ፓፒረ ዲጂታል መታነቂያ ወይስ ስ መታወቂያ? ባሕላዊ የመተጫጨት ሥነ ሥርዓት በብሔረ ዛጉዌ በብሌን ደምሴ ጆሮ ዳባ! ለባለቅኔ? በውብአረገ አድምጥ የግድ ጥብቅ ህግ አያስፈልገውም ቁጥር 1 ጥር፣2015 ዓ.ም በፀጋዓለም ዳኜ ራስን ማስዋብ
አሳታሚ ኢካሽ ፕሮሞሽን ዋና አዘጋጅ ውብአረገ አድምጥ አድራሻ ሃያ ሁለት ታውን ስኩየር ሞል 8ኛ ፎቅ የሳምንቱ ተሳታፊዎች ኅሊና እንዳለ መቅደላዊት አሰፋ ብሌን ደምሴ ሳባ መኩሪያ ውብአረገ አድምጥ ማሪኬቲንግ ሃላፊ ከቨር ኢሉስትሬሽንና ሌይአውት ዲዛይን አበበ አረጋ ርእስ አንቀጽ በሃይማኖት ምክንያት የሚመጣን መካረር መንግስት ቸል ሊለው አይገባም። በታሪክ እንደምናውቀው በሃይማኖቶች ምክንያት የሚመጣ ቅራኔም ይሁን ጸብ ማባሪያ የለውም። በዓለምም እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ጦርነቶችና ደም መፋሰሶች ተከስተዋል። የሚሊዮኖች ህይወትም ተቀጥፏል። ለነፍስ በሚል መሪ ቃልም እልፍ ነፍሶች ጠፍተዋል። በክርስትና አስተምህሮ ዘመነ ሰማዕታት ከሚባለው ዘመን ጀምሮ ሚሊዮኖች ረግፈዋል። ቆይቶም የመስቀል ጦርነት እየተባለ በሚታወቀው የሃይማኖቶች ጸብ ክቡሩ ሰው በብላሽ ተቀጥፏል። በሃገራችንም ተመሳሳይ የዘመን ክስተቶች ነበሩ። በዘመነ ዮዲት ጉዲት የደረሰው የሰውና የንብረት ውድመት ጥቁሩ የታሪካችን ክፍል ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ በሆነ ከ 500 ዐመታት በኋላ የግራኝ አህመድና የክርስቲያኑ መንግስት ለ 15 ዓመታት የማያባራ ጦርነት አድርገዋል። በክርስቲያን መንግስት ፖርቱጋልና በእስልምና መንግስት ቱርክ እየታገዙ የብዙዎችን ነፍስ ሲቀጥፉ ከርመዋል። በገንዘብ ሊተኩት የማይቻል ቅርስና ታሪክም ወድሟል። ይሄን ጦርነት ተከትሎ የክርስቲያኑን መንግስት እናግዛለን በሚል የመጡትና ስውር አጀንዳ ያላቸው ኢየሱሳውያን የባሰውን የወንድማማቾች ደም መፋሰስን አስከትለዋል። ከንጉሱ ጀምሮ የብዙዎቹን ሃይማኖት አስቀይረዋል። በዚህም የተነሳ መካረር ተፈጥሮ ውዱ የሰው ህይወት እንደዋዛ ተቀንጥሷል። በንጉሱ ትእዛዝ በአንድ ቀን ብቻ ደንቀዝ ላይ 9000 የኦርቶዶክስ ምዕመናን ተሰይፈዋል። የሰው ልጅ ከሁሉ ነገሩ በሃይማኖቱ፣ በእምነቱ ሲመጡበት አይችልም። ለሚያምነው አካል መሞትንም እንደ ትልቅ መታደል ይቆጥረዋል። በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን የተፈጠረውም ተመሳሳይ ነው። የቅዱስ ሲኖዶሱን ሉዓላው ስልጣን በሻረ መልኩ የተፈጸመውን መፈንቅለ ሲኖዶስ መንግስት ችላ ሊለው አይገባም። ከዳር ሆኖ ምዕመናኑንም ሆነ ጳጳሳቱን የሚያስቆጣ ንግግር ከመናገር መቆጠብ አለበት። ሲሆን ሲሆን በሀገረ ምስረታ ላይ ሊገልጹት የማይቻል ውለታ ለዋለች ሃይማኖት መንግስት ከጎኗ ሊሆንና የሚተናኮሏትንም ሊከላከልላት በተገባ ነበር። ከብዙ ዐመታት ጀምሮ የኦርቶዶክስ አማኞች ሲገደሉ፣ ሲሳደዱ፣ ሲታረዱ መቆየታቸው የአደባባይ ሃቅ ነው። ይሄ ሁሉ በዝምታ ቢታለፍም የአሁኑ ግን ሊታገሱት የማይገባ ነውና መንግስት ቶሎ ሰላም ቢያወርድ ይበጃል። ምንም አያመጡም እየተባለ እንደ ዋዛ መታየቱ በኋላ ውጤቱ የከፋ ሊሆን ይችላል። እናም ይሄን ጉዳይ በቶሎ እልባት ይሰጥ ዘንድ ፓፒረስ ፀጋዓለም ዳኜ እመቤት መክብብ ፀጋዓለም ዳኜ መጽሔት ታሳስባለች።
ማውጫ ገጽ ዲጂታል መታነቂያ ወይስ መታወቂያ? 1 ባህላችን 4 ጆሮ ዳባ! ለባለቅኔ? 7 ስለ አንቺ 12 ውበት 13 የፊልም አከራዩ የፍቅር ደብዳቤ 15
ዲጂታል መታነቂያ ወይስ መታወቂያ? 1 በውብአረገ አድምጥ የሰው ልጅ ጋርዮሽ ስርዓተ ማህበር ጀምሮ መሰባሰብንና የራሱን መሪ መምረጥ የባህርይ መገለጫው ነው። የሰው ልጅ ከዚያ ማንነቱ ፈቀቅ አላለም። ተራቀቀ እያልን በምንጠራው በዚህ ዘመንም ስነ ፈሊጥ ብዙ መልኮችን ይዞ ከተፍ ብሏል። ብዙዎቹ የአንድን ሃገርም ይሁን የአንድን መንደር ህዝብ በብረት በትር ቀጥቅጠው መግዛት ይፈልጋሉ። ለዚህ የስልጣን ማማም ከሰው ህይወት እስከ ገንዘብ ድረስ በዋል ፈሰስ ይረግፋል። ለዚህም ሲባል ዜጎቻቸውን የሚቆጣጠሩበት አንዳች መላ በማበጀት ውስጥ ህይወቸውን ይገፋሉ። ይሄ የዲጂታል መታወቂያ ጉዳይም ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ ነው። ከአምስት ወራት በፊት በሃገሪቱ የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት “መታወቅ መብት ነው” በሚል መሪ ቃል ምዝገባውን ጀመሮ እስካሁንም በመካሄድ ላይ ይገኛል።የምዝገባውን መጀመርም አስመልክቶ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ዋናው የምንሰጠው አገልግሎት በአገልግሎት ሰጭና በደንበኛው መካከል መተማመን መፍጠር ነው” ብለው ነበር። ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም በዚህ ፕሮጀክት በቀጥይ አራት ዓመታት ከ70 ሚሊየን የሚበልጡ ዜጎች ብሔራዊ መታወቂያ ይኖራቸዋል ብለዋል። ይሄ መታወቂያም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ዜጋ ወይም ነዋሪ ሊኖረው የሚገባው መታወቂያ መሆኑንና ከመታወቂያ ካርድም እንደሚለይ ጠቁመዋል። ዮዳሄ ዘሚካኤል፤ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ምንጭ- አል ዐይን አማርኛ ይሄንን ተከትሎም ዋዜማ ሬዲዮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ለመስራት ሚያስችሉ 150 ማተሚያ ማሽኖችን በ 196 ሚሊየን ብር ወጪ ገዝተው ማስገባታቸውን ገልጸዋል። ደንበኞች እንደሚመዘግቡ የብሔራዊ መታወቂያ ድህረ ገጽ ያመለክታል። በዚሁ ድህረ ገጽ ላይም ይሄ ዘመናዊ ዲጂታል መታወቂያ ሊያስገኛቸው ይችላሉ ተብለው የሚታመኑት ጥቅሞች ማህበራዊ ደህንነትና የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ የተሻሉ የፋይናንስ አገልግሎቶች ፣የሃብት አስተዳደርና ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ማንነትን በዲጂታል ስርዓት በማረጋገጥና የማጭበርበር ወንጀሎችን በመከላከል ደህንነትን ማስጠበቅ የዲጂታል አገልግሎትን እንዲሁም ኤሌክትሮኒክስ ግብይትን ማቀጠፍ የመሳስሉት እንደሆኑ ተገልጿል። ለመሆኑ ይሄ ዲጂታል መታወቂያ እንደሚባለው ጥቅም ሊከት እንደሚችልስ ታስቧል ወይ? የሚለውን ለማየት እንሞክራለን። ሀገራት መሪዎች ዜጎቻቸውን ጠንካራ በሆነ የደህንነት መረብ ውስጥ ይዘው በተጠናከረ የስለላ ዘዴ መምራት በሚመስል ነገር ግን በጭቆና አገዛዝ ውስጥ ያሉ የዓለም ሀገራትን መጥቀስ ይቻላል። ለዚህም እንደ ምስክር ቻይናንና ህንድን መመልከት በቂ ነው። በቻይና ከዲጂታል መታወቂያ ጋር በተያያዘ አዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖች ሳይቀር መረጃ ለመንግስት እየላኩ መሆኑን ቢዝነስ ኢንሳይደር በህዳር 30 ቀን 2018 እ.አ.አ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። ፍራንስ04 ዶት ኮም እንደዘገበው በህንድ ከዚሁ ከዲጂታል መታወቂያ ጋር በተያያዘ የጅምላ ስለላ መኖሩን ገልጸው ብዙ ተቃዋሚዎች መነሳታቸውን አልደበቁም። በሃገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ስድስት ጊዜ ይሄ ጉዳይ ከዜጎች አናት መጽናቱን የማህበረሰብ አንቂዎች ተናግረዋል። መንግስት ስለ እያንዳንዱ ህንዳዊ የፈለገውን መረጃ ያለ ማንም ነገሮችን የሚያደርግበት መንገድ ይለያይ እንጂ አሁንም ከተማ አስተዳደሮች ይሄንን ዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ እስከ ዛሬ ማለትም ረቡዕ, ጥር ቀን 17 2015 ዓ.ም ድረስ ከ1.4 ሚሊየን ዜጎች በላይ ለዲጂታል መታወቂያው መመዝገባቸውንና በቀንም በአመካይ እስከ 5250 ብቻ ነው ወይ ያለው? ከዚህ የባሰ አዘቅት ውስጥ ዜጎችን በዚህ የዲጂታል ዘመን የአንዳንድ ይፈልጋሉ። ላይ ላዩን ሲያዩት ዲሞክራሲያዊ እድገት ላይ ይነሳ ዘንድ ውሳኔ ቢተላለፍም መንግስት በእምቢታው ዲጂታል መታነቂያ ወይስ መታወቂያ?
ዲጂታል መታነቂያ ወይስ መታወቂያ? 2 ፈቃድ መውሰዱ ዜጎችን እጅግ አሳስቧል። በዚሁ አድሃር በሚባለው የዲጂታል መታወቂያ የተነሳ ማንኛውንም ባንክ ሲሄዱና ገንዘብ ሲያስተላልፉ፣ የስልክ ጥሪ ሲያደርጉ በአጠቃላይ ማንኛውንም ድርጊት ሲያደርጉ ቀጥታ በቁጥጥር ስር መሆናቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ይሄንንም የደህንነት ፍጹም ወረራ ሲሉ ይገልጹታል ከዚህ ሁሉ ጀርባም የፈረንሳይ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች ኩባንያዎች ለሃገራቱ የስለላ አገልግሎትና የመረጃ ደህንነት ጉዳዮች እያቀላጠፉ እንደሚገኙ በተያያዥነት መነሳቱ አልቀረም። ይሄ ጉዳይም ወደ ሃገራችን መግባቱን ማረጋገጥ የምንችለው አሌፍ (ALEPH), አሪንክ (ARINC), እና ታለስ (THALES) የተባሉ የፈረንሳይ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ጋር አብረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው በፓሪስ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኢምባሲ ስብሰባ ማድረጋቸውን ኢትዮጵያን ሞኒተር (Ethiopian Monitor) በመስከረም 1 ቀን 2022 እ.አ.አ ያወጣውን ዘገባ በመመልከት ነው። እነዚህ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም በዳር ድንበር ካሜራዎች፣ እንዲሁም በዲጂታል መታወቂያና ደህንነት ጉዳይ ላይ አብረው እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስምምነቱን ያደረጉትም የአሌፍ ዳይሬክተር ያኒክ ሮላንድ፣ የአሪንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አሌይን ማርሳን፣ የታለስ ምክትል ፕሬዝደንት ጅን ክላውዲ ፔሪን ከአምባሳደር ሄኖክ ጋር ነበር። ምንጭ- Ethiopian Monitor ለመሆኑ ይሄ ዲጂታል መታወቂያ የዜጎችን ዕለት ከዕለት ህይወት ከማቀላጠፍ በዘለለ ምን ችግር ሊያመጣ ይችላል? ይሄንን መቃወምስ የሰውን ልጅ እድገትና ዘመናዊነት መጻረር አይደለም ወይ? የሚል ሃሳብ መነሳቱ የማይካድ ነው። ሀገራችን የውስጥም የውጭም ባላናጣዎች ያሏት ሃገር ናት። በታሪክ እንደምንረዳውም ሆነ አሁን ላይ እንደምናየው የብዙ ሃገራት ስውር እጆች የእኛን ሰላም እያደፈረሱት ይገኛሉ። የእያንዳንዱን ዜጋ ሙሉ መረጃ ከሰበሰብን በኋላ እነዚህ ሀገራት ባላቸው የቴክኖሎጂ ብልጫ ተጠቅመው እንደማይመዘብሩን ምን ዋስትና አለን? የእያንዳንዱ ዜጋ ሙሉ ማንነት በጥቂት ሰዎች ወይም ባለስልጣናት ቁጥጥር ውስጥ መሆኑ እንደማይቀር እሙን ነው። ዛሬ ዛሬ የሰው ሰነዶች ለውጭ ሀገራት እየወጡ እየተሸጡ ባሉበት ወቅት የእጅን የዓይንን አሻራ አምኖ መስጠትስ ከዚህ የሽያጭ ተግባር ዜጎች ነጻ ስለመሆናቸው ምንም ማረጋገጫ አይኖርም። በዘመናችን ታላቁ ጦርነት ባዮሎጂካል ጦርነት ነው። የዜጎች እያንዳንዱ መረጃ በጥቂቶች እጅ መሆኑ የሃገሪቱን የጤና ሁኔታ ተጋላጭ ያደርገዋል። እኩይ ዓላማ ያላቸው ግለሰቦች ይሄንን መረጃ ካገኙት በጅምላ ሊጨርሰን የሚችል በሽታ አምርተው እንደማይለቁብን መተማመኛ የለንም። እነዚህን ሁሉ ጉዳዮች መንግስት ባለኝ ቁጥጥር ለመጠበቅ መፈናፈኛ እንኳን ሊኖረን አይችልም። ለምሳሌ የአንድ ግለሰብ ሙሉ መረጃ የመረጃ ቋት ውስጥ ይከማቻል። የዓይኑና የእጁ አሻራ ከ እድሜው ከስራው ሁኔታ፣ ከጤናው ሁኔታ ከሁሉም ማንነቱ ጋር ይከማቻል። የባንክ አካውንቱ፣ የትምህርት ማስረጃው፣ የህክምና መለያ ቁጥሩ ሁሉ የስልክ ቁጥሩ ሳይቀር ከዚህ ዲጂታል መታወቂያ ጋር የተያያዘ ይሆናል። እነዚህ ሁሉ መረጃዎች ደግሞ ከደህንነት ካሜራዎችና ከመንገድ ላይ መብራቶች ጋር ይያያዛሉ። ግለሰብ መቃዎም ቢጀምር ምን ሊከሰት ይችላል? በመጀመሪያ የዚህ ግለሰብ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በመንግስት ቁጥጥር ውስጥ ይሆናል። በጉዳዩ ላይ ጥናት እያደረገ መረጃው ለደህንነት ሰዎች ይደርሳል። እንቅሳቃሴ መንግስት ከጀርባ ሆኖ መመልከት እንደሚችል ተናግረዋል። ወደየት እንደሚሄዱ፣ ምግብ ሲያዘጋጁ፣ ወደ እንደሚገኙ ተገልጿል። እነዚህ የፈረንሳይ ታላላቅ ቁጥጥር፣ በኢንተርኔት የስለላ አገልግሎት፣ በደህንነት ሁሌ እንደሚባለው አረጋግጣለሁ ቢል እንኳ ራሳችንን ከአምባገነን መሪዎች መንግስት ዜጎችን እየረገጠ መግዛት ቢጀምርና አንድ
ዲጂታል መታነቂያ ወይስ መታወቂያ? 3 ምክንያቱ ከስልኮች ጋር የተገጠመ ካሜራ አለና። ካሜራውን ብናልፍ እንኳን ስልኩ ይታወቃልና። ታዲያ በዚህ ጊዜ መንግስት ቀጥታ የባንክ አካውንቱን ይዘጋል። እያንዳንዱን ማህበራዊ አገልግሎት እንደ ስልክ፣ መብራት፣ ህክምና የመሳሰሉትን እንዳይገለገል ይሄ ፍጹም ባርነት ነው። አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ በአልቦ ዘመድ መጽሐፉ እንዲህ ይላል። “የሰው ልጅ ነገሮችን የሚያደርግበት መንገድ እንጂ እየተራቀቀ የሄደው አሁን ድረስ አስተሳስቦቹ እንዳሉ ናቸው” ይላል። ይሄም ማለት ባርነት ቀረ፣ በህግም ተከለከለ እንላለን እንጂ በሌላ መንገድ አሁን ድረስ እየተተገበረ ነው እንደማለት ነው። ቃሉ እውነት አለው። ዜጎችን እዲህ ባሉ ዘላቂ ቀንበሮች ውስጥ ማስገባት እንደፈለጉ ይሄ ጉዳይ በሃራችን ከተተገበረ ነገሩን የሚያከብደው ተጨማሪ ጉዳይ አለ። የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ድህረ ገጽ እንደሚያመላክተው የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ያስፈልጋሉ ያላቸው መሰረታዊ የማንነት መለያዎች እነዚህ ናቸው። ጾታ፣ ሙሉ ስም፣ የትውልድ ቀን፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ እንዲሁም የዓይንና የእጅ አሻራዎች ናቸው። ማስፈንጠሪያውን ተጠቅመን ወደ ድህረ ገጹ ስንገባ ግን ደንበኛው መሙላት ካለበት ግዴታዎች ውስጥ አንዱ ብሄር ነው። ምንጭ- የብሐሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ድኅረ ገጽ ምክንያት ስትታመስ ከ 50 ዓመታት በላይ ሆኗታል። ሙሉ መረጃ ከእነ ብሔራቸው መሰነድ ሌላ ነገር እንድንጠረጥር ያደርጋል። የተማሪዎች ፈተና ሳይቀር መቀበል ያስቸግራል። ዛሬ ሃገሪቱን እየመራ ያለው የብልጽግና ፓርቲ ለአንድ ብሔር ብቻ የሚያደላ ነው እየተባለ ይታማል። እሱ ብቻ አይደለም በተለያዩ የሃገሪቱ ከፍሎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት እየተመረጡ እየተገደሉ ይገኛሉ። ከዚህ ስነልቦና ውስጥ ያልወጣ የፖለቲካ መሪ ባለበት ሃገር ውስጥ ይሄን መረጃ መሰብሰብ የባሰ እልቂት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ታዲያ ወደዚህ ሁሉ የዜጎች ዘለዓለማዊ እስር ከመግባት በፊት ምን መደረግ አለበት የሚለው ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። ለዚህም ብዙ ምሁራን ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። ከእነዚህ መካከል በዋናነት ተጠቃሿ ካትሪን ኦስቲን ፊትስ (Catherine Austin Fitts) ናቸው። እኒሁ ሴትዮ የቀድሞው የአሜሪካ የቤቶችና የከተማ ልማት ምክትል ዋና ጸሐፊ የነበሩና በአሁኑ ሰዓት የሶላሪ ኢንክ ፕሬዝደንት ናቸው። እሳቸውም ጤነኛ የሚባለው አሰራር ከፊሉ ዲጂታል ከፊሉ ደግሞ አናሎግ (የወረቀት) ሲሆን ነው ብለው ይናገራሉ። የወረቀቱን ጨርሶ ጥሎ ሙሉ በሙሉ ዲጂታሉን መጠቀም የዜጎችን ነጻነት መግፈፍ ነው ሂትለር የዲጂታል የጭፍጨፋ ቦታ (Concentration Camp) ነው ብለዋል። ሃሳባቸው እውነት አለው። ከሁሉም ነገር በበለጠ የሰው ልጆች ነጻነታቸውን ይፈልጋሉ። ዛሬ ሳያጤኑበት ፍጹም የሆነ ነጻነታቸውን አሳልፈው ከሰጡ በኋላ ህይወታቸው ከእስረኛ ምንም የተሻለ አይሆንም። ቴክኖሎጂዎች ሁሉ የመጨረሻ ግባቸው የሰው ልጆችን ህይወት ማቅለልና ነጻነታቸውንም በደንብ ማስጠበቅ መሆን አለበት። ከዚሁ የተሻገረና ግለሰባዊም ሆነ ሀገራዊ ነጻነትን የሚጋፋ አሰራር በህዝቦች ላይ ከመስፈኑ በፊቱ ቆም ብሎ መመልከት መልካም ነው እንላለን። አካውንቱን በመከልከል ሊያሽመደምደው ይችላል። ለመነዳት ከመፈለግ ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። እውነታው ደግሞ ሃገራችን በዚህ የብሐር ፖለቲካ ይሄ ችግር ተካርሮ በግልጽ እየታየ በግላጭ የዜጎችን እየተሰረቀ እየወጣ ባለበት ሰዓት ይሄንን አምኖ የማይጠረጠርበት አንዳች ምክንያት የለም። ይላሉ። ጉዳዩን ሲያገዝፉትም ዲጂታሉ ብቻ መጠቀም እንደ
ባህላችን 4 ባህላችን በብሌን ደምሴ ባሕላዊ የመተጫጨት ሥነ ሥርዓት በብሔረ ዛጉዌ © Internet ብሔረ ዛጉዌ በአሁኑ ወቅት በአማራ ብሔራዊ ክልል ውስጥ የአገው ኸምራ ዞን የሚባለውን ቀደም ሲል ደግሞ የኦፍላ ወረዳን አጠቃሎ የዋግ አውራጃ የነበረውንና ከጥንት ጀምሮ የላስታ እውራጃ ይባል የነበረውን እንዲሁም የቡግና ወረዳዎችን የሚያካትተውን አካባቢ ያቅፋል። መታጨት ሲባል አንድ ሰው ለብዙ ቁም ነገሮች ሊታጭ ይችላል ፡፡ ለምሳሌ ያህል ፣ ለሹመት ለምክር ቤት ( ለፓርላማ ) እጩ ተወዳዳሪነት ለትምህርት ቤት ማጠናቀቂያ ምርቃት ወዘተርፈ ችአው። በዚሀ ጽሑፍ ውስጥ የተቀመጠው “መተጫጨት” የሚለው ቃል ግን የሁለትዮሽ ማለትም የወንድንና የሴትን መግባባትንና ስምምነትን የሚጠይቅ ሆኖ ፅንሰ ሐሳቡ ትርጉም ለሁለቱም ተጋቢዎች ቅጽል ወይም ስማዊ ባለቤት በመሆን የሚያገለግል ነው። ይሀንንም “ እጮኛሞች ወዘተርፈ ከሚሉት ቃላት ጋር ማገናዘብ ይቻላል፡ መተጫጨት ሁለት ተቃራኒ ፆታ ያላቸው ተጋቢዎች የጋራ ኑሮ መሥርተው አንድ አካል ወደሚሆኑበት የትዳር ቁም ነገር የሚያደርስ ጥርጊያ ጎዳና ስለሆነ በተጋቢዎቹ ጠለቅ ያለ መተዋወቅንና መጠናናትን የሚሻ / የሚጠይቅ ታላቅ ጉዳይ ነው። በብሔረ ዛጉዌ በመተጫጨት ላይ የወላጆች ሚና በብሔረ ዛጉዌም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዘንድ እንደተለመደው በባሕላዊ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት መሠረት ሴት እጮኛን ፍለጋ ግንባር ቀደም እንቅስቃሴ የሚደርጉት ልጃቸው እጮኛን የሚያፈላልጉ ወላጆች ወደምትታጨው ልጃገረድ ቤተሰቦች ቤት ከማምራታቸው አስቀድሞ የሚያጠኗቸውና የሚመረምሯቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ። ከነዚያ ቁም ነገሮች መካከልም ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡- የልጅቷ ቤተ ሰቦች የዘር ሐረግ አመጣጥ ፣ ባላባቶችና ባለርስት መሆናቸው ( በተለይ ከ 1967 ዓ.ም የመሬት ለአራሹ ዓዋጅ በፊት በነበሩት ዘመናት ) በቂ ሐብት ያላቸው መሆኑ ፣ ከወንዱ ቤተሰቦችና ከዘር ማንዘራቸው ጋር ደም ያልተቃቡ ፣ ማለት የነፍስ ግድያ ችግር የሌለባቸው መሆናቸው የቀረበ የሥጋ ዝምድና የሌላቸው መሆኑ ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይነታቸውና ሌሎች በርከት ያሉ ተዛማጅ ነገሮች ናቸው። እነዚህና በተጨማሪ ተጠንተው መጠናቀቅ ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ ከተጣሩ በኋላ እጮኛ የመለመኑ ሂደት በቀጣይነት ይጀመርና ከትትሉን በኃላፊነት አማጭ ማለት የሁለቱን ወጣት ተጋቢዎች የመተጫጨት ሂደት ለማካሄድና እስከ ሠርጋቸው ቀን ድረስ ከግቡ ለማድረስ በወንዱ ልጅ ቤተሰቦች የሚመረጥና የሴቷን ልጅ ወላጆች ይሁንታንና ተቀባይነትን የሚያገኝ ታዋቂና የማሳመን ብቃት ያለው ግለሰብ ነው። ወደ ሁለቱም ቤተሰቦች በመመላለስ አስፈላጊ መልእክቶችን ያስተላልፋል ፡፡ ከፍ ብሎ እንደተወሳው ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሰጠው በገጠሩ የብሔረ ዛጉዌ አካባቢዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ በሆነው ማኅበረሰብ በኩል ለሚደረገው ባሕላዊ የመተጫጫትና የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው። ስለሆነም በከተሞች አካባቢ ሁለት ዘመናዊ ተቃራኒ ፆታ ወጣቶች ወላጆቻቸው ሳያውቁ እርስ በርሳቸው ተስማምተው የሚፈጽሙ ትን የወቅቱን የመተጨትና የጋብቻ ሥልት አያካትትም ፡ ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ብዙውን ጊዜ የተለመደው ከወንዱ ቤተሰብ ሴት ልጅን የማጨት ሁኔታ ከፍ ብሎ የተነሣ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ የወንዱ ልጅ ወላጆች ሴት ልጅ እጮን ለመፈለግ ሳይንቀሳቀሱ ጥናትም ሳያካሂዱ በድንገት ለልጃቸው እጮኛን የማግኜት እድሎች ሊፈጠሩላቸው ይችላሉ። ከነዚህ መልካም አጋጣሚዎች መካከል አንደኛው የሁለቱ ተጋቢዎች ወላጆች በተለያዩ ቦታዎች ሲገናኙ የሚከሠት ነው።የሁለቱ ወጣቶች ወላጆች ወይም ቤተ ዘመዶች በተለይም ወንዶቹ በልዩ ልዩ ሁኔታዎች በአደባባይ፣ በአብያተ ክርስቲያናት ፣ በዝክርና በለቅሶ ፣ ወዘተረፈ ሊገናኙና ቀስ በቀስም ተላምደው በጥልቀት ሊተዋወቁ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ የሴቷ ልጅ አባት / አጎት ወይም ሌላ የቅርብ ዘመድ የሆነ ሰው በወንዱ ልጅ አባት በተለይ ” ናቸው “ እጮኛ ” አለው ፣ “ እጮኛ አላት ተጭጭተዋል ወጣቶች በራሳቸው ወይም በቤተሰቦቻቸው አማካኝነት የወንዱ ልጅ ቤተሰቦች ናቸው፡ በዚህ አግባብም ለወንድ የሚወስድ ወኪል / አማጭ ተመርጦ ይመደባል ፡፡
ባህላችን 5 በቤተሰቦቹ ሁኔታ በአጠቃላይ በመደሰትና የቅርብ ዝምድናቸውን አጥብቆ በመፈለግ ከግራና ከቀኝ ያሉ በጎ አመለካከቶችን በማመዛዘን የወንዱ ወገን ሳያስበው በድንገት “ ልጄን ለልጅህ ሰጥቼሃለሁ ሊለው ይችላል። በዚያን ጊዜ የወንዱ ልጅ አባት ምንም እንኳን ከቤተሰቦቹና ከወገኖቹ ጋር በጥልቀት መክሮና ዘክሮ ስለ ሴቷ ልጅ ቤተ ሰቦች ዝርዝር ጥናት ያላደረገ ቢሆንም የወደፊት እጮኛና ሚስት ልትሆንለት የምትችለውን ልጃገረድ ጋር ካለው የቆዬ ትውውቅ በመነሣትና ከፈቀደለት ሰው ለልጁ የወደፊት እጮኛና ሚስት ልትሆንለት የምትችለውን ልጃገረድ በማሰብ የመተጫጨቱን ሃሳብ ሊቀበል ይችላል። አማጩ ወደ ልጃገረዷ ቤተሰቦች የሚላከውም በፈቃደኝነት በወላጅ አባት በአጎት ወይም በሌላ የቅርብ ዘመዱ አማት “ ልጄን ለልጅህ ሰጥቻለሁ ” ለተባለችውም ሆነ በወንዱ ቤተሰቦች የግል ጥረት ተፈልጋ ለተገኜችውና በሌሎችም ልዩ በተጣለበት ባሕላዊ አደራ መሠረት ወደ ሴቷ ወላጆች ከወንዱ ልጅ ቤተሰቦች የተሰጠውን መልእክት እነሱን በመወከል ነጠላውን / ኩታውን በወገቡ አደግድጎ ከፊታቸ በመቆም እጮኛዋን እንዲፈቅዱለት ይማጠናል / ይለምናል ፡፡ የሴቷ ልጅ ቤተሰቦችም ስለ ጉዳዩ ቀደም ብለው ቢያውቁም ባያውቁም ልክ የወንዱ ወላጆች እንዳደረጉት ሁሉ በእጮኛ ጠያቂዎቹ በኩል ያለውን ሁኔታ በዝርዝር ወገን ጋር መክረን መልሱን እንነግርሃለን ” በማለት የቀጠሮ ቀን ሰጥተው ያሰናብቱታል። ከዚያም የልጃገረዷ ቤተመዶች ተሰባስበው ስለጉዳዩ በስፋት ከተወያዩና ከተመካከሩ በኋላ መተጫጨቱን ካላጋጠማቸው በስተቀር በሰጡት የቀጠሮ ቀን አማጭ ብለናል ” በማለት የምሥራቹን ይነግሩታል። እሱም ያንኑ ደስ የሚያሰኝ መልስ ሳይውል ሳያድር በአስቸኳይ ለወንዱ ልጅ ቤተሰቦች ያበሥርና ቀጣይ ተግባራትን በቅደም ተከተል ለማከናወን ይዘጋጃል ፡፡የሴቷ ልጅ ወላጆች ለወንዱ ልጅ ቤተሰቦች የሚያስተላልፏቸው ትእዛዞች የታጨችው ልጃገረድ ወላጆች የሚፈልጉትን ጉዳይ የወንዱ ቤተሰቦች እንዲያከናውኑላቸው ሲከጅሉ በአማጩ በኩል ትዕዛዝ ያስተላልፉላቸውና ያለምንም ማመንታት እሺ በጎ ብለው ተፈፃሚ ያደርጋሉ። የልጃገረዷ ወላጆች እንዲተገበሩላቸው ከሚያስተላልፏቸው ትእዛዞች መካከልም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው። እርሻን ማረስ የወንዱ ልጅ ወላጆች በአማጭ በኩል የሚደርሳቸውን ሑዳድ መሬት የመደበል ( የማረስ ) ወይም አርሶ የመዝራት ትእዛዝ ከዚህ ቀጥሎ በተቀመጠው መንገድ ያከናውናሉ። ትእዛዙ ከሴቷ ልጅ ቤተሰቦች ቀደም ብሎ እንደደረሳቸው የወንዱ ልጅ ቤተሰቦች ጎረቤት ዘመድ አዝማድ ጥማድ በሬዎቻቸውን በማሰባሰብ መጥተው እንዲያግዟቸው ይለምኗቸዋል። እነዚያም ሰዎች ከዚያ በፊት ትብብር ጠያቂዎቹ የዋለላቸውን ውለታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ያለምንም ማመንታት በተባለው ቀንና ቦታ ጥማድ ያላቸው ጥማዳቸውን የሌላቸው ደግሞ ዶማቸውን ይዘው እንዲታረስ ትእዛዝ ከተሠጠበት ሁዳድ ይዘምታሉ። ከዚያም በአንድ ቀን ደብለው አርሰውና ዘርተው የተደገሰውን ምግብና መጠጥ ተጋብዘው ማታ ለማታ አካባቢ ወደየቤታቸው ይመለሳሉ። ሰብልን መሰብሰብ የመኸር ወቅት ሲደርስ የልጃገረዷ ወላጆች ያዘመሩትን ሰብል ብቻቸውን ሰብስበው ለመክተት የሚያዳግታቸው መሆኑን ሲረዱ የወንዱ ልጅ ቤተሰቦች እንዲያጭዱላቸው ትእዛዙ እንደደረሰም ታዛዦቹ ከፍ ብሎ እንደተነገረው ወገኖቻቸውን አሰባስበው በአካባቢው የተለመደ አጠራር መረት ወበራ / ደቦ ወይም ጅጌ በሚባለው ተባብሮ የደረሰውን ሰብልም በአንድ ቀን አጭደውና ከምረው የተዘጋጀውን ድግስ በልተውና ጠጥተ ወደ የመኖሪያቸው አመሻሽ ላይ ይመለሳሉ። ለቤት ጣራ ክዳን የሚሆን የጥድ ጠርብ ማጓጓዝ ወይም ሰንበሌጥ ሣር አጭዶ ማምጣት አብዛኛውን ጊዜ ለቤት ጣሪያ ክዳን አገልግሎት የሚውሉት የጥድ ጠርብና የሰንበሌጥ ሣር የሚገኙት ደጋማና ወይና ደጋማ ሥፍራዎች ነው። በተለይ ቆላማነት በሆኑ ጥጋግ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የሴት ልጅ ወላጆች ይህን ዓይነቱን ትእዛዝ እንዲፈጽሙላቸው ሲፈልጉ መልእክታቸውን ለወንዱ ልጅ ቤተሰቦች ይልካሉ። ታዛዦቹም ቀደም ብለው በሚያደርጓቸው ጥናቶች በመመሥረት የጥድ ጠርብና የሰንበሌጥ ሣር አሉባቸው ከዚያም ዘመድ አዝማዶቻቸውን አሰባስበው በወቅቱ በነበረው ሁኔታ ከየጫካው ጥዱን ከዚያ በፊት አስቆርጠውና አስፈልጠው ሣሩን ግን በዕለቱ አሳጭደው ከታዘዙበት ሥፍራ ያደርጋሉ። የሴቷ ወላጆች የሚያዙት ግን ሁለቱን ማለትም ጥዱንና የሰንበሌጥ ሳሩን በአንድ ጊዜ እንዲያመጡላቸው ሳይሆን አንዱን ብቻ በመለየት ነው ።በአሁኑ ወቅት ግን በደን መራቆት የተነሣ የጥድ ጠርብም ሆነ የሰንበሌጥ ሣር ከጫካ ቆርጦና አጭዶ የአማጭ / ትእዛዝ ለመፈጸም አይቻልም። ምክንያቱም ማንም ሰው ያለ መንግሥት ፈቃድ ይህንን ማድረግ ፈጽሞ እንደማይችል በዓዋጅ የተከለከለ ስለሆነ ነው። ከዚህም የተነሣ የሴቷ ወላጆች ይህን የመሰለውን ትእዛዝ ዛሬ የሚያስተላልፉ አይመስለኝም። የወንዱ ወላጆች በአጋጣሚ የሚታዘዙም ከሆነ ቁሳቁሶቹ ካለበት ቦታ በገንዘብ ገዝተው ስለሚወስዱ ዋጋቸው በግድ መታሰብ ይኖርበታል። ባሕላዊ መንገዶችለታጨችሴት ልጆች ጭምር ነው።አማጩ አሁንም ትእዛዛቸውን በአማጭ በኩል ያስተላልፋሉ። ለማጥናት ወይም ለአባት አደሩና ለወጉ ለማእረጉ ሲባል የሚከለክል ወይም የሚያሰናክል ጠንከር ያለ ችግር ሲመለስ “ ተቀብለናል ፈቅደናል አቻ ለአቻ ጋብቻችን ነው የመሥራት ሂደት ወደ ከታዘዙበት ማሳ / ሁዳድ ይጓዛሉ። የሚባሉትን ቦታዎች በትክክል ለይተው ያረጋግጣሉ።
ባህላችን 6 የጤፍ ዱቄት ማስፈጨት የሴቷ ልጅ ወላጆች ለሠርግ ለተዝካር ወዘተርፈ ድግሥ የሚያገለግል የጤፍ ዱቄት በሴቶች እጅ ከቤታቸው አሰልቀው ማድረስ ሲሳናቸው ሥራውን ሙሉ በሙሉ ወደ ወንዱ ልጅ ቤተሰቦች በትእዛዝ መልክ ያስተላልፉታል፡ ትእዛዝ ተቀባዮቹም ዘመናዊ የእህል ወፍጮዎች ራቅ ባሉ የዙሪያ ገቡ ከተሞች ተተክለው በነበሩበት ዘመን ዓቅማቸው የሚፈቅድ ከሆነ የራሳቸውን በርከት ያሉ የጋማ እንስሳትን ( አህያ፣ በቅሎ፣ ፈረስ ) ከየወገኑም ጭምር በትብብር አሰባስበው ጤፉን ከተቀመጠበት ቦታ ሄደው በማስጫን በነዚያ ወፍጮዎች አስፈጭተው መልሰው ይሰጡ ነበር ።ይህን ማድረግ የማይችሉት ግን ጤፉን ወደ እንደዓቅማቸው ወስደው ነበር።በአሁኑ ወቅት ግን በገጠሩ ቢሆን በእጅ መፍጨት የለም። ካልተቋረጠና አሁንም ከቀጠለ ተፈፃሚ የሚሆነው በዚሁ መንገድ ነው። የሚጠምዱት በሬ የሚያጥራቸው ከሆነ የተሰጠውን በዚህ ባሕላዊ የመተጨት ሥነ ሥርዓት ላይ ሴቷን ልጅ የመምረጡም ተግባር ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ድረስ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በወላጆች ውሳኔ ብቻ ነው። ሁለቱ እጮኛሞች በተለይ የሚኖሩባቸው አካባቢዎች በጣም የተራራቁ ከሆኑ እስከ ሠርጋቸው ዕለተ ቀን ድረስ ምንም ዓይን ለዓይን የመተያየት ዕድል የላቸውም። አልፎ አልፎ ግን ወንዱ ልጅ ምንም እንኳ የወላጆቹን ውሳኔ ማስቀየር ባይችልም “ ልጅቷ ቆንጆ ናት ወይስ ለማረጋገጥ ተደብቆም ቢሆን እጮኛው ወደምትኖርበት መንደር በመጓዝ ወደ ወንዝ ወርዳ ውሀ ስትቀዳ። ወደ ጫካ ሄዳ እንጨት ስትለቅም። ከብቶችን ስታግድ። ለጥምቀት ወይም ለሌሎች ክብራተ በዓላት ተጊጣና ተውባ ከእድሜ እኩያዎቿ ጋር ለማክበር ስትሄድና በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች ከቤቷ ስትወጣ ሳይታወቅበት አይቷት ሊመለስ ይችላል ፡፡ በሌላ በኩል ግን ሴቷ ልጅ በእድሜዋ ከወንዱ ልጅ በጣም የምታንስ ከመሆኗ አንፃር ከቦታው ርቀትና ከባሕል ተፅዕኖም የተነሣ እጮኛዋ ያደረገውን ዘዴ ተጠቅማ ሁኔታውን የማጣራት እድል አይኖራትም :: እንዲያውም ሁኔታው ሁሉ ገና ምንም ስለማይገባት በጭራሽ ሐሳቡም አይኖራትም። በዚህም ምክንያት እጮኛዋን ለመጀመሪያ ጊዜ እያፈረችም ቢሆን የምታየው በሠርጋቸው ቀን ብቻ ነው። በሌላ በኩል ሁለቱ እጮኛሞች የሚኖሩት በጎረቤት አካባቢ ከሆነ እርስበርሳቸው ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ይተዋወቃሉ። አብረውም ያድጋሉ። ቤተሰቦቻቸውም ጧትና ማታ ቀን በፊት ያለውን ሁኔታ ዝርዝር ሁለታቸውም ያውቁታል። ከዚህ በላይ እንደተገለፀው ወንዱ ወላጆች / ቤተሰቦች በጎረቤት አካባቢ የሚኖሩ ወይም በአንድ ሰበካ ሆነው በየጊዜው የሚገናኙ ካልሆኑ በስተቀር ራቅ ባሉ ቦታዎች የሚኖሩ ከሆኑ ልጅቷን ከማግባቱ አስቀድሞ በእጮኛነት እያሉ ከአባቷ ከእናቷ ወይም ከሌሎች የቅርብ ዘመዶቿ ጋር በግልፅ እንዲተዋወቅ ባሕሉ አይፈቅድለትም። በአጋጣሚ ከሩቅ ሲመጡ ካያቸውም ሸሽቶ ይደበቃል። ከራሱ ወላጆች መኖሪያ ቤት በእንግድነት ተጋብዘው ከመጡም እስከሚሄዱ ድረስ ተሸሽጎ ይቆያል። በእሱ ፋንታም ወንድሞች ካሉት እንግዶቹን ከአደባባይ ጀምሮ ከቤት ተስተናግደው እስኪወጡ ድረስ ዘንጋቸውን፣ ጫማቸውን፣ ጠብመንጃ ካለም እሱን ወዘተርፈ በመቀበል ተንከባክበው ይሸኟቸዋል ፡፡ ውስጥ በቅርብ የሚኖሩ ከሆኑና አዘውትረው ከተገናኙ ወንዱ ልጅ ለእጮኛው አባትም ሆነ እናት ራሱን በማጋለጥ እጅ ነሥቶ ጫማ ስሞ ይተዋወቃቸዋል። ከዚህ በኋላ በሌላ ቀን ሲያገኛቸው በቅሏቸውን ይቀበላቸዋል ( ካላቸው )ጠብመንጃም ከያዙ ይሸከምላቸዋል። ዘንጋቸውን ጫማቸውን ተቀብሎ ይይዛል። ጠቅለል ባለ አነጋገር እንደ አሽከርና እንደ ልጅ ሆኖ በአደባባይ ያገለግላቸዋል፣ ይንከባከባቸዋል። ሆኖም ግን በባሕሉ መሠረት ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሄዶ አይገባም። ምግብም አይበላም። መጠጥም አይጠጣም። የእጮኛውን እናት ገና ስላልተዋወቃቸውና በሌላም ምክንያት ሊሆን ይችላል። ከእጮኛው ወላጅ አባት ሌላ የእጮኛውን ቤተዘመዶች በሙሉ ለይቶ ማወቅ ማክበር ትሕትና ማሳየትና በጥንቃቄ መያዝ ይጠበቅበታል። በነሱ ዘንድም ንቁ ብልሕ ቀልጣፋ ወዘተርፈ .. ሆኖ መታየት ይገባዋል ፡፡ ከልጁ በተቃራኒ ግን የታጨችው ልጃገረድ የእጮኛዋ ወላጆች በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች እሷን ሊጠይቁ የወላጆቿን ደስታና ኃዘን ሊካፈሉ ወደ መኖሪያ ቤቷ ሲሄዱ የተላኩላትን አልባሳትና ጌጣጌጦች አድርጋና ተውባ በመምጣት ትስማቸዋለች። በመምጣት ከአጠገባቸውም ቁጭ ብላ ታጫውታቸዋለች። ይህም ሁኔታ የወደፊት አሳዳጊዎቿን አስቀድማ ለማወቅና ለመላመድ መልካም እድልን ይሰጣታል። ከዚህ በተጨማሪም የሁለቱን ተጋቢዎች ጉዳዮ ከመተጫጨት ጀምሮ እስከ ሠርጋቸው ቀን ድረስ ወደቤታቸው እየተመላለሰ የሚያስፈጽመውን አማጩን ልጃገረዷ ከማንም የበለጠ ታውቀዋለች። መኖሪያ ቦታቸው የሰፈራቸውን ሴቶች በለመን በቁና የቀበሌ ማዕከል ዘመናዊ ወፍጮዎች ለታላላቅ የድግስ ተግባራት ብቻ ሳይሆን ለዕት ተዕለት የምግብ ፍጆታም ከዚህ በላይ በቅደም ተከተል ሌሎችም ያልተጠቀሱት ትእዛዞች መካከል አንደኛ ተግባር የታጨችው ልጃገረድ ወላጅ አባት ወይም ሌላ የወኪል ስራው በሚከናወንበት ሥፍራ ፆታውን ለይቶ በመጥቀስ ከበረት ውስጥ ካሉ እንሳት እንድ ቁም የዳልጋ ከብት የተሰጠው መሆኑን ለወንዱ ልጅ ቤተሰቦች በተሳተፉት ሰዎች ፊት በይፋ ይገልጻል፣ ይህም የተሰጠው የዳልጋ ከብት በተጋቢዎቹ የሰርግ ቀን ለወንድ ቤተሰቦች ከሚሰጡት ሽልማቶች ውስጥ ገብቶ ይቆጠራል።የወንዱ ወላጆች ለጊዜውለእርሻ ቁም ከብት አስቀድመው ሊገለገሉበት ይችላሉ። ከብቷ እንስት ከሆነችም ወስደው ጥጃ ስትወልድ የወተቷን አላባ መጠቀም መብት አላቸው። አስቀያሚ ወዘተርፈ የሚለትን ጥርጣሬዎች በዓይኑ አይቶ ስለማይለያዩ የመወሰን መብት ባይኖራቸውም ከሰርጋቸው በሌላ በኩል ደግሞ የሴቷ ወላጆች በአንድ ሰበካ
ጆሮ ዳባ! ለባለቅኔ? 7 ጆሮ ዳባ! ለባለቅኔ? በውብአረገ አድምጥ የአንድ ማህበረሰብ ንቃተ ህሊና በሚያደንቃቸውና እንደ ዓርማ በሚመለከታቸው ግለሰቦች ላይ የተመሰረተ ነው ተብሎ ይታሰባል። ብዙ ጊዜ ቃሉ እውነት አለው። የህይወትን ትብስብስ እየተመለከቱ የማያልፉ፣ መኖር የሚባለውን አሰልቺና አጓጊ ሁነት በሃሳባቸው የሚንጡ አሳቢያን በዓለም ላይ ሁሌም አሉ። ተመስገን ነውና ሀገራችን ኢትዮጵያም ከጥንት ጀምሮ ልቡናቸው ለቅኔ የሰላ፣ ሃሳባቸው ህያውነትን የተመላ አሳቢዎች ነበሯት። አሁንም አሏት። ወደፊትም ይኖሯታል። ከመለኮት እስከ እመቅ እመቃት፣ ከሰፊው የሰው ልቡና እስከ ስነ ተፈጥሮ የሚቃኙ ባለቅኔዎች በሃገራችን እንደ ጉም ተምመዋል። ሀይማኖትን ከዓለማዊ ህይወት ጋር እያዳበሉ በቃል ሰይፍ የሚመትሩ ምላጭ የቅኔ ቋቶች በሃገራችን የታሪክ ሰንሰለት ውስጥ ተሰግስገው ትናንትናችንንም ሆነ ሲልም ብራና ዳምጠው ቀለም በጥብጠው የእውቀት ዣታቸውና የሃሳብ በረከታቸው ለእኛ ይደርስ ዘንድ ተብከንክነዋል። ይሄው ዛሬ ታሪካችን እያልን የምንኮፈስበት ከዓለም ጋርም የምንፎካከርበት የልባችንን ስብራት የሚጠግንልን ሞገሳችን ነው። ታላቁ ጥያቄ ግን እንደ ህዝብ እነዚህን የሃሳብ ባለቤቶች፣ የሰው ልጅ የሚገዳቸው ንቁና ስስ ልባሞችን እህ ብለን እናዳምጣቸዋለን ወይ የሚለው ነው። የምናልፍበትን የታሪክ ድግግሞሽና ዝባዝንኬ በአንክሮ ለሚመለከት ግን ለባለቅኔ ወይም ለአሳቢ የምንሰጠው ጆሮ ከተራ ጭብጨባ እንደማያልፍ አመላካች ነው። ምን እንደነካን እንጃ ዘመናቸው ካለፈ በኋላ ሙሾ መደርደር ይቀለናል። በዘመናቸው እንደ ነብይ እየተናገሩ፣ ከውስጠ ስሜታቸው በሚፈልቅ እዝነትና ስስት መንገዱን እያሳዩን እኛ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለትን የሰርክ ተግባራችን ካደረግነው ቆይተናል። የአሁኑ ደግሞ ይባስ። ከአያያዝ ይቀደዳል የነገሩንን ግን ደግሞ ነው ብለን ሳንቀበላቸው መጥፎም ነው ብለን ሳናወግዛቸው እንዲሁ ሆድ እንደባሳቸው እንደ ጥላ ያልፋሉ። በሆነ ዘመን ላይ እንደ አንድ የታሪክ ዘበዝ መዝዞ ለመበሻሸቂያ ወይም ለአጉል ጉራ ብቻ በስማቸው ከማነብነብ ውጭ የያዙትን የሃሳብ ደርዝ እየተነተንን ለመተርጎም አንታትርም። በሃይማኖት አስተምህሮ በኩል ያለችዋን መንገድ ብቻ በአንዳንድ ደገኛ ተቆርቋሪዎች ፈሩን ለማስያዝ እንጣጣራለን። ለዚህም ይሆናል ባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ ለሙዚቃ ባለሙያው አበበ ብርሃኔ በሰጠው “መገና” ግጥም ላይ እንዲህ የሚተክዘው። መላና ባላውን አጣነው ፈልገን ……………….. እያለ የሚቀጥል ከዘመናት አርምሞና መብሰልሰል በኋላ የተቀዳ ጸአዳ የህይወት ማይ ነው። የባለቅኔውን ስም ካነሳነው ወደ ዋናው ጉዳያችን እንግባ። ይሄ የመዘንጋትና እንደ ብላሽ የመታየት እጣ ከደረሳቸው እንቁ የሃገራችን ባለቅኔዎች መካከል እዚሁ ቅርባችን ሙሉጌታ ተስፋዬ በ1946 ዓም ወልዲያ ተወልዶ በ1996 ዓም እዚህ ዓለምገና ያረፈ በሃምሳ ዐመቱ የተለየን እጹብ ድንቅ ባለቅኔ ነው። ከሩቅ ሳንሄድ ለሙዚቀኞች የሰጣቸውን የዘፈን ግጥሞች ብቻ በወፍ በረር ብንመለከት የሰውዬውን ግዝፈት እንረዳለን። ከድምጻዊ አበበ ተካ ወፍዬ እስከ ድምጻዊ ሃና ሽንቁጤ “ሆዴ ባለ አብሾ”፣ ከአበበ ብርሃኔ “መገና” እስከ ድምጻዊ ታምራት ደስታ “ሐኪሜ ነሽ”፣ ከድምጻዊ ጃን ስዩም “ጋሜው” እስከ ድምጻዊ ብጽዓት ዛሬአችንን እንደ ፈርጥ አድምቀውታል። ከዚያ ከፍ ከአነጋገር ይፈረዳል በሚል ተረት ውስጥ ስንት እውነት አወይ መገን እኔ፣ አወይ እኔ መገን፣ እንዲህ ሩቅ ነው ወይ፣ አጥቢያና ወጋገን? ይቸግራል ለካ፣ ሃገር ይዞ ወገን የነበረው ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ) ነው ። ባለቅኔ
ጆሮ ዳባ! ለባለቅኔ? 8 ስዩም “አደራ ልጄን” የተሰኙ የዘፈን ግጥሞችን ብቻ በዓይነ ልቡና መመልከት ይበቃል። ከተራ ሊስትሮነት ተነስቶ እስከ ኢህአዴግ ጉምቱ ሰው መሆን የቻለ፣ በአኗኗር ዘይቤውና በዓለም እየኖረ ለዓለም ባለው ብላሽ አተያይ በብዙዎች ዘንድ እንደ ኢምንት ተቆጥሮ ያለፈ ሆደ ቡቡ ነው። ቅኔ እንደ ዥረት የሚቀዳለት ከአማልክቱ አንዳች ውል ያለው የሚመስል ብሎ የሚመለከተው ሲያጣ ተመልሶ ድርግም ያለ ታላቅ ዓይናፋር የምስራቅ ኮከብ ነበር። እንዲሁ ከባለቅኔው ጋር መተዋወቂያ ወይም ማስታወሻ ይሆነን ዘንድ በዘመኑ ከጻፋቸው ግጥሞች ውስጥ አንዱን በወፍ በረር ለማየት እሞክራለሁ። የግጥሙ ርእስ “የማረሻው ሹም ሽር” ይሰኛል። የተጻፈው በ1987 ዓመተ ምህረት ነው። በእኔ የመረዳት መጠን አያ ሙሌ ከጻፋቸው ግጥሞች ውስጥ ለእኔ ዋና ስራው ይሄ ነው ብዬ አምናለሁ። ረጅም የሚባል ግጥም ነው። በቃላት ውበቱም ይሁን በሙዚቃዊ ስልቱ አንዳች መንፈስ በልቡና ያሰርጻል። ጮኽ ብለው ሲያነብቡት ከትናጋ ላይ እየፈለቁ ወደ ህዋው የሚወረወሩ ቃላት የልብን አታሞ እየደለቁ ሲዘረገፉ ይሰማሉ። በመሃሉ የሚሸመነው የዘመን መልክና ህመም ያስናፍቃል። በ 302 ስንኞች የተቀነበበውን ግጥም ለሶስት ዐበይት ከፍሎች ከፍዬ ለመመልከት እሞክራለሁ። እነዚህን ሃሳባዊ ሶስት ክፍሎች ወይም መደቦችም ሀሌታ፣ እግዚኦታ እና አንድምታ ብዬ ሰይሜአቸዋለሁ። እስኪ ገረፍ ገረፍ እያደረግን ለማየት እንሞክር። ግጥሙ እንዲህ ይጀምራል። የማረሻው ሹም ሽር ዳብሬ---- በሬ ምንህ ክፉ”። የግጥሙ ጥልቅ ሃሳብ ከርእሱ ይጀምራል። የሃገራችንን የፖለቲካም ይሁን የስተዳደር ሁናቴ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስንመለከተው የሚሾም የሚሻረው ማረሻው ነው። የጠጠረው መሬት ይበረጋገስ ዘንድ በትክሻው ቀንበር ይዞ እየገፋ ሲጓዝ የሚውለው በሬ ከቁጥር አይገባም። ለዚህም ነው ባለቅኔው በሬ ምንህ ክፉ የሚለው፣ በሬ የሃገራችንን ሕዝብ ይወክላል። በባዶ ሆዱ በተጣጋ ጎኑ ቀንበር ሲስብ የሚውል በሬ እንዲሁም ከኋላ እርፍ ይዞ ልማም ያጠማረረው ገበሬ ከቁጥር ሳይገባ በሃገራችን ፖለቲካ ግን የሚሾም የሚሻረው ማረሻው ብቻ ነው። ብረት ነው። ውልና ህልሙን እንግዲህ የቀጠቀጠው ባለ ርዕዮተ ዓለም ያውቀዋል እንጂ። ከቤት ቢገቡ በበሬ ትክሻ ታርሶ በተመረተ እህል የተደፈደፍ ግሩም ጠላ ይገኛል። ከጓሮም ቢሄዱ ለማገዶ የሚሆን የበሬ በረከት አለ። ወደ ሃገራችንም ሲመለከቱ ይሄን ያገኛሉ። ይሄ ባለታሪክ ህዝብ ባህሉን፣ ቋንቋውን፣ እምነቱን፣ አኗኗሩን ሁሉን ሰንዶ የተጣራ የታሪክ ዘመራ ጠላ አቆይቷል። ዙሪያ ደጀኑን ቢመለከቱም ለማገዶ የሚማገድ አሁን ድረስ ለእናት ሃገሩ ለመሰዋት የተሰደረ ህያው ሰውነትን ያገኛሉ። ይህ አይደል ታዲያ ባላገርነት? ሀሌታ ባለቅኔው የበሬ (ለህዝብ) ያለውን ምስጋና እና ውለታ እንዲህ በቅኔ እያመሰጠረው ይወርዳል። በርዬ ብሩዬ ሆሆ-- ሆሆ አያ በሬው ዳብሬ ይለዋል። ዛሬ ከዓለም ፊት ስንቆም ማንም መሳቂያ መልክ እንዲመለክት የምናደርገው በአባቶቻችን ትክሻ ላይ ነው። ክብርና ሞገሳችን እነሱ ናቸው። ለሚያየን ላንለያይ አንድ ሆነን የተገመድነው፣ ብንናቆር እንጂ ጨርሰን እንዳንቆራረጥ ተብትቦ የያዘን ስውር መረብ የእነሱ በረከት አይደለምን? ምንድን ነው የምንከፍለው ለእነዚህ ግሩማን አያቶቻችን ከአንዱ ሀሌታ ውጭ? ባለቅኔው ይቀጥላል--- እኔማ እኔውማ ልጅህ ከርታታ ኮከብ ነበር። ድንገር ዝም ባለ ዓለም ውስጥ ቦግ ውስጥን ያብሰከስካል። የሆነ ያልተደረሰበት ሰፊ ዓለምን “በሬ ምንህ ክፉ፣ ዳብሬ ምንህ ክፉ እጓዳ ቢገቡ፣ ይገኛል ድፍድፉ በጓሮም ቢዞሩ፣ ይገኛል ጥፍጥፉ ማረሻው ደግሞ በእሳት አንዳጅ አንጠረኛ የተቀጠቀጠ ስል እምዕንተ ውእቱ፣ እኔማ ባንተ ተከብሬ ቅርሽም፣ አነባብሬ ሶብሬ እኔማ-- የልቤ ደርሶ፣ ሰብሬ--- ነብሬ የማያደርገው ፣ ወዶም ይሁን ተገዶ የታሪካችንን ግዙፍ ጥሬው ትሬ ፈጅህ፣ መደቆሻ መጅህ እኔማ--- በንተ ደርጅቼ፣ አደይ ለምለም፣ ባለም በጅቼ እኔማ--- ባንተ ቆረንጮ በነዳሌ ቦራ፣ ያደራ ጮጮ ጡቱን ጡቱን ተብዬ፣ በእንኮኮ ተቀማጥዬ
ጆሮ ዳባ! ለባለቅኔ? 9 እኔውማ ልጅህ ጥሬው ጥሬ ፈጅሕ እያለ ከአባቱ ጋር በንጽጽር ራሱን ይወቅሳል። ራሱን በመውቀስ ውስጥ ደግሞ የአባቱን ከፍታ እንደ አርማ ሰቅሎ በሃሌታ ያደባልቀዋል። የአባቶቹን ዣት ያልካደ ዛሬ ለቆመበት መሰረት የትናንቱን የተገነዘበ የአሰላሳይ መወድስ እንዲህ አይደለምን? እድሜ ላንተ አያ ዳብሬ- እድሜ ላንተ አይያ ዋለ ብሎ ይጠይቃል። እውነት ግን እንደ ህዝብ ወይም እንደ ሃገር ቀደምቶቹ ለእኛ ምን ያልሆኑልን አለ? አድረን ጥጃ ብቻ የበዛበት ጉጻጉጻም ጎዳና ነውን? በባለቅኔው ምናብ ግን ትርጓሜው ሌላ ነው። የዚህ ሁሉ ቅርሻም የዘመን መልክ የአባቶቻችን መንገድ ባለመከተላችን ነው የሚል ይምስላል። ግን እውነት አለው? አባቶቻችን ለእኛ ምን ያልሆኑልን አለ? እንደ በሬ ተለጉመው አልተነዱልንም? እንደ በሬ ታርደው አልተበሉም? በዱር በገደሉ፣ በየፈፋው በጉድባው፣ በጋራው በሸንተረሩ፣ በወንዙ በሃሩሩ እየተመተሩ አልረገፉምን? እውነት ሌት በጨለማ ቀን በዋይ እየተንገበገቡ ሃገር አላቆዩንም? የዘመናትን የውጭ ባላንጣዎች ጉሰማ እየመለሱ ሽፍን አድርገው እንደ በቆሎ ዘር አላቆዩንም? ታዲያ ከእነሱ አንጻር እኛ ምንድን ነን? አድሮ ጥጃ አድሮ ፈንጣዥ የትናንት ሞትና መብከንከን የማይሰማን ከንቱ መደዴዎች አይደለንምን? የሚል መንፈስ ያለው ነው። ይቀጥላል በሃሌታው---- ዛሬ ዛሬ ዓይንን ስልጣን እየሸበበው ክራሞታችን ሁሉ በሞት የታጀበ ነው። ከየት እንደመጣ የማናውቀው የሞት መንፈስ በሁላችን ልቡና ገብቶ ጉንዳን እንዳተራመሰው የፈረስ መንጋ ሽቅብ እያስኮበኮበን ነው። ግን ግን እውነት አለን። የሞትና የጭቅቅት ታሪክ አይደለም ቀደምቶቹ በታተመው ህያው ጽላት እንመሰክራለን። እኔማ እንቁላሏን የትም የምትጥል የበሬ ገበሬ ልክ አይጠፋን። እንዲህ እያለ ሀሌታውን ያወርደዋል። ሁሉም በሃገር ላይ ነው ይባላል። እኛም ትናንትና በተደላደረው ርብራብ ላይ እንደ ቆላ ገራዱ ስንቀማጠል ለሚያየንም እናስቀናለን። ምን አነሰን? እግዚኦታ ባለቅኔው እንዲህ እንዲህ እያለ ሃሌታውን ሲያወርደው ይቆይና በዘመኑ የነበረውን አሁናዊ ማንነት ይታዘበዋል። መከረኛ ነፍሱ ማቃሰት ትጀምራለች። ቃላትም ፈራቸውን ሳይለቅ ከልቡናው ዲብ እየተሹለከለኩ አንዳች ሚስጥር ይዘው ይነሰነሳሉ። ብቻ ዛሬ ብሎ ይጀምረዋል። ፍዳዬን የኋሊት ጥዬ፣ ዳብርዬ ብሩ ብርዬ እድሜ ለአንተ እኔማ፣ ወልጄ ስሜ -ከርሜ ቀሰም ዘርቼ፣ ቅሜ--- እንዳቅሜ አድሮ ጥጃ ሆንሁብህ፣ እንጂ ለእኔማ ለእኔ ላንተ እኝደራሴ ምስለኔ፣ ለእኔማ ለእኔ፣ ምን ያልሆንህልኝ አለ? የሆንነው እኛ እንጂ እውን የቀደምቶቹ መንገድ ህጸጽ እርካብና መጣብር፣ ለጊዜው ቢያጥበረብር ዓይን ሸብቦ ምላስ ቢያስገብር--- ማን እንደ ነፍስ ክብር? ማን እንደ ልብ፣ ድልብ ግብር? በልብ ጽላት፣ በደም ሙላት፣ የለቆጧት እውነታ ተግባር ላይ፣ ፈራ ተባ፣ ብትል ለለቱ ለመድፈር እንኳን፣ ብታመነታ እውነት የማታ ማታ፣ ግንባሯ መች ይታጠፋል እውነት የማታ ማታ፣ ክንዷ መች ይዘነጠፋል ያወረሱን። የምናፍርበትን ሳይሆን የምንከብርበትን ነው የተቀበልነው። እሱ ከልባችን ከታተመ ማን ፈቀቅ ያደርገዋል? ከልባችን ደግሞ አናፈገፍግም። በልባችን ላይ እድሜ ላንተ አይያ፣ እድሜ ላንተ---ምን ጎድሎብኝ ምን ጎድሎባት ነፍሴማ፣ ወፌ ዘራፌ ዋነሴማ ዘርፌ አክናፌ፣ የቆላ ገራዶ ቅምጥል አንተን አምና ተለማምና፣ የሳር ጎጆ ቀልሳ እኔና እሷማ ምን ሊከፋን? ምን ጎደለብን? ምን አነሰን? ታሪክ? እውቀት? ባህል? ብዛ ዛሬ ሞይዘሬ፣ ብቻ ዛሬ፣ ልብ ስገዛ ስጎለምስ ዓይነ ጉልላት፣ ጉብል እክብል ላባብል
ጆሮ ዳባ! ለባለቅኔ? 10 ስሰበስብ ------------- ብሎ መንገብገቡን ይጀምራል። እድሜ እየገሰገሰ ማስተዋልም እየተነሰነሰ ሲመጣ የዘመኑን ህያው ገጸ ቅብ ማማተር ይጀመራል። ባለእጅ የጠፈጠፈችውን የማዕድ ማስቀመጫ ሙሆዶ መደርመስ ሲጀመር፣ ዘመናዊነት ወይም ሶሻሊዝም ወይም ካፒታሊዝም በሚሉት ርዕዮተ ዐለም ትውልድ መናጥ ሲጀምር ቆም ብሎ ማስተዋል ለሚገባው ብዙ ነገር ይመጣል። ሃገር ይሏት ህያው ስንቅ እንዴት እንደተከበረችና እንደቆየች መላና ባላው አልታይ ሲል ከእግዚኦታና ከእዬዬ ውጭ ምን ይባላል ይሆን? ይለዋል። የልብስ ገበር ለገላ እንደቀረበ ሁሉ የህዝብ እሮሮ የሚያበግነው የመረገጥና የመንገላታት ጭካኔ የሚያሳምመው ባለቅኔም እኔ ከላይኛው ጋር ምክር የለኝም እያለ ማንባቱ የአባት ነው። ከአንተ ነው ቅርበት ያለን ይለዋል። ህመምህን እታመመዋለሁ፣ ሞትህን እሞተዋለሁ፣ ታሪክህ ታሪኬ ነው፣ ደስታህ ደስታዬ ነው፣ ወዮታህም እንቅልፍ ያሳጣኛል ምን ላድርግልህ አባትዋ? የሚል የሰቀቀን ድምጸት ከልቡናችን ይፈልቃል። አዎ ያም ሆነ ይሄም ሆነ አንገት ቅልስ እየተደረገ ዲቁናና ክህነቱ በማረሻው ላይ ያንዣብባል። ክህነት የተጠመቀ ደግሞ መንፈሳዊ ስራው ሌሎችን በሃይማኖት ማጥመወቅ ነውና ከየትም በቃረመው ስርዓት ክህነት ወይም ርዕዮተ ዓለም አባት ዓለም ዳብሬን ማጥመቁን ይጀምራል። በሬ ሆዬ የሚያውቅ የሃገሩን ሰርዶ ነውና እንዴት ብሎ የማንንም ጨምዳዳ ልብሰ ተክህኖና አዲስ አስተምህሮ ይቀበል? እዚህ ጋ ነው እልህ ያንገበገበው መላ የሚፈጠረው። አንድምታ አባቶቻችን አንድን እውነት በሁሉም መንገድ ለማስረገጥ ሲሉ አንድምታ ይሉት አስረጂ አላቸው። ለየትኛውም ሚስጢር አንድምታ እንዲላላ ያደርገዋል። በማረሻው ሹም ሽር ውስጥም ሃሌታውም ሆነ እግዚኦታው በአንድምታ መጠናቀቁ አይቀርም። መላና ባላውን አጣነው ፈልገን ቢልም የነፍሱ መም ያመጣዋል ባለእጅ የተፈጠፈችውን፣ ሙሆዶ ስደረምስ አስብቼ ፣ቀጥቅጬ ልስብ በተለቅቶ አሳብ አራጣ፣ እጣ እጣ ስከስብ ዓይን በመግለጫዬ፣ ጎጆ በመውጫዬ፣ የሚስጥርህ ቋጠሮ፣ አልፈታ ብሎኝ በቁጭት እንባ ስዘግን፣ ይኸውልህ አያ ዳብሬ-- ይኸውልህ አለሁ፣ እንዳስቀመጥኸኝ አለሁ እንደፈጠርኸኝ፣ መሰሪ ያውሰለሰለውኝ፣ ጨምዳዳ አባ ምን ግዴ ጎዳዳ፣ ስፋ የሚለኝ ቀዳዳ አይያ- በምን እዳይት ልጣፈው? በምን ካሎስ በምን ክር? ገበር ነኝ እንጂ የውስጥ ልብስ፣ እኔ ከላይናው የለኝ ምክር አይያ--- የሆነውስ ሆነና፣ ክህነት ሊቀበል ነው፣ ድቁና አንገቱን ቁልቁል ቀልሶ፣ ድፍት የሚለው የእኛ ቤት ቁና። ያመላከተውን ግን ሹክ ከማለት አይቆጠብም። እንዲህ አይያ-- ዋንጫችን ጥቅል፣ ዘራችን ቅልቅል-- ደማችን እየቅል፣ ኑሯችን ምስቅልቅል፣ እዛና እዚህ፣ ነጋ ጠባ ፣ብን ብን ቢሆንብን ንፍገት ወንዝ ባያሻግርም፣ ቸርነት ብቻውን፣ ጸይም አሳ አያሰግርም ሁሉም ቢሆን ያለ ሰው፣ ተነፋነፍ ነው ብንዋሰው፣ እጀ ጠባብ ነው ብንለብሰው ብየ እንጂ የምነግርህ፣ እኔና አንተማ አንድ ነን፣ የምወድህ። ---
ጆሮ ዳባ! ለባለቅኔ? 11 አዎ ኢትዮጵያዊነት ክቡር ገመድ ነው። በዘመን ሰንሰለት ውስጥ አንዱ ከአንዱ እንዳይፈታ ተደርጎ ታስሯል። ይሄ አሌ የማይባል ሃቅ ነው። በዚህ ውስጥ ደግሞ አንዳች መንገድ ፍለጋ መዳከር አለ። ደግነት እየመሰለን ስንቱን የእኛ ያልሆነ ስርጣስርጥ መንገድ ጎበኘን። ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ እንደሚባለው ያለንን ወደ ገደል እየወረወርን ይጠቅማል ብለን ስንቱን መናኛ የሃሳብ መቼም አያደምቀንም። የሰው ወርቅ አያደምቅ ነውና ነገሩ ለራሳችን ችግር የራሳችን መላ አለን ይላል ባለቅኔው። መሬት ላራሹም ቢባል - አንጣራሽ መስሎ አጫራሽ ቆራሽ አሰፍስፏል ጎራሽ- ወፍ ዘራሽ የንጉሱን ቀጭን አገዛዝ ለመፈረካከስና አንዲት የበለጸገች ንቅናቄ ማንነታችንን እየደረመስን በደም አባላ ተላልቀን። መጨርሻ ላይ እጃችንን አጨብጭበን ቁጭ አልን። ከጳጳሱ የበለጠ ክርስቲያን እንዲሉ ህወሃትም ከደርግ የበለጥሁ ሶሻሊስት ነኝ ስትል ጉተናዋን ነስንሳ ወደ ዙፋን እንኳን ለመቆም ቸገረን። ይሄንን ነው አጫራሽ እያለ ባለቅኔው የሚገልጸው። በስጋ ሊያዛምዱህ? ይላል ምሉዕጌታ። አዎ ጥንተ ጠላታችን ጣሊያን በሁለተኛ የቂም በቀል እርኩሰቷ፣ በመርዝ ጭስ ማንገብገቧ ሳያንስ አንዱ በአንዱ ይነሳ ዘንድ በዘር ልታቧድነን ፈለገች። በጊዜው አልሳካ ቢልም ተማርን በሚሉ ሃሳውያን ተቀንቅኖ በህወሃት መንግስት ስርዓት ሆኖ መጣ። ይሄ ግጥም የተጻፈበት ወቅት 1987 ዓም ነበርና ባለቅኔውም ይሄንን ነበር የሚቃዎም። በስጋ አትዛመድ፣ አንድ የሰው ልጅ ነህ፣ ነገ ፍሬው የከፋ ይሆናል እያለ መንገዱን ሲያሳየን ነበር። ግን ዓይን እያለን አላየንም፣ ጆሮ እያለን አልሰማንም። ብሎ ነዋ እንቅጩን የሚናገረው። ባለቅኔ አይፈራም። በረድፉ ሳያስቀምጥ አይልመጠመጥም። ትናንትና ንጉሱን ገርስሰሃል። ያሰብኸው ግን አልመጣም። ዛሬም ደርግን አስወግደሃል። የፈለግኸው ግን አልመጣም። አሁንም መንበሩን እየተቆናጠጠ ያለው የህወሃት አገዛዝ በስጋ እያቧደነህ ነውና አልገዛም በል አሁንም ሲለን ነበር። በመጨረሻም ወትሮም ቢሆን የኮሶ - ልጅ ታውቅ የለ እንዴ አብሽር የእኔ ምንሽር! (ላባት ዓለም ዳብሬ ጥቅምት 1987 ዓም አዲስ አበባ) ብሎ ይጨርሳል። ባለቅኔው በጊዜው ያለውን አማራጭ ተናግሮ ነበር። በሰዓቱ መምረር እንዳለብን እየመጣ ያለው አገዛዝ የባሰ መቀመቅ እንደሚከተን፣ በዘር መቧደኑ የማታ ማታ ሞት እንደሆነ በባለቅኔ ራዕይ እየተመለከተ ዘከዘከልን። እሱም አልቀረ መላውን አብሮ እንካችሁ አለን። እኛ ግን በዝምታ አለፍነው። ለ30 ዓመታት ብዙ እንክርዳዶች ተፈጠሩ። በእርስ በእርስ መነቋቆር ብዙ የጋራ ድሎችን ሳይቀር አቅላቸውን አሳጣነው። ሰዎች በጅምላ ረገፉ። የሞት ዜና ቤታችንን ሞላው። ይሆው ከዘመናት በኋላ ቀየርነው ብለን ፎከረን። ግን የእፉኝት ልጅ እፉኝት ነውና የሚሆነው ከዚያ የህመም መርግ አላመለጥንም። ከመጀመሪያ እንደ ህዝብ የባለቅኔዎቻችንን ምክርና ሃሳብ ለመስማት ዳተኞች ነን ያልሁት ይሄንን ነበር። ይሄንን ግጥም እንደ ምሳሌ ወሰድን እንጂ ብዙ ጸሐፍት እንዲሁም ባለቅኔዎች ራሱ አያ ሙሌም በተለያዩ ግጥሞቹ መሰል ጉዳዮችን አንስቷል። ግን ከአስተውሎት ይልቅ ስሜት እየነዳን ቆም ብለን ለማሰብ እድል አጣን። ይሄው ሁሉን እያየነው ከዚያው አዙሪት አልወጣንም። ጌታ ሆይ እባክህ እዝነ ባለቅኔ አድለን እያልን እንጸልይ ይሆን? ወይስ በከያኒውና በተደራሲው መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት መጣር? ቸር ያድርገን! ድሪቶ ጎዘጎዝነው። ምንም ቢሆን ምን በልካችን ያልተሰፋ ሀገር ለመመስረት በሚል የልጆች እቃ እቃ የሚመስል ተንጠረበበች። እርስ በእርስ ተበታተንንና እንደ ግለሰብ እኮ ዘንድሮም ሊጠምዱህ? ትንሽ ስጋ፣ እንደ መርፌ ትወጋ፣ ብለው ለማንም እብቅ ገለባ፣ ሰለባ ሁነህ ከምታነባ፣ አልገዛም በል አሁንም፣ አሻፈረኝ በል እንደገና በሱ እጅ ከመደርደር፣ እንደሁዳዴ በገና በለቅኔ አያቅማማም። የተገለጠለትን የሃሳብ ዘለበት እና- የኔ ጌታ፣ የእኔ ምንሽር አለሁ እኔም፣ ከጎንህ ነኝ አብሽር ያለ ኮሶ እንደማይሽር? ምረር! የማረሻው ሹም ሽር
ስለ አንቺ 1 2 ስለ አንቺ በህሊና እንዳለ በስላንቺ አምዳችን ላይ ማንኛውም የሴቶችን ጤና የሚመለከት ጉዳይ ይዳሰሳል። ለመሆኑ ሴቶች በፈቃዳቸው ፅንስ ማስወረድን የኢትዮጵያ ህግ ይፈቅዳል? ስለፅንስ ማቋረጥ (ውርጃ)የህክምና እና የህግ ባለሙያዎች ምን ይላሉ? ምን አስተያየትስ አላቸው? የፅንስ ማቋረጥ ምንነት (Photo: Rahul Gupta) ውርጃ(ፅንስ ማቋረጥ)የምንለው ፅንስ ከተፈጠረ እስከ 28 ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ፅንሱ ከተቋረጠ ነው፣ የዓለም የጤና ሚንስቴር በጥቅሉ ውርጃን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ደህንነቱ ያልተጠበቀ በማለት በሁለት ይከፍለዋል። ደህንነቱ የተጠበቀ ውርጃ እውቀት ባለው ባለሙያ፣ ንፅህናው በተጠበቀ መሳሪያና ቦታ፣ በቂ የህክምና መሳሪያ ባለበት የሚሰራ ሲሆን ደህንነቱ ያልተጠበቀ ውርጃ ማለት ደግሞ እነዚህን ነገሮች የማያሟላ ውርጃ ነው። በሌላ መልኩ የፅንስ መቋረጥ በራሱ ጊዜ የሚከሰት እና በፍላጎት በባለሙያ የሚሰራ ተብሎም ይከፈላል። አንዲት ሴት በፈቃዷ ፅንሱ እንዲቋረጥ ከፈለገች በሁለት አይነት መንገድ ሊሰራላት ይችላል። እነዚህም በአፍ የሚወሰድ መድሀኒት በመጠቀም ወይም በማህፀን በሚገባ መሳሪያ በመጠቀም ነው። በመድሀኒት ፅንስን ለማቋረጥ የፅንሱ እድሜ እንደ ጤና ተቋሙ ቢለያይም በከፍተኛ ጤና ተቋማት እስከ 28 ሳምንት ድረስ ያለ ፅንስ በመድሀኒት ሊቋረጥ ይችላል። በቀላል ቀዶ ጥገና ወይም በመጠረግ ጽንሷን ለማቋረጥ የምትመርጥ ሴት የፅንሱ እድሜ እስከ 24 ሳምንት መሆን አለበት። በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ቅድስት ደህንነቱ የተጠበቀ ህጋዊ ውርጃ ብዙ ሴቶች አገልግሎቱን አግባብ በሆነ ቦታ እንዲያገኙ መደረጉ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ውርጃን እንደሚቀንስ ያስቀመጡ ሲሆን ከውርጃ በኋላ የበዛ ደም መፍሰስ፣ ከፍ ያለ ትኩሳት፣ እንዲሁም መጥፎ ጠረን ያለው ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ካለ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ እንደሚያስፈልግም አክለው ተናግረዋል። ፅንስ ማቋረጥና መካንነት በተለምዶ እንደሚባለው ፅንስ ማቋረጥ መካንነትን አያመጣም። ነገር ግን በቀዶ ጥገና የፅንስ ማቋረጥ ከተጠቀሙ ሴቶች ላይ 1.6% ወይም ከመቶ ሴቶች 1.6 ሴቶች ላይ የማህፀን ጠባሳ በመፍጠር የቀጣይ የማርገዝ እድል እንዳይኖር ያደርጋል። ይህ የማህፀን ጠባሳ ተደጋጋሚ ውርጃ እና የማህፀን ቀዶ ጥገና የምታደርግ ሴት ላይ ይጎላል። የኢትዮጵያ ህግ ደህንነቱ የተጠበቀ ውርጃን እንዴት ይደነግገዋል? የፅንስ ማቋረጥን የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 551 እንደሚደነግገው በህክምና ባለሙያ በተፈቀደ የጊዜ ገደብ እንዲሁም በህክምና ተቋማት ውስጥ ፅንስ ሲቋረጥ በወንጀል የማያስቀጣባቸው ሁኔታዎች አሉ። እነሱም የሚከተሉት ናቸው። 1. በአስገድዶ መድፈር ወይም በዘመድ መካከል በተደረገ የግብረስጋ ግንኙነት የተጸነሰ ከሆነ 2. ላይ ጉዳት ካለው 3. ፅንሱ የአፈጣጠር ችግር ካለበት 4. ያለባት ከሆነች ወይም ለአካለ መጠን ያልደረሰች በመሆኗ ምክንያት ሊወለድ የሚችለውን ህፃን ለማሳደግ የወሊደም ሆነ የአካል ዝግጅት የሌላት ከሆነ ናቸው። ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያች ፅንስ ለማቋረጥ ሴትዮዋ መደፈሯን ወይም ከቤተሰብ መጸነሱን ማረጋገጥ ሳይጠበቅባት ቃሏል መስጠት ብቻ በቂ ነው። ይህንን መመሪያ ጥሶ የተገኘ ከአንድ ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከሶስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል። ዳሩ ግን ህጉ ይህንን ቢያስቀምጥም የጤና ተቋማት ከእነዚህ ውጭ በሆነ ምክንያት ፅንሱን ላልፈለገች ሴት አገልግሎቱን ሲሰጡ ይስተዋላል። በርግጥም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ውርጃ እንዳይፈፀም ህጉ ከፊቱ መላላቱ ዋነኛው ምክንያት ሆኗል፣ ኢትዮጵያ ሀይማኖቷና ባህሏም ውርጃን የሚቃወም በመሆኑ ያልተፈለገ እርግዝና የገጠማት ሴት አገልግሎቱን ለማግኘት ስትሳቀቅ ይስተዋላል። ይሄን እና መሰል ጉዳዮች በነጻነት የማይወራባቸው በመሆናቸው የማህበረሰባችን እውቀትም አናሳ ነው። ሴት ልጅ መብቷን ልትጠቀም እንዲሁም ወንድ ልጅም በፅንስና ውርጃ ላይ እኩል ሀላፊነት ሊሰማው ይገባል። በራሱ ጊዜ የሚገጥም ውርጃ ውርጃ በራሱ ጊዜ ተፈጠረ የምንለው ፅንስ ከ 28 ነው።ለዚህም የአፈጣጠር ችግር መኖር፣የእናት የማህፀን ዓመት በላይ መሆን ሲጋራ ማጨስ፣ የተደጋገመ ውርጃ እንዲሁም አልኮል ችግሩን ሊያባብሱት ይችላሉ። ምልክቶቹም የዳሌ ህመም፣ከማህፀን የሚፈስ ደም፣ከማህፀን የሚወጣ ስጋ መሰል ነገር ናቸው። ማህፀን ላይ የቀረ የፅንስ አካል ካለ ማስወጣት፣ ብግነት ወይም ኢንፌክሽን እንዳይኖር መከላከል እና የህመም ማስታገሻወች ተጠቃሽ ናቸው። እንደ ማጠቃለያ አንቺ የማህበረሰቡ አንድ አካል ነሽና ስለጤናሽ ማወቅ ይገባሻል አንተም የሴት አካል ነህና ሴት ልጅ በባህል ተከልላ ህይወቷን እንዳታጣ ልታግዛት ይገባል። የእርግዝናው መቀጠል በእናት ህይወት እና ጤና እንዲሁም እናት የአካል ወይም የአእምሮ ጉድለት ሳምንት በታች ያለ እናት ፈቃድ በራሱ ጊዜ ሲወርድ ጉዳት፣እንደምክንያት ሲጠቀስ የእናት እድሜ ከ35 ለዚህ ችግር ህክምናዎቹ እንደ ውርጃው አይነት ቢለያዩም
ውበት 13 ውበት አያስፈልገውም ውበት የሰው ልጆችን ለዘመናት ሲማርክ የቆየ ጽንሰ ሃሳብ ሲሆን ትርጉሙም በታሪክ ውስጥ ይገኛል። ለተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን ሊያመለክት ስለሚችል የውበት ትርጓሜም አብሮ ሊለያይ ይችላል። የተለያዩ ባህሎች እና ማህበረሰቦች በሥነ-ጥበባቸው እና በሥነ-ጽሑፎቻቸው ውስጥ የሚንፀባረቁ ልዩ ልዩ የውበት ጽንሰ-ሀሳቦችን አዳብረዋል። እንደ ቬኑስ ደ ሚሎ (Venus de Milo) ባሉ ቅርጻ ቅርጾች ከተገለጸው የጥንቶቹ ግሪኮች አድናቆት ጀምሮ እስከ ህዳሴ ሰዓሊያን በተመጣጣኝ መጠን እና ሚዛን ላይ ካደረጉት ትኩረት በመነሳት ውበት የሰው ልጅ የጥበብ አገላለጽ ዋነኛ አካል ነው። ዛሬ፣ ውበት ብዙውን ጊዜ የስልጣን ወይም የደረጃ ነጸብራቅ ሆኖ ይታያል፤ነገ ደግሞ ምናልባት የተለየ ትርጉም ይኖረው ይሆናል። Photo: Maurizio Bolognini. Museo Tattile Statale Omero Archive. ስለ ውበት ስናወራ በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ሰው ስለ ውበት ምንነት ያለው አመለካከት ተጨባጭ መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። በመሰረቱ፣ ውበት ለአንድ ሰው ስሜትን ፣ ደስታን ወይም እርካታን የሚያመጣ ነገር ነው። ውበት በሚያምር ሁኔታ ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን ከማድነቅ የተገኘ ስለሚሆንም ጭምር ነው። ይሄም እንደ የፊት ገጽታዎች ወይም የሰውነት ቅርጽ ያሉ አካላዊ ባህሪያትን ፣ የቀለም መርሃግብሮች ፣ ሲሜትሪ ወይም ሌሎች የጥበብ አገላለጾች ያሉ የእይታ ውበት; ወይም እንደ ፍቅር ፣ፍትህ ያሉ ረቂቅ ፅንሰ ሀሳቦችን ያጠቃልላል። እያንዳንዱ ሰው እንደ ምርጫው እና ልምዱ በባህሎች እና በጊዜ ውበትን የሚገልጽበት የራሱ መንገድ የውበት ጽንሰ-ሐሳብ ከጥንት ጀምሮ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሰረጸ ነው። እንደ ፕላቶ ባሉ የክላሲካል ጸሃፊዎች የተገለጹት ማጣቀሻዎች እንኳን ዓለም አቀፋዊ የውበት መመዘኛዎችን አልፈዋል ብሎ ያምን ከነበረው አካላዊ መጠን አንፃር ፍጽምናን ያብራራሉ - ይህ ውስጣዊ ሙላትን ለማግኘት አልፎ ተርፎም ዘላለማዊነትን ለማግኘት ቁልፍ ተደርጎ ይታይ ነበር። በአካላዊ ውበት ላይ በማህበራዊ ደረጃ የተገነቡ ሀሳቦችን ማሰራጨቱ እስከ ዘመናዊው ቀን ድረስ ቀጥሏል። በተለይም ሴቶች እንደ ቆንጆ ለመቆጠር ከእውነታው የራቁ የሰውነት እሳቤዎችን እንዲጠብቁ ከሚጠበቀው አንጻር በከባድ ሁኔታ በማለፍ ላይ ይገኛሉ (ጊለን 2020)። በግላችን ማራኪ ሆኖ ያገኘነውን ነገር የሚገልጽ የተፈጥሮ አካል እንዳለ፣ የህብረተሰብ ተጽእኖዎች ስለ ውበት ያለንን አስተያየት ሊቀርጹ እንደሚችሉ እና ሊናቁ ወይም ሊናቁ እንደማይገባቸው ማስታወስ አለብን። ምክንያቱም ስለ ውበት ሁሉን አቀፍ የሆነ “ትክክለኛ” ትርጉም ስለሌለ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ራስን ለተፈጥሮ ድንቅ ነገሮች ማጋለጥ አዎንታዊ ስሜቶችን ያነሳሳል። በተመሳሳይ መልኩ ሙዚቃ ከተሻሻለ የማተኮር እና የማበረታቻ ደረጃዎች ጋር የተቆራኘው በሚያረጋጋ ቅንብር አወቃቀሩ ምክንያት ነው። እነዚህ በውበት እና በውበት የሚሳተፉበት መንገዶች ግለሰቦች የህይወት ፈተናዎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲቋቋሙ ሊረዷቸው እንዲሁም ለግል ደስታ ብቻ የሚውሉ ጊዜያትን በመስጠት - ከስራ እና ከስራ ጋር በተያያዙ ግቦች ከሌሎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች እራሳቸውን እውቅና የሚሰጡባቸው መንገዶች ናቸው። አንዳንድ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ቀኑን ሙሉ በትንንሽ ተድላዎች መደሰት አንድ ሰው በሕልው ውስጥ ሚዛኑን እንዲጠብቅ የሚረዳው እንዴት እንደሆነ ይጠቁማሉ። በፀጋዓለም ዳኜ አለው። ራስን ማስዋብ የግድ ጥብቅ ህግ
ውበት 14 አንዳንዶች ውበት ዘላለማዊው ስጦታ ነው ሲሉ ይደመጣሉ። ምንም አይነት ወቅታዊ ፋሽን እና አዝማሚያዎች ቢኖሩም፣ ምንም ይሁን ምን ውበት ሁል ጊዜ የተከበረ እና የሚደነቅ የመሆኑ እውነታ መካድ አይቻልም። በዓለም ዙሪያ ያሉ ፈጣሪዎች ምንነቱን ለመያዝ ሲሞክሩ በሥዕሎች፣ በቅርጻ ቅርጾች እና በስነ-ጽሑፍ የማይሞት ሆኖ ለዘለዓለም ይኖራል። ለዚህም ሞናሊዛ ምስክር ናት ።ውበት ውበት ብቻ አይደለም። በትጋት እና በትጋት ሊገኝ የሚችል ምልክት ነው። በተወሰነ ደረጃ ውበት ስለራሳችን ማንነታችንን ከዓለም ጋር እንድናካፍልም ብርታት እና በራስ መተማመን ይሰጠናል። በታሪክ ውስጥ፣ ቀለም-አልባ ምስሎች ከሁሉም የዓለም ማዕዘናት ውበትን በተመለከተ የተለያዩ ትርጓሜዎችን ማስተዋልን ሰጥተውናል። እነዚህ ክፍሎች አንዳንድ ባህሎች ፍጽምናን እንዴት እንደሚመለከቱ እና እነዚህ ግንዛቤዎች በጊዜ ሂደት እንዴት እንደሚሻሻሉ እንድንመለከት ያስችሉናል። ለምሳሌ ከሶስት መቶ ዓመታት በፊት ፋሽን ናቸው ተብለው የሚታሰቡ መቀናጫዎች ከዛሬው በእጅጉ ይለያሉ። እነዚህ የውበት መገለጫዎች በኪነጥበብ ውስጥ ፈጠራን ለማነሳሳት ጠቃሚ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ ። ለምሳሌ ድርሰት ፣ቲያትር፣ድራማ ፣ስዕል ወዘተ... እንደነዚህ ያሉ ምሳሌዎችን ስንመለከት፣ ከእይታ ማራኪነት እጅግ የሚበልጡ ብዙ ሌሎች ውስጣዊ ባህሪያት እንዳሉና በውጫዊ ገጽታ ላይ ለምን ትኩረት እንደምንሰጥ ከማሰብ ይልቅ በህብረተሰቡ ዘንድ አድናቆትን ይፈጥራሉ። ብልህነት፣ ድፍረት፣ ርህራሄ እና ደግነት ያሉ የባህርይ ባህሪያት እንዲሁ ተፈላጊ ነው ተብሎ ለሚታሰበው ነገር አስተዋፅዖ ያደርጋሉ። በደንብ ተጠንተው ይሁን ሳይጠኑ ከውጫዊው ውበታችን በላይ ለውስጣዊው ውበታችን ዋጋ የሚሰጡ አባባሎች እንመልከት 1. ”ውበት ይጠፋል መልካም ልብ ግን ለዘላለም ይኖራል።” 2. “ በጎነት የሌለበት ውበት እርግማን ነው.” 3. “ከመልካም ልብ ውበት የበለጠ የሚያበራ ውበት የለም።” 4. ”የጥበብ ውበት ከአጭር ጊዜ ህይወት ይበልጣል እናም ዘላለማዊነትን እና ጊዜን ያስራል.” 5. “በዓለም ላይ በጣም ቆንጆው ነገር ማየት የማትችለው ነገር ነው፤ አስተዋይ ልብ እና ደግ ነፍስ” 6. “በተመልካቹ ዓይን ውስጥ ያለ ውበት ከሌሎች የውበት ዓይነቶች ፈጽሞ ሊመጣጠን አይችልም.” 7. “ከእያንዳንዱ አካላዊ ውበት በታች ትልቅ ውበት አለ!” 8. “የአንድ ሰው እውነተኛ ውበት ከመልካቸው ባሻገር በነፍሱ ውስጥ ሊገኝ ይችላል.” 9. “ቆንጆ ቃላት ሁልጊዜ እውነት አይደሉም, ቆንጆ ፊቶች ሁልጊዜ ደግ አይደሉም ነገር ግን በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ ባለው ደካማ ውክልና ምክንያት ይህ እንደዛ ያልሆነ ይመስላል ።በተጨማሪም በውበት ላይ ፍቺዎችን መስጠት ሰዎች አሉታዊ የሰውነት ምስል ጉዳዮችን ወደሚያበረታቱ ጎዳናዎች እንደሚመራቸው ማስተዋል አለብን። በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ እርምጃዎች በመንግስት ባለስልጣናት ካልተወሰዱ ወይም በመዝናኛ ኢንዱስትሪ ውስጥ ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች ትኩረት ካልሰጡት ይህ በሚያሳዝን ሁኔታ ቁጥጥር ሳይደረግበት ይቀጥላል ። እኛን በጋራ በይበልጥ ወደ ክፍት አስተሳሰብ ለመምራት ሁሉም የልዩነት ዓይነቶች በህብረተሰቡ ውስጥ መያዛቸው አስፈላጊ ነው። አስተዳደግ እና እምነት ቢኖራቸውም ድጋፍ እንዲሰማቸው የመቀበል ስሜት እንዲኖራቸውና ውበትን የማያዳላ አመለካከት ማድረግ ይቻላል። ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል። እውነተኛ ስለዚህም የሁሉም ሰው ልዩ ባሕርያት ምንም አይነት ማድረግ ትክክል ነው ፤ከዚያ በኋላ ግለሰቦች ራሳቸውን
የፊልም አከራዩ የፍቅር ደብዳቤ 15 በመቅደላዊት አሰፋ ሔርሜላ የፍቅር abcdን የጀመርኩት ባንቺ ነው፡፡ የኔ ውድ ከዛ ከተለየሽኝ ቀን ጀምሮ ግራና ቀኙ ጥቁርና ነጩን መለየት ተስኖኛል፡፡ ልቤ ከደመና በላይ እየተንሳፈፈች ማረፊያ ያጣቸው ወፍ ሆናልሻለች፡፡ ባለቀለም ህልሞችን ስቃዥ ነው እማድረው ቀዝቃዛው ወላፈን ሌሊቱን ሙሉ ሲገርፈኝ አድራለሁ፡፡ ምን ልበልሽ በአጠቃላይ የበረዶ ዘመን ሆኖብናል፡፡ ሔርሚ ናፍቆትሽ አንጃይተር ዲስኦርደር አሲዞኛል፡፡ ወንድሜ ያዕቆብ ግን ሰው ለሰው አይተኛም የሳጥናኤል ጎል ይሆናል ብሎ ከርቤ ሲያጥነኝ ይውላል፡፡ በጭስ ተደብቄ ነው እምውለው፡፡ ምግብም ሁላ ከዳቦ እና ሙዝ ውጪ አልበላ ብሎኛል ደሞ ፖለቲካ አይደለም እሺ! ድፍረት አይሁንብኝ እንጂ ሰኔ 30 በ11ኛው ሰዓት ዳገቱ ላይ የተፈጠረው ክስተት ህሊና ካለው ሰው የሚጠበቅ አልነበረም! ለአባትሽ ስለእኔና አንቺ ግንኙነት ከእነዛ እርጉም ጎረቤታሞቹ አልማዜና ፍርቱና ውጪ የሚያሳብቅለት ሰው አይኖርም፡፡ ሶስተኛው ዓይን ያላቸው እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ የመንደሩ FBI በያቸው የስንቱን ጎረምሳና ኮረዳ እንባ አለባቸው መሰለሽ እኔም ከዛ ቀን በኋላ ቁራኛዬ ሆነዋል፡፡ ውዴ በዛ በክረምት አህያ እንኳን ከማይችለው የአባትሽ ጡጫ፣ እርግጫና ቡጥጫ አውቃለው አላዳንኩሽም ግን ምን ላርግ ከኋላዬ ያልታሰበው ዱላ አከርካሪዬ ላይ ሲያርፍ አባትሽ እግር ስር ተዝለፍልፌ ስወድቅ ጢባጢቤ ተጫወቱብኝ የእግዜር ድልድይ ባላገኝ ኖሮ ይሄኔ የተዘጋው ዶሴ ላይ ነበርን፡፡ ይገርምሻል ከዛ በኋላ ጥላዬን እንኳ አላምነውም፡፡ ይዋጣልን አይባል ነገር በጋንታ አንፈላለግ ነገር ፋዙካሽ ሆኑብኝ፡፡ ቀድሞውን እኮ ወጣት በ97 ያስጨረሰው፣ ወታደር ሳይሆን ወቶ አደር የሆነው የአቶ ጌጤ ልጅ መሆንሽን ባቅ ኖሮ አስፋልት ለብለቡን ወደ ሰባ ደረጃ እቀይረው ነበር፡፡ ብቻ ግን በኔ በደካማው ተፈጣሪ አንደበት መመስገን የማይገባው አምላክ ይመስገን! በ17 መርፌም ቢሆን ለማገገም ችያለው! የወንዶች ጉዳይ የገባው እምዬ ጭሱ ወንድምሽ ግን ይመቸው! ወይኔኔ ያራዳ ልጅ ነው፡፡ አንቺን ሊያገናኘኝ በት በት ሲል ነበር፡፡ ከዛ ግን ብዙ ሳይቆይ አቶ ጌጤ ለቅጣት ክረምትን በሙሉ ወደ እንሳሮ ፈንጂ ወረዳ እንደላኩሽ ነገረኝ፡፡ እነዛ ግን…. ቀቢው፣ባለታክሲው፣ መካኒኩ፣ ሼፉና ትራፊኳ እህትና ወንድሞችሽ በዚህ ነቄ ትውልድ ዘመን የመጬ ዥልጥ ናቸው፡፡ ሀ እና ለን እንኳን የማይለየው ወንድምሽ ቾንቤ እንኳን እንዴት እንደፈነጨብኝ ባየሽ! ብቻ ሙዳቸው ከባድ ሚዛን ነው፡፡ ይህን አብሳላት እንጂ ፈጠራት የማያስብለው ውበትሽን በከንቱ ሊያባክኑት አልወደዱም መሰል ለአዲስ አበባ ሃብታም፣ ለሲቲ ቦይስ፣ ለባለ ስልጣን ልጅ በሌላ አማርኛ ለሌባ ልጅ ነው ሊድሩሽ የሚፈልጉት፡፡ ለእንደእኔ አይነቱ የፊልም አከራይ የከበረ ደሃ አሳልፈው የሚሰጡሽ አይመስሉም፡፡ ፍቅር እና ገንዘብ እኮ ለየቅል ናቸው፡፡ ፍቅር ሲመነዘር ትርፉ ኪሳራ ነው፡፡ ብርር ጤዛ ነው ይመጣል ይጠፋል በያቸው፡፡ እኔ ደግሞ ከገንዘብ ውጪ የጎደለኝ የለም! የልጅ ሀብታም የለም ወደፊት ግን ጠንክሬ ከሰራው ዘጠነኛው ንጉስ የማልሆንበት ምክንያት የለም፡፡ ብቻ ለእኔም እውር አሞራ ቀላቢው ያውቅልኛል፡፡ ሔርሚዬ ስንት ሞት ነው መሰለሽ እኔጋ የገጠመው ስንት… how many times death come to me! we have take pan each other together ብዬ እንጂ…. ኪያዬ ናፍቆትሽ Blind አርጎኛል! የኔ ላምባዲና የምትመለሺበት ቀን አይራቅ እላለው፡፡ 400 ፍቅር ቢመጣ እንኳን ያንቺን እሩብ የሚደርስ የለም! ዛሬ ምን አጋጠመኝ መሰለሽ አመሻሽ ላይ ከሰፈራችሁ ተሻግሮ ያለው ፌርማታ ላይ ቁች ብዬ ብርዱን ከትዝታሽ ጋር ሁለት ታዳጊ ጥንዶች መንገዱ ጠቧቸው እየተላፉ ወንዱ ይጎነትላት ልጂቱ በሳቅ እየፈረሰች ሳለ መንገደኛው ሁሉ በዓይኑ ገርመም እያረገ ታዝቧቸው ያልፋል፡ ፡ መች ገዷቸው እነሱ በራሳቸው ዓለም ይንሳፈፋሉ፡፡ ድምፅሽ፣ ለቅሶሽ ሁላ ሳይቀር ናፍቆት ግሳንግሱን ጭኖ ገነፈለብኝ ሁለንተናዬ አንቺን ፈለገ በዓይኔም በልቤም ላይ ያሳለፍናቸው ሽው አሉኝ፡፡ አንዲት ምሽት ከቤታችሁ አጥር ስር ከኔ መለየት ቢከብድሽ ጥለፈኝ በናትህ አልሽኝ፡ ፡ ወይኔ አሁን ነበር እንሳሮ መኖር፡፡ ጥለፈኝ አልነበር ያልሽው የንፋሱ ፍልሚያን እየሰነጠኩ ላታመልጪኝ አታሩጪኝ እያልኩ በአደይ ወይም በሱፍ አበባ መሃል ገምዛ ወስጄ የሀምሌ ሙሽራ ነበር የማደርግሽ፡፡ ዋሽንት እየነፋሁ አንጀት በሚያርሱ ዜማዎች የባላገር ፍቅር እና የፍቅር ጥግን እየኮመኮምን 79 ዓመት መቀመጥ ነበር፡፡ ለመሆኑ አጎበር ይዘሻል ቢጫ ወባ ተጠንቀቂ በኋላ ኪኒኔ ምናምን ብትይ የሚሰማሽ የለም! ስትመለሺ ለረጅም ጉዞ የሎሚ ሽታ ጥሩ ነው ስላሉ 50 ሎሚ ግዢና ያዢ፡ ፡ መምጫሽ እንደ 9ኛው ሺ ቢርቀኝም ግን በስንዱ አቆጣጠር ጶግሜ7 ትመለሻለሽ አሉ፡፡ የኔ ላምባ፣ የኔ ረቡኒ፣ ህይወቴ የምወድሽ የምሳሳልሽ ስትመጪ ቀዩን ቡትስ ማነው ቀዩን ከንፈርሽን ግጥም እስካደርገሽ እጓጓለሁ፡፡ በመጨረሻም ግን ልነግርሽ የምፈልገው ከቤተሰቦችሽ ጋር መሮኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ፍቅሬን ላድን ስለአንቺ ምንም አደርጋለው! እዋዋን እኔ የአፄ ማንዴላ ልጅ ነኝ! ማንንም አልሰማም፡፡ ሱማሌው ቫንዳም ነው ምሆንባቸው! በቃ ባንቺ አይምጡብኝ ከመጡ ግን መንደሩን ሂሮሺማ ነው ማደርገው! ፍቅር እስከመቃብር ይደገማል! እኔና ቤቴ ግን አንቺን እንጠብቃለን! አፈቅርሻለው ያንቺው ሌባ ድንግሉ ያቤፅ!!!! ጋር አብሬ እየኮመኮምሁ ሳለ ከወዲያ አሻግሮ ጎሚስታው እነሱን በዓይኔ እየሸኘሁ ወድያውኑ ጠረንሽ፣ ሳቅሽ፣ እያሳደድኩ ይዤ በሰማያዊ ፈረስ ጭኜሽ ቼ በላው እያልሁ ያው አሪፍ አይቸኩልም በሚለው ግን ትቼዋለሁ! ልክ እንደ አከራይ እና ተከራይ እንደ ሌባና ፖሊስ መጫወት የፊልም አከራዩ የፍቅር ደብዳቤ
የፊልም አከራዩ የፍቅር ደብዳቤ 16