ሃይማኖቶች ደግሞ ፍጹም አፍቃሪ ነው ብለውናል። አፍቃሪ ከሆነ እኒህ ሁሉ ሚዛን የጎደላቸው ነገሮች መኖር ነበረባቸው? እንዲህ እንዲህ እያለ የትችት ውርጅብኙን ይቀጥላል ዴቪድ ሂዩም። ዲዛይንን በመመርኮዝ ከቀረበው መከራከሪያ ቀጥሎ ሌሎች የአምላክን መኖር ያስረዳሉ የተባሉ መከራከሪያዎች በተለያዩ ፈላስፋዎች ቀርበዋል። ቀጥሎ እነሱን እንመለከታለን።Cosmological (or causal) Argument - የትዕይንተ ዓለም እንቅስቃሴ አመክንዮ ይህ መከራከሪያ ልክ ንድፍን (designን) መሰረት እንዳደረገው መከራከሪያ ሁሉ በተፈጥሮ ውስጥ በመኖር በተገኘ ልምድ ላይ የተመሰረተ ነው። ነግሮች ሲለወጡ ሲንቀሳቀሱ እናያለን ። እነዚህ ነገሮች እንዲለወጡ ወይም እንዲንቀሳቀሱ ደግሞ አንቀሳቃሽ የቀደመ ነገር ወይም ምክንያት መኖር አለበት። የቀደመውን ምክንያት ፍለጋ በሄድን ቁጥር ሌላ የቀደመ ነገር እያገኘን ልንቀጥል ነው። ወይም ደግሞ ይህ የምክንያት ተቀጣጣይነት የሆነ ቦታ ላይ ማቆም አለበት። ያ የምንቆምበት ነገር ደግሞ የነገሮች ሁሉ አስገኝ ምክንያት መሆን ይኖርበታል። ለዚህ የነገሮች ሁሉ ምክንያት ደግሞ ሌላ ምክንያት መጠየቅ የለበትም። ምክንያቱም የሆነ ቦታ ላይ ካልቆምንና የነገሮች ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 54
ጅማሮ ካልኖረ የነገሮችም ቀጣይነት አይኖርም። እናም ይህ ስለተፈጣሪነቱ የቀደመ ምክንያት የማይጠየቅበት አካል አምላክ ነው ይላል የትዕይንተ አለሙን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገው መከራከሪያ።አርስቶትል እና ቶማስ አኩዊያንስ የትዕይንተ አለም እንቅስቃሴን አመክንዮ በማራመድ በፊታውራሪነት የምናገኛቸው ቀደምት ፈላስፋዎች ናቸው። Summa theologica የሚለው የቶማስ አኩዊያንስ ስራ በሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዘንድ የእግዜርን ህልውና ማስረገጫ ተደርጎ ለረዥም ጊዜ አገልግሏል። ዴቪድ ሂዩም እና ኢማኑኤል ካንት በሃይል ከተቹት በኋላ ግን በተለይ ካቶሊክ ባልሆኑ አሳቢያን ዘንድ የተገፋ መከራከሪያ ሆኗል።የሂዩም ትችት - በትዕይንተ ዓለም እንቅስቃሴ አመክንዮ (cosmological argument) ላይ ሂዩም ትችቱን ሲጀምር እንዲህ ይላል “ነገሮች በምክንያት ቅደም ተከተል ነው የሚንቀሳቀሱት ወይም የሚመጡት ከተባለ ታዲያ ወደኋላ ሳናቆም በምክንያት ላይ ምክንያት እየደራረብን መሄዱ ምን ያስቸግራል ?!” ይለናል።In such a chain, too, or succession of objects, each part is caused by that which preceded it, and causes that which succeeds it. Where then is the difficulty? But the whole, you say, wants a cause. I answer that the uniting of these parts into a whole, like the uniting of several distinct countries into one kingdom, or several distinct members into one body, is performed merely by an arbitrary act of the mind, and has no influence on the nature of things.⁴ሂዩም ይላል ፥ ግድ የለም ይህ አመክንዮ (Causal argument) ልክ ነው ብለን ብናስብ እንኳ ያ የመጨረሻው ምንም ቀዳሚ የሌለው ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 55
ምክንያት ለምንድን ነው አምላክ መሆን ያለበት? አስጀማሪው ሌላ ቁስ ቢሆንስ? ያን ቁስስ ምን አስጀመረው?! ቢባል ሂዩም መልሱ አምላክ ያላችሁትንስ ማን አስጀመረው ይሆናል። አይ አምላክማ ምክንያት (cause) አያስፈልገውም ካላችሁ ሂዩምም መልሶ እንግዲያውስ ቁሱም ምክንያት አያስፈልገውም ይላችኋል።የኢማኑኤል ካንት የ causal argument ትችት ኢማኑኤል ካንትም ልክ እንደ ዴቪድ ሂዩም፣ በ Critique of Pure reason መጽሃፉ ብርቱ ትችቱን አስቀምጧል።የመጀመሪያው የካንት መከራከሪያ-¬ ለምን ምድር ላይ ያለ የነገሮችን ቅደም ተከተል አይተን የማይታይ ነገርን ለማብራራት እናውለዋለን? የሚል ነው። ነገሩን ሲያብራራው ፥ የነገሮች የምክንያትና የውጤት ትስስሮሽ ገለጻ የሚሰራው ለሚታየውና ለምንዳስሰው እንዲሁም ልምምዱ ላለን አለም ብቻ ነው እንጂ ለማናዉቀው ነገር አይሰራም ይላል።ሌላኛው የካንት ሃሳብ ደግሞ ፥ casual argument ን የሚያራምዱ ሰዎች የግድ አንድ ጀማሪ ምክንያት መኖር አለበት የሚሉት ነገር ከራሱ ከአመክንዮአዊ አስተሳሰብ ማዕቀፍ ውጭ መሆኑ ነው። ምክንያቱም ለሁነቶች መፈጠር ሌላ የቀደመ ምክንያት ያስፈልጋል ሲሉ ቆይተው የመጀመሪያው ላይ ለመድረስ ሲሉ ግን ራሳቸው ሲሉት የነበረውን የምክንያትና የዉጤት ትስስር ህግ ይሽራሉ። ይህ ለካንት ፍጹም ኢ- ምክንያታዊ ይሆንበታል። ሂዩምና ካንትን ጨምሮ ብዙ ፈላስፎች ይህ የምክንያትና የደንብ ውጤት ትስስርን ተከትሎ የመጣው መከራከሪያ የልዕለ ሃያል መኖርን አያስረዳም ሲሉ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 56
ይኮንናሉ። በመቀጠል ደግሞ የስነ ኑባሬን አመክንዮ እንዳስሳለን።የስነ-ኑባሬ (ontological) አመክንዮ የስነ-ኑባሬ አመክንዮ ከላይ ካየናቸው ሁሉ የተለየው ነው። ምክንያቱም ከላይ ያየናቸው ሁሉም የሚዋሱት አለም ላይ ያሉ ነገሮች ምልከታና ልምድን ሲሆን፣ ይኽኛው ግን ከልብ የሚመነጭና ከልምድ(-experience) የተነጠለ መሆኑ ነው። አለም ላይ ያሉንን እውቀቶችና ልምዶች አምላክን ለመፈለጊያ እንደማነጻጸሪያ አንጠቀምም። ይልቁንስ ኢ-ምንጨታዊ (inductive ) የሆነ ዘዴን ተጠቅመን እግዜርን/አምላክን እንፈልጋለን እንጂ። አንስሌም (St. Anslem) ፣ ሬኔ ዴካርት (Descartes) እና ባሩክ ስፒኖዛ (Spinoza) የስነ- ኑባሬን መከራከሪያ ለአምላክ ህልው መሆን እንደማስረጃ ይጠቀሙ የነበሩ እውቅ ፈላስፎች ናቸው።ለአንስሌም(St. Anslem) በአዕምሮ ሊታሰብ የሚችለው ትልቁ ነገር እግዜር/ አምላክ ነው። በአዕምሮ ሊታሰብ የቻለው ትልቁና ከሱ በላይ ሌላ ትልቅ ሊታሰብበት የማይችል ነገር እንደማለት ነው። ይህ የታሰበ አካል ደግሞ እውን ህልው መሆኑን St. Anslem ያምናል። ካመነ ደግሞ ለእሱ ያ አካል አለ ማለት ነው። ይሄም የስነ- ኑባሬ አመክንዮ (ontological argument) ይባላል።የስነ ኑባሬ አመክንዮ ላይ የቀረቡ ትችቶችSt. Anslemን ከተቃወሙት መሃል በዘመኑ የነበረው መነኩሴ Gaunilon ይጠቀሳል። መነኩሴው የስነ-ኑባሬን መከራከሪያ ሲተች እንዲህ ይላል “ እንደፍጹምና ታላቅ ነገር የታሰበ ሁሉ እውን መሆን ከቻለማ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 57
ሁሉም ፍጹም ተደርገው የታሰቡ ነገሮች ሁሉ እውን ሊሆኑ ነው። ለምሳሌ አንዲት ፍጹም የሆነችን ደሴት እናስብ። እንበልና ይቺ ደሴት ማንም አሳሽ (explorer) አይደርስባትም። በተጨማሪም ከሷ ውጭ ሌላ ፍጹም ደሴት ሊታሰብ አይችልም። ስለዚህ እንደ St. Anslem ከሆነ ያቺ ደሴት በእውን መኖር አለባት። ከሌለች ደግሞ ከሷ በላይ ፍጹም ነገር ሊታሰብ ይችላል ማለት ነው (ወይም እሷ ፍጹም አይደለችም እንደማለት)። ስለዚህ ፍጹምና ብቸኛ የሚለውን ሃሳብ ይዘን ደሴቷን እውን ልናደርጋት ነው ።” እንዲህ ያለው አስተሳሰብ ለ Gaunilon በጣም ከንቱና እርስ በእርስ የሚጣረስ ነው።Gaunilon pointed out that if this sort of reasoning were legitimate, one could also show that all kinds of unreal or imaginary objects must also exist.For example, if one could imagine that there is a perfect island somewhere beyond the point where any explorer could possibly go, it follows that if this island is perfect, or is that island than which none greater can be conceived, then, according to Anselm’s argument, the island must exist. If it did not, then it would not be perfect, or be that island than which none greater could be conceived. But since by definition it is perfect, and no greater island can be imagined, then from that concept alone, we can be sure that it must actually exist. By indicating that one could develop all sorts of ontological arguments about all sorts of ideas, Gaunilon sought to show that the argument contained elements that are ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 58
absurd and contradictory.5ቶማስ አኩዊናስ (Thomas Aquinas) ደግሞ አንስሌም(St. Anslem)ን ሲተቸው ፣ የ አንስሌም ችግር የእግዜርን መኖር ሳያስቀድም ባህሪውን ፍጹም አድርጎ ማሰቡ ነው ይላል። ስለአንድ ነገር ባህሪ ወይም ምንነት ከማወቃችን በፊት መኖሩን ማወቅ አለብን ይላል - አኩዊናስ። በርግጥ እሱም አማኝ ስለነበር እግዜር ፍጹም ነው መባሉ ከፍቶት አይደለም ይህን የሚለው። ይልቁንስ የእነ አንስሌም መከራከሪያ ደካማ ነው ብሎ ለመተቸትና የተሻለውን መከራከሪያ ወይም ማስረጃ ለመፈለግ ከመሻት እንጂ።የስነ- ኑባሬ አመክንዮን ካንትን ጨምሮ ሌሎችም ብዙ ፈላስፎች ዘርፈ ብዙ ትችት አቅርበዉበታል። ከዕለት ዕለት ልምምዳችንም የተነጠለ ስለሆነ እንደ አንድ ጽንሰ ሃሳብ መቀበል ይቸግረናል ሲሉ አለመስማማታቸውን ይገልጻሉ።በአጠቃላይ ጥንትም ዛሬም የአምላክን ህልውና እና ሃይማኖትን በአመክንዮ ማብራራት ይቻላል ብለው የሚያስቡ ሰዎች የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የሃይማኖት ጉዳይ በአመክንዮ የሚሆን ነገር አይደለም፤ ሃይማኖት እና አመክንዮ ፍጹም ሊታረቁ የሚችሉ ነገሮች አይደሉም የሚሉም በርካቶች ናቸው። በመቀጠል ደግሞ ኢ- አማኝነትን (Athesm) ፣ ዳኢዝም (deism) እና የመሳሰሉ ሃሳቦችን እንመልከት።ኢ - አማኝነት (Atheism) ኢ- አማኝነትን በቀላሉ ለመግለጽ ፥ ኢ- አማኝነት ማለት በአምላክ(-god or godess) መኖር አለማመን ማለት ነው። የተፈጥሯዊ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ እድገት ትልቅ እምርታን ማሳየቱን ተከትሎ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 59
ኢ- አማኞች ተፈጥሯዊውን አለም ለማብራራት ወይም ለማወቅ ምንም ልዕለ ሃያል አካል አያስፈልገንም ይላሉ። እዚህ ጋር ነገሩን እንደማባ’ያ ፒር ሲሞን ደ ላፕሌስ (Pierre-Simon de Laplace) ከናፖሊዮን (Napoleon) ጋር የነበረውን ጭውውት እንመልከት። Laplace ለናፖሊዮን አጽናፈ አለሙ ወይም ሁለንታው እንዴት እንደመጣ እያስረዳው ነበር። ናፖሊዮንም “እግዜርን የት ልታደርገው ነው በዚህ ሀተታህ ?” ብሎ ይጠይቃል። Laplace ይመልሳል “እሱ መላምት አያስፈልገኝም።” በአፉ ስናናግረው ፥ “I have no need of such a hypothesis.” ብሎ ይመልሳል። ሳይንስ ይበቃኛል ወይም በሱ መንገድ ብቻ ነው ተፈጥሮን መግለጽ የሚቻለው ብሎ ያሰበ ይመስላል።እንደ ፍሪድሪክ ኒቼ (Nietzsche) እና ሲግመንድ ፍሩድ (Freud) የመሳሰሉ አሳቢያን ደግሞ ሃይማኖት የሰው ልጅ ይፅናናበት ዘንድ የፈጠረው ነገር ነው ይላሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን እንዲሁም ሁለንታውን ሲመለከት የእንግዳነት እና የፍርሃት ስሜት ይሰማዋል። ስለዚህ አንዳች እረፍት የሚያደርግበት፣ ፍርሃቱን የሚያስወግድበት መጠለያ ሲፈልግ ሃይማኖትን አገኘ። በዚያም መሸገ ይላሉ የስነልቦና ባለሙያዎቹ።እንደ ኢፒኩረስና በርትራንድ ረስል ያሉ ፈላስፎች ደግሞ ሃይማኖተኞች አለ ያሉትንና ፍጹም የሁሉን ቻይነት፣ ሁሉቦታ ተገኝነት እንዲሁም ሁሉን አፍቃሪነት ባህሪ የሰጡትን አምላክ ሃሳብ በመመርመር እርስ በእርስ የሚቃረኑ ነገሮችን በመምዘዝ ብርቱ ትችታቸውን ያቀርባሉ። ለምሳሌ:- አምላክ ሁሉን አፍቃሪ እና ሩህሩህ ከሆነ ለምን የአለሙን ስቃይ እያየ ዝም ይላል? ርሃብ፣ወረርሽኝ፣ ጦርነት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ… ወዘተ. በሚንጣ’ት አለማችን ውስጥ የእግዜር ርህራሄና ፍቅር የቱ ጋር ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ። ስቃይን ማቆም ካልቻለ ደግሞ ሁሉን ቻይ አይደለም። ማቆም እየቻለ ደግሞ ዝም ካለ ፍጹም አፍቃሪ አይደለም። እያሉ ይተቻሉ። ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 60
Pantheism (ራሱን ሁለንታን እንደ አምላክ) ይሄ ነገር አልሸሹም ዞር አሉ እንጂ ሌላ አይደለም ኢ- አማኝነት ነው ብለው ከወደ አለማመኑ የሚመድቡት ብዙዎች ናቸው። የዚህ ሃሳብ(pantheism) አራማጆች ግን የተፈጥሮ ህግ ወይም እራሱ ሁለንታ አምላክ ነው ይላሉ። ፓንቴኢዝምን ከሚያራምዱት ፈላስፎች መካከል ባሩክ ስፒኖዛ በጣም ታዋቂው ነው። አልበርት አንስታይንም የሆነ ወቅት ላይ “በአምላክ መኖር ታምናለህ ወይ?” ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ “በስፒኖዛ አምላክ አምናለሁ ።” ሲል መልሷል።ዴዪዝም (Deism) አምላክ አለ ነገር ግን ሌሎች ሃይማኖቶች እንደሚሉት ከሰው ልጆች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የለውም። ሁለንታውን ፈጥሮ ትቶልናል የሚል ሃሳብ ነው - ዴዪዝም።አማኝነት (Theism) በአንድ አምላክ ወይም አማልክቶች መኖር ማመንን ይመለከታል ይሄኛው ደግሞ። እንዲሁ መኖሩን ማመን ብቻ ሳይሆን ይህ አምላክ ወይም አማልክቶች ከሰው ልጆች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለቸው ያምናል። ለምሳሌ ጸሎትን ሰምቶ እንደመመለስ ያለ አይነት ግንኙነት። ተአምራቶችም ሌላ አምላክ/ኮች ከሰው ጋር የሚገናኙባቸው መንገዶች ናቸው።ማጠቃለያበመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኹት ፍልስፍና ሃይማኖትን ስታጠና አንዱን ኮንና አንዱን ለማጽደቅ ሳይሆን ሃይማኖቶች የያዙትን ሃሳብ ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 61
ለመተንተን እና ለመመርመር ነው። ውግንናዋ ወደአንዱ እንዳልሆነ ይሰመርበት። በዚህ መጣጥፍ የአምላክ ሃልዎትን አስረጅ ተብለው የቀረቡትን መከራከሪያዎች እስከ ትችቶቻቸው እንዲሁም ስለ አምላክ መኖር አለመኖር የተቀመሩ ጽንሰ ሃሳቦችን ልክ እንደ አማኝነት (theism) ፣ዴዪዝም፣ ፓንቴኢዝም፣ ኤቲኢዝም (ኢ - አማኝነት) የመሳሰሉትን አብረን አይተናል። የሃይማኖት ፍልስፍና እጅግ ሰፊ የፍልስፍና አካል ነውና በዚህ መልኩ አጠር አጠር አድርገን ለማየት ሞክረናል። በዚሁ አበቃሁ።¹ Phlisophy MADE SIMPLE by Richard H.Popkin (Ph.D.),Avrum Stroll(Ph.D.) 1st edition 1969 ( page 140)² ዝኒ ከማሁ 144³ ዝኒ ከማሁ 146⁴ ዝኒ ከማሁ 1535 ዝኒ ከማሁ 157ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 62
ብርሃን ጨልጦ መስከር (የእሳቱ ሥላሶች)ብርሃን ጨልጦ መስከር (የእሳቱ ሥላሶች) በያዕቆብ ብርሃኑ የተደረሰች የመጣጥፎች ስብስብ ናት። መጽሐፏ ብሉያት እና ሐዲሳት በሚሉ ሁለት አበይት ክፍሎች ተከፍላለች። ከዚህ ቀደም “ከባዶ ላይ መዝገን” እና “በፍም እሳት ማቃመስ” ከተሰኙ መጽሐፎቹ ላይ ተመርጠው፣ እንዲሁም አዳዲስ ሌሎች መጣጥፎች ተጨምረውባት ለንባብ በቅታለች። መጽሐፏ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተጻፉ መጣጥፎችን አቅፋ ብትይዝም፣ ማዕከሏን የሰው ተፈጥሮ እና ሰብዓዊነት ላይ ታደርጋለች። ሰውነት እንደ ግለሰብ፣ እንደ ሀገር እና እንደ ዓለም (እንደ ሰው) ያለፈበት ውጣውረድ፣ ያሳካቸው ስኬቶቹ፣ የገጠሙት ፈተናዎች እንዲሁም የተጋረጠበት የህልውና ፈተና ከታሪክ፣ ከሚቶሎጂ፣ ከስነ ጽሑፍ፣ ከባህል እና ከፍልስፍና አንጻር ተዳስሷል። የህልውና ዕጣፈንታውን ስሙር ያደርግ ዘንድ ወደ ቀደመ ንጽህናው ይመለስ ዘንድ ጥቁምታዎች ተቀምጠዋል። ጥሪም ተደርጓል-የሰውን ልጅ ቀልቡን የማስታጠቅ ጥሪ። እነሆ ስለ ሰብዓዊነት፣ ስለ ሰው ልጅ ህልውና ፈተናዎች እና ህልውናችንን ማስጠበቂያ መፍትሄዎች ታነብቡ ዘንድ “ብርሃን ጨልጦ መስከር” ን ባይራ ለአንባቢዎቿ ትጋብዛለች። መልካም ንባብ።የመጽሐፍ ግብዣባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 7 ገጽ 63