51ፅናት የሰው ልጆች ላለመውደቅ ከጊዜና ከእጣቸው ጋር የሚያደርጉ ተጋድሎአቸው ነው።በሁነቶች ያልፀና ሰው መውደቂያው ቅርብ ነው። ማንም ይወድቃል።የሰው ልጅ ሆኖ የማይወድቅ የለም። ችግሩ መውደቁ ሳይሆን ወድቆ ለመነሳት ጥረት ያለማድረጉና ወድቆ መቅረቱ ነው።መማር ቀላል ነው።ከባዱ ተምሮ አለመለወጡ ነው።ሰፈራችን በዚህ የታደለች አይመስለኝም። የተማሩና በትምህርታቸው ተምረው ያልተለወጡ ብዙ አሉ።ለሌሎች ትምህርት የሚሰጡ እልፍ ከህይወት መንገዳቸው ወጥተው የወደቁ ወጣቶች አሉ። ለራስ ትምህርን መውሰድ ግን አልቻሉም።እኛ ሰፈር የዕውቀት ጠርዙ ተምሮ ወረቀት መያዝ ነው። በዚህች መንደር በመማር ችግር መፍታት አለማወቅ ነው። ዕውቀትን የምንለካው ከስምንት አሊያም ከአስር ትምህርት ጨርሰን በጫትና ሲጋራ መሃል ተወሽቀን በምንፈጥረው አልባሌ የወሬዎች ጥራትና ቅቡልነትን በመንዛት ነው።በዚህ መንደር ዕውቀት የወለደው የብርሃን ፊርማ አይታሰብም። ዕውቀት ገደብ የለው፣መንደርና አርማ የለው። በ’ኛ መንደር ግን ዕውቀታችን እርሾ አልባ ቡኮ፤ መንገድ የለሽ ጉዞ ሆኖ ሰው ሀሳቡን የሚያቀርበው በቋንቋው ቁምጣ ስር ተወሽቆ ነው።በዚህ የኤሊ ጉዞ ሰፈራችን መድረሻዋ ዛሬ ከሰዓት ነው ―ነገን ያለማየት። ይህንን ነው ጀብራሬው ሰካራም...የራስ መንገድ ጉዞየእውቀት ብርሃን ጮራን በራስ ውስጥ ገንዞ...ሲል ያሸሞረው።እናም ይህንን እውነታ ሳይ እታመማለሁ። የዚህችን ምስኪን ሀገር እጣ ፈንታ ሳስበው ምን ትሆን? እያልኩ ዛሬ ላይ የለበሰችውን ፀዓዳ የሀር ቀሚስ ተቧቅሰው ተቃምተው እጅጌዋን ላይ ሰፈር፣የወገቧ ላይ መቀነቷን ታችኛው ሰፈር፣ የተቀረውን ያው ልማደኛው የኛ ሰፈር ወስደውት የመጨረሻ ዕጣዋ ወልዶ መና መቅረት መሆኑን ሳስተውል ለምንስ አላዝን?!ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
52አዎ! በዚህች ምንዱብ ሰፈር አረቄ ጠጪዎች፣ ክፋት ቸርቻሪዎች፣ አዳፋ ለባሾች፣ መንገድ የለሽ ጉዞ ጀማሪዎች፣ በተናጠል ሳይሆን በወል ዘራፊዎች፣ ሀሳብ መንታፊዎች፣ ጊዜያቸውን አባክነው ጥቂት ምንዳ ከመንግስት ጠባቂዎች፣ በየመንገዱ ዳር ቁማር ቆማሪዎች፣ አዎ በዚህች መንደር ብዙ ምግባር ያላቸው ብዙ ሰዎች አሉ።ዘጠኝ ወር ተረግዞ አንድ ቀን ሳይደላው አርባ ዓመት ኖሮ በችጋር አለፈውሲል ልማደኛው ጀብራሬው ሰካራም... እኔም ከተከበብኩበት ተስፋ ፈላጭ ውሎ ቀስ ብዬ መፃፍ በማቆሜ ቀለም ማፍሰስ ያቆመች ብዕሬን አንስቼ የኋልዮሽ እየገረመምኳቸው አካባቢውን ጥዬ ሽቅብ ወጣሁ።አንዳንዴ ተስፋ ከሌለበት ጉዞ ተስፋ ያለበት መቆም ይሻላል። ኢትዮጵያ ሆይ ልጆችሽን ተቆጪያቸው....ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
53ለቁጭት እንባ እንኳን የሚሆን ሁነኛ ዘመኑን የተቀማው ትውልድ! ይጠይቃል!ዮዲት አማኑኤልቅጽ ፪ ቁጥር ፮ |ጥቅምት ፳፻፲፰
54ለቁጭት እንባ እንኳን የሚሆን ሁነኛ ዘመኑን የተቀማው ትውልድ! ይጠይቃል!“ጊዜ በሰው ህይወት ዘበት አይታክተውእኔም ምላሽ ባጣም መጠየቄን አልተውኩታ ገጠም ናቸው አልፋና ኦሜጋእንዴት ቀን ይመሻል በቅጡ ሳይነጋ?ማን ዘረፈው ጠጉሬን?ማን አሰረው እግሬን?ጉልበቴን ምን በላው? አቅሜን ማን ወረሰው?ተወልዶ ሳይጨርስእንዴት ያረጃል ሰው?”ብሎ ነበር አንዴ በእውቀቱ ስዩም ማለዳችን ላይ ተያይተን ሳንጨርስ ምኔው ማምሻው ላይ እንደተፋጠጥን ግራ ቢገባው ነው መሰል። የመወለዳችን ብስራት ተነግሮ ሳያልቅ እርጅና እድሜያችን ላይ ስናንዣብብ ብንታይ፣ ለመድከም እና እጅ ለመስጠት መጣደፋችንን ላየ፣ የቀትሯ ፀሀይ ወጥታ አናታችንን ሳትለበልበው ከምኔው ሙቀቷና ብርሀኗ ደብዝዞ ወደ ጉያዋ ስትሸሸግ ላስተዋለ እንደው ቀትር የሌለው ምሽት፣ ማደግ የሌለው መወለድ፣ ወጣትነት የሌለው እርጅና ምን ይሉት ነው ያስብላል።የሆነ ትውልድ አለ ተፋጅነቱት፣ ጠያቂነቱን፣ ሞካሪነቱን፣ ጉጉቱን፣ ውድቀቱትን፣ ቁጭቱን፣ ወጣትነቱን የተቀማ። ፋታ በሌለው ሁነት ከልጅነት ወደ እርጅና የተንደረደረ ምስኪን ትውልድ። ከመጠየቅ ከማወቅ ይልቅ በፍርሀት ተጠፍንጎ፣ በሁሉም ነገር የሚበረግግ፣ ዘመኑን ያልዋጀ፣ ወይ ከአባቶቹ ወይ ከመጪዎቹ መሆኑ ያልለየለት፣ የታናናሾቹ አመጣጥ ሲያስፈረጥጠው ለኩርኩም የተሰናዳ እጁን ከማወናጨፍ ወደ ኋላ የማይል፣ ደግሞም ዝም ጭጭ ያለ ድንጉጥ ትውልድ አለ። አንድ ሀገር አለች የሆነው ዘመን ወጣቶቿን ገና ማለዳዋ ላይ የቀበረች።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰ዮዲት አማኑኤል
55ደራሲ ጋሽ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር አንዴ “ወጣት መሆን ጥሩ ነው። ገንዘብ ባይኖርህ ጤና ይኖርሃል፣መልክ ባይኖርህ አንጎል ይኖርሃል፣ እውቀት ባይኖርህ ጉራ ይኖርሃል፣ ፍቅር ባይኖርህ ተስፋ ይኖርሃል፣ደስታ ባይኖርህ ንዴት ይኖርሃል፣ መጨቆን ቢበዛብህ ሬቮሉሽን ታስነሳለህ፣ መኖር ቢያስጠላህ ወይ ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ። ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሃል። ወጣት ነህና!” ብሏል ትኩሳት የተሰኘው መፅሀፉ ላይ።እውነትም አለም ላይ ከተከወኑ ስረ ነቀል የአስተሳሰብ ለውጦች፣ ርዕዮተዓለማዊ አመፆች በወጣቶች እንቅስቃሴ የተከወኑ እና የተመሩ ናቸው። እዚህ ላይ ግን ወጣትነትን ከእድሜ ወሰን ተሻግረን ባልደከመ መንፈስ፣ ራዕይን መሸከም በሚችል ጫንቃ፣ ለገድል ብቁ በሆነ የወጣትነት መንፈስ እየመሰልን እንዘልቃለን።ወጣትን እንደራዕይ ተሸካሚ እና ተጋዳሊ…በተለያዩ ጥንታዊ ሚቶች ለመንፈሳዊ አላማ የታጩ እና ለአለማዊ ግብር ራሳቸውን ያጩ ተጋዳላዮችም በዚህ የወጣትነት መንፈስ የተጠመቁ ናቸው።ቴዎድሮስ ገብሬ በይነዲሲፕሊናዊ የሥነፅሁፍ ንባብ በተሰኘው መፅሐፉ “ሚቶች ማህበረሰብ የወል ማንነቱን የሚገልፅባቸው እና የጋራ ራዕዩን የሚቀምርባቸው እንዲሁም እምነታዊ፣ እውቀታዊ እና ልቦናዊ ሁኔታዎችን የሚያንፀባርቅባቸው እንዲሁም በየዘመኑ የታዩ ለውጦችን መዝግቦ የሚቆይባቸው ሀይማኖታዊ፣ ፍልስፍናዊ፣ ኪናዊ... ሰነዶቹ ናቸው።” ይላል።በዚህም ፅሁፉ የተነገሩ ጥንታዊ እና አዳዲስ ሚቶች የሚጋሩትን አንድ ነገር አንስቷል።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
56የገድል ጥሪ (The call to adventure) “ይሄ ጥሪ ተጋዳሊውን ከአቋመ ማህበሩ የሚለይ፣ ወደ አዲስ እና እጅግ የተለየ ዓለም የሚመራ የማንቂያ፣የመቀስቀሻ ደወል ነው።” ይላል።ከዚህም በኋላ ግለሰቡ ከልጅነት ከፍ ወዳለ ብስለት ደረጃ ሲደርስ አካባቢውን ለመረዳት፣ ራሱን ለመፈተሽ፣ ማህበረሰቡን ለመመርመር ይነሳሳል። በዚህም የሰውን ልጅ የህይወት ትርጉም ከራሱ እና ከማህበረሰቡ አኗኗር ዘይቤ ጋር እያነፃፀረ መመዘን ይጀምራል። በዚህ ሂደት ነው በእሱ እና በማህበረሰቡ መሀከል ያለውን የእውቀት እና የግንዛቤ ልዩነት የሚረዳው።“ተጋዳሊው ከዚህ በኋላ ለውጥን አለመናፈቅ፣ ከወግና ከልማዱ አለማፈንገጥ፣ በማህበሩ የኑሮ ሥርዓቶች ላይ አለማመፅ አይቻለውም።” ይላል። በነባሩ ልማድና ስርአት ላይ ተመስርቶ የቆመው ማህበር ነባሩ አስተሳሰብ አዳዲስ ሀሳቦችን፣ ፍንገጣዎችን፣ ልዩነቶችን ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለማይሆን በዚህ መሀል ከግለሰቡ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ይገባል።ይሄ ሁሉ የሚሆነው ግን ግለሰቡ ጥሪውን የተቀበለ እንደሆነ ነው። የሰው ልጅ ሰብአዊ እና ማህበራዊ ህልውና እጅጉን ከሚት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ሁሉም ዘመን የእኔ የሚለውን ሚት እና ሚት ፈጣሪውን ይፈልጋል የሚለው ቴዎድሮስ የዴቪድ ሊሚንግን ሀሳብ በመዋስ ነባሩ ሚት ሀይማኖታዊ ተጋድሎ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን የዚህ ዘመን የሚት ልማድ የተመሰረተው ወይም እየተመሰረተ ያለው በሥነልቦና፣ በፊዚካዊ ሳይንስ፣ በኪነጥበብ እና በመሰል እውቀቶች እንደሆነ ይገልፃል። በነባሩና በአዲሱ ሚት መሀከል ያለውን ልዩነት ሲያነሳ የነባሩ ሚት ገድል ቀድሞ የተወሰነ እና የታወቀ ነው። ተጋዳሊው ከመወለዱ በፊት በልዕለ ሀያሉ የታጨ ነው። የአዲሱ ዘመን ሚት ግን እያንዳንዱ ግለሰብ በራሱ ጥረት ራሱን ለገድል የሚያበቃ እጩ ተጋዳሊ ነው። በነባሩ ሚት የሚታወቀው በዘመን ውስጥ አንድ ተጋዳሊ ይነሳል የሚለውን አስተሳሰብ የሻረ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ክስተቶችን አልበርት አንስታይን እና ሲግመንድ ፍሮይድን ያነሳቸዋል።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
57በአንድ ዘመን ውስጥ ነባሩን ፊሲካል ሳይንስ እና የስነልቦናውን ሳይንስ የነቀነቀ አዲስ አብዮት ያስነሱ እና ዘመኑን የዘወረ ሚት ያስተዋወቁ የአዲሱ ዘመን ተጋዳሊ ናቸው። ይላቸዋል።ባህሎቻችን ምንም እንኳን የቀደምት ተረኮቻችን ቅይጥ ቢሆኑም፣ በነባር እሴቶቻችን እርሾነት የተበጃጁ ቢሆኑም ነባሮቹ ተጋዳልያን ለአዲሱ ራዕይ ማደሪያነት አይበቁም። ከአዲሱ ሚት የሚወለደው እና አዲሱን ራዕይ የሚሸከመው ተጋዳሊ ከገዛ ራሱ ጋር ተፈላልጎ የተገናኘ፣ ዩንቨርሳዊ ቁርኝት (universal interrelatedness) መፍጠር ይጠበቅበታል።እዚህ ጋር አዲሱን ሚት ችላ ያለ የነባሩ ሚት ምርኮኛ ሥፍራ አይኖረውም። ይላል። የእነዚህ የሚቶች ተጋዳሊ ወይንም አለም በተለያዩ የጀብድ ስራቸው ጀግና የምትላቸው (heroic figures) ሌሚንግ የአዲሱ ሚቶሎጂ መሰረት ለሚላቸው የዘመናዊው ሳይንስ፣ ስነልቦና እና አዳዲስ እውቀቶች ጀርባውን የሰጠው ማህበረሰብ መሀል የዘመኔን ተጋዳሊ ካገፕው በሚል ሀሰሳዬን ጀመርኩ።ነገሩ “ሆዱ ፈሪ እግሩ ዳተኛ አዳም ሲዋጋ እርሱ ይተኛ” ሆነና፣ ያማተረው አይኔ አዲስ ነገር የማንፈልግ፣ ራሳችንን በእውቀት ከማሳደግ እና ከማሻሻል ይልቅ ከነበረው ነገር ጋር ሁሉ ካለ ምንም መጠይቅ የምንስማማ፤ የተሰጠንን ለምን፣ እንዴት ብለን ሳንጠይቅ አሜን ብለን የምንቀበል፤ ጭራሽ በምን ሁኔታ እንደተቀበልነው እንኳን ለማናውቀው አስተሳሰብ ጥብቅና የምንቆም፤ በዙሪያችን እየተካሄደ ላለው ነገር ባይተዋርነት የሚያጠቃን፤ ለአዳዲስ አስተሳሰቦች ደጃፋችንን በብረት መዝጊያ የቸከርን፤ ዘመናዊው አለም ራሷን ላበጃጀችበት አዲሱን ሚቶሎጂ ለመረዳት ሩቅ የሆንን ወጣቶችን አስተዋለ። መራቃችን አልነበረም ቁም ነገሩ፣ እየተጓዝንበት ያለው የአዲሱ ሚቶሎጂ ሀዲድ የት እንደሚያደርሰን ከመጠየቅ እና ከማስተዋል ይልቅ ከቅዥታችን ጋር ወደ ኋላ ለመጓዝ የወል ስምምነት ላይ መድረሳችን ያሳስባል። ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
58ዶክተር እጓለ ገ/ዮሀንስ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ ላይ አንድ ህዝብ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ለብዙ ዘመናት ብቻውን ተዘግቶ የኖረ ጊዜ ከገዛ መንፈሱ ከተገኙ የስልጣኔ ሀብታት ተደስቶ ረክቶ ሌላ መኖሩን ባለማወቅ የራሱን የመጨረሻ አድርጎ ይኖራል። ጊዜው ሲደርስ በስደተኞች፣ በነጋዴዎች፣ በተማሪዎች እና በሌሎችም አማካኝነት (ጊዜው እንዳሁኑ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና ማህበራዊ ሚዲያ ውጤቶች አለመጥለቅለቁን ልብ ይሏል) በሩ ይከፈትና አዲስ የስልጣኔ መንፈስ ይገባል። በመጀመሪያው ነገር ሰክረው የአዲሱ ነገር ጠበቃዎች ፈጥነው የሚሆኑ አሉ። ነገርን ሳያጤኑ፣ ሳያላምጡ እንዳገኙት መዋጥ የሚዳዳቸው እንዳሉ?ሲገልፁ። በሌላ በኩል ደግሞ እጣፈንታቸውን ከነባሩ ጋር በማጣመር አዲሱ እውቀት፣ ስልጣኔ እንዳይገባ በርትተው የሚጋፉ እንዳሉ ይናገራሉ። ነገር ግን ይሄ ከንቱ ልፋት ነው። ስልጣኔዎች በህሊና ልፋት የሚገኙ ስለሆኑ በየትም ቢወለዱ ዘመዳሞች ናቸው ይላሉ። እኛ ዛሬ ከራሳችን አልፈን ለእውቀት ጎራ ለይተን የምዕራብ ዕውቀት፣ የምስራቅ ምንለው እርባና ቢስ እንደሆነ ሲያመላክቱ። አያይዘው ለምህረትም ለመአትም የማይቸኩል አስተዋይ፣ አራቂ እስኪመጣ እንዲሁ በጠብ በክርክር ብቻ መካን የሚሆን ትውልድ፣ ከአንደኛው ወይም ከሌላኛው ሳይሳተፉ እንዲሁ የሚያልፉ ትውልዶች ይኖራሉ ብለዋል። ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
59እዚሁ ዘመን ላይ ሆነን ነገሩን ስናጤነው ለገዛ ነባራዊ እሴት እና ባህሉ ያለው እውቀት ውስን በሆነ እና ለማወቅም ለመርመርም ፍላጎት በሌለው እንዲሁም ለአዳዲስ እውቀቶችም ዝግ የሆነ ወጣት ትውልድ መሀል የሚፈጠረው ክፍተት እጓለ ከሚለው በሁለት የተለያዩ የስልጣኔ መንፈሶች መሀል ከተወጠሩት ትውልዶች በላይ ምን ያህል አስከፊ ሊሆን እንደሚችል ጥያቄ የሚፈጥር አይመስለኝም። እውቀት ጠል ትውልድ ወደኋላም ወደፊትም ይሄድ ዘንድ የማይችል እግረ ቆራጣ ተንፏቃቂ ነው። ትላንት በዚህ አልፌ ነበር ለማለት የሚያስችለውን ዳና ለማሳረፍ አይችልም።እንደው “ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል” እንዲሉ ወጣትነት ያለውን ሀይል፣ነገሮችን የማወቅ፣ የመጠየቅ ተነሳሽነቱ በማህበረሰቡ ልማዳዊ ድር ተተብትቦ ድፍረትና ሀይሉን ተቀምቶ፣ እንዲው በዘልማድ አኗኗር እንደዋለለ ጊዜውን በዋዛ ፈዛዛ ማሳለፉ ሀገር ለምታደርገው ጉዞ ዳገቱ ላይ ስትደርስ ተንገዳግዶ ለመውደቅ ቀጠሮ ከመያዝ ለይቼ አላየውም። ወጣት ለሀገር ትልቁ ሀይል አንቀሳቃሽ ሞተር ነው። ወጣት የሌላት ሀገር ደግሞ ድኩም፣ ጉዞዋ አዝጋሚ እና ለውድቀት የቀረበች ናት።ከግማሽ በላይ ህዝቧ የወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ ዜጎች አሉባት ተብላ በምትታሰብ ሀገር፣ የወጣቱ ሚና ተዛንቆ ሀገር ሚዟኗን ብታጣ ራሳችንን የምንፈትሽበት፣ የምንጠይቅበት፣ የምንቆዝምበት፣ የምንቆጭበት ዘመናችንን ማን ዘረፈን? ስንል እንጠይቃለን።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
60ወጣትን በእድሜ ወሰንፕሌቶ (Plato) The Republic ላይ ነፍስን በሶስት ክፍሎች sprit፣Aptite፣Reason ብሎ በመከፋፈል የማህበረሰብን ሚና በእነዚህ የነፍስ ክፍሎች ወክሎ አብራርቷል። እና ቀደምት ተፅእኖዎች የነፍስን ባህሪ የመቅረፅ አቅም እንዳላቸው በማሰብ ወጣቶች ስለሚነገራቸው ተረክ፣ ስለሚያደምጡት ሙዚቃ እና ማንኛውም ኪነጥበባዊ ውጤቶች ያሳስበው ነበር።ለፕሌቶ የወጣትነት ጊዜ sprit እና Apitite የሚላቸውን የነፍስ ክፍሎችን ለመቆጣጠር ምክንያትን (Reason) በጥንቃቄ መዳበር ያለበት የምስረታ ጊዜ ነው። ዝነኛው የዋሻው ምሳሌ (Allegory of the cave) ለወጣቶች የፍልስፍና ትምህርት ከድንቁርና (ጥላ) ወደ እውነት (ፀሐይ) የሚያደርጉበትን የሽግግር ጊዜን ያሳያል።ከዘመነ አብርሆት በኋላም ስለወጣቶች አብዮታዊ ሀሳብ ካነሱት ፈላስፎች ውስጥ ዣን ዣክ ሩሶ አንዱ ነው። ወጣቱ በተፈጥሮ መልካም ነው። ነገር ግን ከጊዜ በኋላ በማህበረሰቡ አስተሳሰብ የሚበከል “noble savage” ነው ሲል ተከራክሯል። ወጣቶችን ግትር በሆነ መንገድ መቅረጽ ሳይሆን ከማኅበረሰብ ልማዳዊ ምግባራት የሚከላከል እና የማወቅ ጉጉታቸውንና ምክንያታቸውን ከተቀረው ዓለም ጋር በተፈጥሯቸው እንዲያዳብሩ የሚያደርግ “ትምህርት” እንዲሰጥ ተሟግቷል። ወጣቶች ለሩሶ በማህበረሰቡ ተፅዕኖ ከመበከላቸው በፊት የተፈጥሮ ቅድስና ጠባቂዎች ናቸው።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
61ኢማኑኤል ካንት (Immanuel Kant) “Dare to know” ላቲነኛው (sapre aude) በሚለው ሞቶ ወጣቶች ያለ ሌሎች መመሪያ የራሳቸውን ምክንያት እንዲያዳብሩ እና የማህበረሰቡን ወግ፣ ልማድ የሚጠይቁበት ወኔውም ድፍረቱም እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርቧል።ከዚህ አንፃር ግለሰቦች ምክንያታዊ መስመር ላይ የሚመጡበት እና የወረሱትን ተለምዷዊ አስተሳሰብ ለመተቸት እና ለማሻሻል የሚጠቀሙበት ወቅት እንደሆነ ይገልፃል።በእርግጥ ኢማኑኤል እንደሚለው ልማዳዊ እኗኗርን፣ የማህበረሰብን እሴቶች እና ባህልን ከመፈተሽ እና ከመመርመር በፊት የሚኖሩበትን ማህበረሰብ ማንነት ማወቅ እና መረዳት ይቀድማል እና ምን ያህል ራሳችንን እናውቃለን? ወይንም ለማወቅ እንፈልጋለን? የሚለውን ጥያቄ ከላይ እንዳነሳሁት ራሳችን እንድንብሰለሰልበት ትቼው አልፋለሁ።የኅላዌነት ፍልስፍና (Existential philosophy) አቀንቃኞች የግለሰቡን ሥር ነቀል ነፃነት እና እሱን ተከትሎ በሚመጣው ሸክም እና የኃላፊነት ውጥረት ላይ ያተኩራሉ። ይህ ስሜት ብዙውን ጊዜ በወጣትነት ጊዜ የሚስተዋል ነው።ሶረን ኬርጋድ (Jean-Paul Sartre) ወጣትነትን “የጭንቀት” እና “ተስፋ መቁረጥ” ስሜት የሚስተናገድበት ጊዜ እንደሆነ ገልጿል። ከአሉታዊ መልኩ ባሻገር ጭንቀት የነፃነት እዳ እና ገደብ የለሽ እድሎችን ከማወቅ ጋር የሚመጣ ነው። ለኪርኬጋርድ የወጣትነት ተግባር ከ “ውበት” ደረጃ ወደ “ሥነ-ምግባራዊ” ደረጃ የሚሸጋገርበት እንዲሁም ማንነቱን በጋለ ስሜት የሚወስንበት እና በቁርጠኝነት ምርጫዎችን የሚያደርግበት ጊዜ እንደሆነ አስረድቷል።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
62“ከትርጉም በፊት ህልውና ይቀድማል” ሲል አጽንዖት የሚሰጠው ዣን ፖል ሳርተር ወደ አለም የተወረወርነው ያለቅድመ ዓላማ ነው እና በምርጫችን የራሳችንን ትርጉም መፍጠር አለብን ይላል። ይህ የነፃነት ክብደት በወጣትነት ውስጥ በጥልቀት ይሰማል፣ አንድ ሰው አስቀድሞ የተገለጹትን የልጅነት ሚናዎች ትቶ ራሱን የመፍጠር አስፈሪ እና አስደሳች ተግባር ይፈፅማል። ወጣትነት የሰው ልጅ ራሱን የሚገልጽበት እና ትክክለኛነትን የሚቀበልበት ወሳኝ ወቅት እንደሆነ ያብራራል።የ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፈላስፎች ወጣቶችን በባህል፣ በስልጣን እና በፖለቲካ ኢኮኖሚ መነፅር ይተነትኑ ነበር።ኸርበርት ማርከስ (Herbert Marcuse) የኢንዱስትሪው ማህበረሰብ አመፆችን ለማስወገድ እንዴት የውሸት ፍላጎቶችን እንደሚፈጥር እና የሸማቾችን ባህል እንዴት እንደሚጠቀም ተንትኗል። በ1960ዎቹ በተካሄደው የተማሪዎች ተቃውሞ የተሳበው ማርከስ በእነሱ ውስጥ “ታላቅ እምቢተኝነት” በማየቱ እና ወጣቶች ወላጆቻቸው ተስማምተው ያፀደቁትን ጨቋኝ ሥርዓት ለመቃወም እና እውነተኛ ነፃ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያስችል አቅም እነሱ ላይ በማየቱ ነበር። ወጣቶች ከዚህ አንፃር የአብዮታዊ ለውጥ ዋና ወኪል ናቸው ይላል።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
63ወጣትን እንደ ታላቅ አእምሯዊ ብቃትአሜሪካዊቷ ፈላስፋ አያን ራንድ ደግሞ ወጣትነት ላይ ልዩ እና ጥልቅ የሆነ አመለካከት ነበራት። ከባዮሎጂካል ደረጃ ባሻገር በሃሳብ፣ በራስ የመመራት እና የታላቅነት አእምሮአዊ ብቃት አድርጋ ትገልፀዋለች። የእርሷ አመለካከት በዋነኝነት በልብ ወለድዎቿ በተለይም “The Fountainhead” እና “Atlas Shrugged” ላይ ተገልጿል።ጥልቅ የጉጉት ስሜት፣ የአንድ ሰው ህይወት አስፈላጊነት/ የመኖር ፍላጎት፣ ግለሰብ ታላላቅ ስኬቶች የመቀዳጀት አቅም እንዳለው የሚሰሙን ስሜቶች ተፈጥሯዊ እና ትክክለኛ እንደሆኑ ታምናለች። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በህብረተሰብ ግፊቶች ተቀባይነት ለማግኘት ሲባል እና ከብዙሀኑ ጋር ለመመሳሰል በሚደረግ ጥረት እኒህ ስሜቶች እየደቀቁ ይመጣሉ።ራንድ The Fountainhead ውስጥ ከሳለችው የፍልስፍናዊ እሳቤዎቿ ተሸካሚ ሃዋርድ ሮርክ የተሰኘው ገፀባህሪ ይህንን መንፈስ ያቀፈ ነው።ይህ ገጸ-ባህሪ አቋሙን ለባሕላዊ ስርአቶች ለመሠዋት ፈቃደኛ አይደለም። በዚህም የወጣትነት አስተሳሰብን ወደ ጉልምስና የማስቀጠል ሃሳቧን አንፀባርቃለች። ህብረተሰቡ በተለይም በመንጋ ሀሳቡ እና በአሉታዊ ስነ-ምግባር የወጣትነትን መንፈስ ስልታዊ በሆነ መንገድ ያጠፋል ሲል ትከራከራለች። እንደ ኤልልስዎርዝ ቶሄ ያሉ ገፀ-ባህሪያት ደግሞ የማህበረሰብን አሉታዊ ተጽዕኖ ያመለክታሉ። የግል ምኞቶችን በማቃለል እና የራስን ጥቅም መስዋዕት ማድረግን እንደ ቅዱስ ተግባር የሚሰብከውን ልማድ፣ ወጣቶች ምክንያታዊነትን እና ግለሰባዊነትን እንዲቃወሙ የሚያስተምሩ የትምህርት እና የባህል ሥርዓቶችን ነቅፋለች።ዛሬ ሀገራችን ላይ የአዲሱ ሚት ራዕይ ተሸካሚ (ተጋዳሊ)- ራንድ የምትለው የወጣትነት መንፈስ- መቼ ተወልዶ መቼ ስርአተ ቀብሩን እንደፈፀመ እየጠየቅን ቆመናል።ወጣት የማወቅ ጉጉቱን፣ ምክንያታዊነትን፣ ጠያቂነትን፣ ለአላማ መቆምን፣ ቁርጠኝነትን፣ ከመንጋ አስተሳሰብ ነጠል ብሎ ብቻ ለመቆም የሚያስችል ድፍረት የመሳሰሉትን የወጣትነት መለያዎቹን ሊያጣቸው አይገባም። ሆኖም ግን መሆን ሚገባንን ትተን ለምን መገኘት የማይገባን ጎራ እንደቆምን ግር ቢለን እንዲህ ብለን እንጠይቃለን።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
64ወጣትነታችን በማን እና መቼ ተዘረፍን?ለሚሰማ...በእረፉ ብቻ በህግ አምላክ ሰበብ የዘመመ አጥር ከመገፋት ላይድን ደካማ ጎጆህን ከመፍረስ ላታስጥል አጥርህንም ጠበቅ ጎጆህንም ቀና ሀይልህን ሰብስበህ ምሽት ፅልመትህ ላይ ቀን እንድታበራዘመንህን ቃኝተህ መንገድህን አጥራ እንላለን።ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰
65ቅጽ ፪ ቁጥር ፰ |የካቲት ፳፻፲፰ባይራ ፡- ቃሉ ዶርዚኛ ሲሆን ትርጉሙም ታላቅ፣ ቀዳሚ፣ ፊተኛ ማለት ነው።ኑኒ ባይራክ!ታላላቆች ነን!ባይራ ዲጂታል መጽሔት Bayradigital @Bayradigitalwww.bayradigital.comበማሕበራዊ ሚድያ ይወዳጁን!ሃሣብ አስተያየትዎን ያጋሩን